2022-06-30 12:40:44
ሰላም ሰላም እንዴት ናችሁ ሼፍ ዘሩ ነኝ።
ዛሬ መፃፍ የፈለኩት አንድ የምግብ ባለሞያ ሊኖረዉ ይገባል ብዬ ማስበዉ የባለሞያዉ ስብዕና ምን መምሰል አለበት በሚለዉ እናያለን።
[ ] በፍላጎትና በተነሳሽነት ሙያዉን ወደዉ የመጡ መሆን አለባቸዉ።
[ ] በመንግስት ወይም በግል ደረጃዉን በጠበቀ የሰለጠኑ መሆን አለባቸዉ።
[ ] ሙሉ ጤናማ እና በየ6ወሩ የጤና ምርመራ ያደረጉ (የተደረገላቸዉ)
[ ] ታማኝ ታዛዥ ንቁ ቀልጣፍና የስራ ሞራል ያላቸዉ።
[ ] የሚሰሩበትን መስራቤት ሚስጥር ጠባቂ ና አስተዋይ የሆኑ።
[ ] ሰአት አክብረዉ በስራ ቦታ የሚገኙና አስገዳጅ ምክንያት ካልሆነ በቀር ከስራ መደባቸዉ ላይ የማይቀሩ።
[ ] ለሚሰሩት ስራ በቂ እዉቀት ያላቸዉ ና ለማወቅ ለመማር ዝግጁ የሆኑ ።
[ ] ስለሚሰሩበት ማሽነሪ በቂ እዉቀት ያላቸዉ።
[ ] በጋራ ስራ እሚያምኑ (team work) የሚያምኑ ተባባሪና ችግር ፈቺ የሆኑ ።
[ ] ለእንግዳ እርካታ የሚተጉ ና የሚጨነቁ።
[ ] አደጋ ሳይከሰት በጥንቃቄ የሚሰሩና ሀላፊነት የሚሰማቸዉ።
[ ] ብክነትን ና ብክለትን በመከላከል በምግብ ደህንነት ቅድሚያ የሚሰጡ።
[ ] ቅድሜያ ለድርጅቴ የሚል መንፈስ የተላበሱ መሆን አለባቸዉ።
419 viewsZerubabel ermiys, 09:40