Get Mystery Box with random crypto!

#ለሕዝቤ_ባካፍል_ይሻለኛል ሴኔጋላዊው አጥቂ ሳዲዮ ማኔ በአመት እስከ አስር ሚልዮን ዶላር ያህል | ጋሻ ƬƲƁЄ ꍟ꓄ꃅꀤꂦᖘꀤꍏ

#ለሕዝቤ_ባካፍል_ይሻለኛል

ሴኔጋላዊው አጥቂ ሳዲዮ ማኔ በአመት እስከ አስር ሚልዮን ዶላር ያህል ያገኛል። እናም ጋዜጠኞች በእጁ የያዘውን የተሰበረ ሞባይል አይተው፣ ምነው አዲስ መግዛት አቅቶህ ነው ብለው ቢጠይቁት ምላሹ ይህ ነበር

"ስለምን አስር ፌራሪ ያስፈልገኛል? ሃያ የአልማዝ ሰዓቶች እና ሁለት ጀት ምን ይሰራልኛል? ይህን ማድረጌስ ለአለም ምን ይጠቅማታል።

ርቦኝ ያውቃል፤ በክሰል ማውጫ ውስጥ ሰርቼ አውቃለሁ፣ ጫማ አጥቼ በባዶ እግሬም እግር ኳስን ተጫውቻለሁ። እናም አሁን ህዝቤን መርዳት እችላለሁ።

ትምህርት ቤት መገንባትን እመርጣለሁ፤ ለተራቡት ባበላ፣ ለታረዙት ባለብስ ይሻላል። በአገሬ ሴኒጋል ስታዲየም፣ ትምህርት ቤት ገንብቻለሁ። በዛም ላሉ ደሃ ቤተሰቦች ሁሉ በየወሩ 70 ዩሮ እንዲደርሳቸው አድርጌያለሁ።

ውድ መኪና፣ የቅንጦት ቤት ምንም አያደርግልኝም። ካገኘሁት ጸጋ፣ ጥቂትም ቢሆን ለህዝቤ ባካፍል ይሻለኛል"

@gasha_tube