Get Mystery Box with random crypto!

የመናገሻ ገነተ ጽጌ ሰ/ት/ቤት

የቴሌግራም ቻናል አርማ genetetsige — የመናገሻ ገነተ ጽጌ ሰ/ት/ቤት
የቴሌግራም ቻናል አርማ genetetsige — የመናገሻ ገነተ ጽጌ ሰ/ት/ቤት
የሰርጥ አድራሻ: @genetetsige
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.84K
የሰርጥ መግለጫ

"ለነገዋ ቤተክርስቲያን የምትጨነቁ ከሆነ የሰንበት ትምህርት ቤትን አገልግሎት በልባችሁ አኑሩ፡፡"
ብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-07-14 19:28:28
ሙሉ ቪዲዮውን ለመመልከት

1.3K views16:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 11:45:38
የስማቸው አጻጻፍና የፊደላቱ ትርጉም ( የቅድስት ሥላሴ የስማቸው ፊደላት ትርጉም ያለው በመሆኑ "ስላሴ" ወይም "ሥላሤ" ሳይሆን “ሥላሴ” በማለት የፊደላቱን ቀለም አስተካክሎ መጻፍ ይገባል።)
አምኃ ሥላሴ / መኩሪያ ተስፋዬ
የቅድስት ሥላሴ የስማቸው ፊደላት ትርጉም ያለው በመሆኑ "ስላሴ" ወይም "ሥላሤ" ሳይሆን “ሥላሴ” በማለት የፊደላቱን ቀለም አስተካክሎ መጻፍ ይገባል። ይህ “ሠ” ሠራተኛው ወይም ንጉሡ ሠ የሚባል ሲሆን፤ ይህ “ሰ” ደግሞ እሳቱ ሰ ይባላል።
➧ “ሥላሴ” ከስማቸው ፊደል ሠራተኛው "ሠ" ይገኛል ይኸውም ቅድስት ሥላሴ ዓለምን መፍጠራቸውን ያመለክታል፤ በተጨማሪም ንጉሡ "ሠ" ይባላል ይኸውም ቅድስት ሥላሴ የፈጠሩትን ፍጥረት የሚገዙ የሚያስተዳድሩ መሆናቸውን ያስረዳል። በአጠቃላይ በዚህ "ሠ" ስማቸው መጻፉ ቅድስት ሥላሴ ዓለምን ፈጥረው የሚያስተዳድሩ መሆናቸውን ያስረዳል።
➧ ከስማቸው ፊደል ላይም እሳቱ "ሰ" ይገኛል ይኸውም እሳት ባህር ገደል ካልከለከለው በስተቀር ሁሉን ላጥፋ ቢል ይቻለዋል ቅድስት ሥላሴም ቸርነታቸው ካልገደባቸው በስተቀር ሁሉን ላጥፋ ቢሉ የሚቻላቸው መሆኑን ያስረዳል።
- አንድም፦ እሳት ወርቅን ከእድፉ፣ ምግብንም ከተዋህስያን እንደሚያጠራ ቅድስት ሥላሴም ሰውን ከኃጢኣቱ በምህረታቸው የሚያነጹ ናቸው።
በቅድስት ሥላሴ የስማቸው ፊደል ላይ ሁለት በፊደል ቤት ቢለያዩም ተመሳሳይ ድምጸ ቀለም ያላቸው "ሥ" "ሳ"
እና በፊደል ቤትም በድምጸ ቀለም ከሁለቱ የምትለይ "ላ" እናገኛለን። ይህም "ሥ" እና "ሴ" የአብ እና የመንፈስ ቅዱስ ምሳሌ ናቸው በድምጽ ቀለም መመሳሰላቸውም አብና መንፈስቅዱስ ሰው አልሆኑም፥ "ላ" የወልድ ምሳሌ ናት "ላ" በድምጸ ቀለም ከሁለቱ እንደምትለይ ወልድም በተለየ አካሉ ሰው በመሆኑ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ይለያል።
1.5K views08:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 22:09:18
1.3K views19:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 18:19:46

