Get Mystery Box with random crypto!

ቃሌ ነው.... ባይደክመኝ መኖር እፈልግ ነበር ግን አልቻልኩም ። እኔን በማጣት የምትሰበሩ ነፍ | ጋሻ ƬƲƁЄ ꍟ꓄ꃅꀤꂦᖘꀤꍏ

ቃሌ ነው....

ባይደክመኝ መኖር እፈልግ ነበር ግን አልቻልኩም ። እኔን በማጣት የምትሰበሩ ነፍሶች እንዳላቹ አውቃለሁ ። ከኔ አለመኖር ፍላጎት አይበልጥም ። ሳለሁ አንድም ቀን በድያቹ ይቅርታችሁን ሳልጠይቅ የቀረሁ አይመስለኝም ። ዋጋችሁም ሳይገባኝ ቀርቶ አያውቅም ።

ጋሼ

በርጅና ዘመን በደከመ ወራት ልጄ ልጄ
አሳቢዬ ፤ ፈገግታዬ እንዳትል ብዬ ታግያለሁ.. እውነት አቃቶኝ ነው !!

ሳለሁ የአቅሜን ፈገግ እና ቀና እንድትል ጥሬአለሁ የውለታህን ጥንጥዬም ባታክል ልጅክ ይወድካል ።

ከማንም በላይ እንደምትሰበር አውቃለሁ ። ከማንም በላይ አቅም አልባ እንድምትሆን አውቃለሁ። ልጅክ ስለሆንኩ የኮራኸውን ያህል አንገትክን አስደፋሁህ አይደል ? ይቅር በለኝ
ለኔ ያላጓጓኝ ህይወት ላንተ ምን ይጠቅምሃል ብዬ ነው?

አታቲ

ዘመንሽን ሙሉ በልብሽ እንደምኖር አውቃለሁ ። እንደኔ አይነት ወንድም እንደማታገኚም አውቃለሁ ። አይንሽ በለቅሶ ብዛት እንደሚጠፋ አውቃለሁ ። ተረጂኝ ምድርን ተጠይፌያት ነው ።

እናቴ

ሃዘን እንደማትችይ አውቃለሁ ። እጦት እንደሚሰብርሽ ከሃያ አመት በፊት የሞተች እህትሽ መርሳት ተስኖሽ በየ ጨዋታው ስታስገቢያት አይቻለሁ ። ሁለት ቀን ድምፄን ካልሰማሺኝ ጭር እንደምትይ ፣ሳቅሽ፣ ኑሮሽ ፣ቀልብሽ ፣ አንደሚሰዋ
አውቃለሁ።

አንድ እርምጃ ወደፊት መራመድ ቢያቅተኝ ነው ። በየደቂቃው እሱ ቢኖርልኝ ሃዘንሽ ከእድሜሽ ቀድሞ ይገልሻል ።

ግን

አንድ እኔን ለማሳረፍ እንዴት ይሄን ሁሉ ሰው እገላለሁ ????