Get Mystery Box with random crypto!

#ተአምር_ከትንሽ_ይነሳል! የትኛውም ሰው እንደተወለደ እምነትም ሆነ አመለካከት አይኖረውም። ሁላ | ጋሻ ƬƲƁЄ ꍟ꓄ꃅꀤꂦᖘꀤꍏ

#ተአምር_ከትንሽ_ይነሳል!

የትኛውም ሰው እንደተወለደ እምነትም ሆነ አመለካከት አይኖረውም። ሁላችንም ከተለያየ ቦታ፣ ኃይማኖት፣ ባህል እንዲሁም ልማድ እንወርሳለን። ከእነዚህ ሁሉ ነገሮች የምናገኘውን እኛነት እንዴት በራሳችን ድጋሚ ልንቀርጸው እንችላለን?  ታሪካችን የሆነው በድግግሞሽ ነው።

ስለዚህ ልምድ ቀጣይነት ያለው ድግግሞሽ ነው። ምናልባት ሂሳብ ላይ ጎበዝ አለመሆን፣ የሰዎችን ስም መዘንጋት፣ አቅጣጫ ለመጠቆም መቸገር ባለፈ ታሪክ ውስጥ  ድክመቶቻችን ናቸው።

የትክክለኛው አድራጎት ባለቤት፣ የትክክለኛው ንግግር አዋቂ...ለመሆን ደጋግሞ መሞከር ያስፈልጋል።

የሚፈለገውን ሰው ለመሆን ትናንሽ የሚባሉ ልምዶችን ማዳበር ወሳኝ ይሆናሉ። ምናልባት በአንድ ምሽት ቅጽበት ህይወትን ላይቀይሩ ይችላሉ። ትናንሽ ልምዶች ሲባል አንድ ፑሻፕ መስራት ሰውነትን አይቀይርም፤ ለአንድ ደቂቃ ተመስጦ ማካሄድ ምንም ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ትናንሽ ልምዶችን እያዳበርናቸው ስንሄድ፣ እየደጋገምናቸው ስንመጣ፣ እያሳደግናቸው ስንከሰት የምንፈልገውን ሰው ለመሆን አንቸገርም።

በራስ መተማመን ሲባል እኔ ጸሐፊ እሆናለሁ፣ እኔ እሯጭ እሆናለሁ ብሎ የማውራት አይደለም። ይልቁንም ጸሐፊ ለመሆን ንባብን መደጋገም፣ አሸናፊ ሯጭ ለመሆን ዘወትር ልምምድ ማድረግ ለዛ ግብ ትናንሽ ልምዶችን ማዳበር ይጠይቃል።

#Atomic_Habits_የልማድ_ኃይሎች