1.6K views15:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 10:47:25
"ስለመጀመሪያዋ ሕንፃ ቤተክርስቲያን" ከቅዳሴ ማርያም የተወሰደ
በሊቀ ጉባኤ ጌታሁን ደምፀ
++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
ቤተክርስቲያን ቅሉ መጀመሪያ በፊሊጲሲዮስ የተሠራው በእርሷ ስም ነው እና ፤ ጳውሎስ እና በርናባስ በፊሊጲሲዩስ ከተማ ገብተው አስተማሩ ሕዝቡም አመኑ ተጠመቁ ፣ ካመናችሁ ከተጠመቃችሁ እንግዲህ ወደ ቤተ ጣዖት አትሂዱ አሏቸው ፣ የለመድነውንማ ከነሣችሁን መካነ ጽሎት ስጡን አሏቸው፣ እምይዜሰ አንትሙኒ ከመዝ ግበሩ ብሎ አዟቸው ዐረገ። ሕንፃ ቤተክርስቲያን የተጀመረው ከዚያ ወዲህ ነውና ፣ በዘመነ ሐዲስ የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን በእመቤታችን ስም በፊሊጲሲዮስ ከተማ ተመሠርታለች።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!
1.7K views07:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-21 11:54:47
የሰ/ት/ቤታችንን 60ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል በማስመልከት የተዘጋጀ ልዩ ጉባኤ
ከሰኔ 22-23 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ጀምሮ
1.9K views08:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 23:21:13
ቅዱስ ሚካኤል " መልአከ ምክሩ ለልዑል " ለምን ተባለ?

-> እግዚአብሔር አማካሪ ያስፈልገዋልን ? ቢሉ እንደማያስፈልገው በ ት.ኢሳ 40፥13 ላይ " የእግዚአብሔርን መንፈስ ያዘዘ፥ ወይስ አማካሪ ኾኖ ያስተማረው ማን ነው ፤ ወይስ ከማን ጋራ ተመካከረ ወይስ ማን መከረው የፍርድንም መንገድ ማን አስተማረው ዕውቀትንስ ማን አስተማረው የማስተዋልንስ መንገድ ማን አሳየው " በማለት ፈጣሪ እንደ ፍጡር አማካሪ የማያሻው መሆኑን ተገልጾልናል።

መልአከ ምክሩ ለልዑል መባሉ ፦

1. በአማላጅነቱ ነው ፦ በመጽሐፍ ቅዱስ ምልጃ በአማካሪነት ተገልጾ ይገኛል በሉቃ.13፥6 ላይ ጌታችን ፍሬ ያለገኘባትን በለስ መሬት ከምታጎሳቁል ትቆርጥ ባለ ጊዜ የበለስዋ ጠባቂ ጌታውን ልንከባከባት ታፈራም እንደሆነ ለዐመት እንያት አለው ጌታውም የባሪያውን ልመና ፣ ምልጃ (ምክር ) ተቀብሎ በለስዋን ተዋት ይላል በዚህ ክፍል ምልጃ በምክር መንገድ መቅረቡ እንረዳለን ስለዚህ መልአከ ምክሩ ሲልም ከአምላክ የሚያማልድ ማለት ነው፡፡

2. ቧለሟልነቱን የሚገልፅ ነው፦ ፈጣሪ በምድር ላይ ሊያደግ የፈቀደውን ሁሉ ለቅዱሳን ፣ ለመላእክት አስቀድሞ የሚገልጽላቸው በመሆኑ አማካሪው ይባላሉ።
" በእውነት ጌታ እግዚአብሔር ምስጢሩን ለባሪያዎቹ ለነቢያት ካልነገረ በቀር ምንምአያደርግም። " ት. አሞ 3፥7

3. ቅሩበ እግዚአብሔር በመሆኑ ነው :- በቀድሞ ሳጥናኤል ቦታ የተሾመ በመሆኑ ከመላእክት ሁሉ ለጌታችን የቀረበ በመሆኑ መልአከ ምክሩ ለልዑል ተብሏል።
1.7K views20:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-17 19:38:17
የገለፃ እና የትምህርት መርሐግብር "ወቅታዊ የቤተክርስቲያን ፈተና እና መፍትሔው" በሚል ይዘት በሰኔ 26 2014 ዓ.ም ከቀኑ 7፡30 ጀምሮ።
1.5K views16:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-07 06:25:17
1.7K views03:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-04 09:47:50
2.2K views06:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