Get Mystery Box with random crypto!

መናገር ተስኖኛል ብለህ ታዝናለህን?ለምን ውቡን የዝምታ ጥበብ አትቆርስም ?....እንደ እንቁ የከበ | ጋሻ ƬƲƁЄ ꍟ꓄ꃅꀤꂦᖘꀤꍏ

መናገር ተስኖኛል ብለህ ታዝናለህን?ለምን ውቡን የዝምታ ጥበብ አትቆርስም ?....እንደ እንቁ የከበሩ ፣ እንደ ወርቅ የነጠሩ ዘላለማዊ ዝማሬዎችን አታዳምጥም? ከማይረባ ቃል ውብ ዝምታ እጅጉን ይሻላል። በምስጠት ውስጥ ያማረ ውስጣዊ የዜማ ዥረትም በውጫዊ ጩኸት አይደፈርስም ።"

ሰዉ በፅሞና ከነቃ የልቦናዉን ባህር በሚያምር ባህሪዉ የመዋጀት እምቅ አቅም አለዉ። ለዚህም ዉስጣቸዉ የሰከነ ሰዎች ዝምታ መለያቸዉ ነዉ። ዉስጣቸዉ የተረበሸ ሰዎች ደግሞ ዉጫቸዉንም በረብሻ ይሞላሉ።

ሰው በጥሞና ተቀምጦ አእምሮውን ሲያዋቅር፣ ነፍሱን ከሀልዮቱ ሲያስታርቅ ከራሱ አልፎ በዙሪያው ባሉ ሰዎች ላይ ተጽዕኖ ያደርጋል።

ውስጣቸው የሰለጠነ፣ እግረ-ህሊናቸው የበረታ፣ በአርምሞ የመጠቁ ዜጎች ሲበዙ፣ ያኔ ሀገር ሰላምና አንድነቷ የእውነት ይፀናል።

የእያንዳንዳችን የውስጥ ዓለም ሲያምር እንደ ህዝብ ውጫዊ  ህይወታችንም ይዋባል። ውስጣቸው የተረበሹ ሰዎች ግን ህዝብና ሀገርን ይረብሻሉ።


#አርምሞ  መፅሐፍ
#ዶ/ር ኤልያስ ገብሩ 
#ከመጽሐፍ የተቆነጠረ