Get Mystery Box with random crypto!

#በዝናብ_ውስጥ1ሳለህ_ጥለውህ_የሄዱትን_አስታውስ ይህ ሰው፣ ንፋስ የቀላቀለ ዝናብ ከመዝነቡ በፊት | ጋሻ ƬƲƁЄ ꍟ꓄ꃅꀤꂦᖘꀤꍏ

#በዝናብ_ውስጥ1ሳለህ_ጥለውህ_የሄዱትን_አስታውስ

ይህ ሰው፣ ንፋስ የቀላቀለ ዝናብ ከመዝነቡ በፊት ከፈረሱ ጋር እየሰራ ነበር። ሆኖም መብረቅ የቀላቀለ ዝናብ መዝነብ ሲጀርም ሁሉም ጥላ ፈልጎ ተጠለለ።

አዎ ሰውየው ፈረሱን ጥሎ አልሸሸም። ዝናብ እየዘነበበት ፈረሱን አቅፎ ቆመ። በሃይለኛ ዝናብ ውስጥ አብረው ቆሙ።

ዝናቡ ሲያባራ፣ በዙሪያው የነበሩ ሰዎች  በግርምት ሲመለከቱት አስተዋል፤

ልብን በሚያሞቅ ፈገግታ ውስጥ ሆኖም እንዲህም አላቸው "እርሱ እኔ በምፈልገው ጊዚያት ጥሎኝ አልሄደምና፣ አሁን እንዴት ተችሎኝ ጥዬው እሸሻለሁ "

በዝናብ ውስጥ ሳለህ ጥለውህ ያልሄዱትን አስታውስ፣ ጸሃይ ስትወጣልህማ ሁሉም ይወድሃል።

@gasha_tube