Get Mystery Box with random crypto!

ፍኖተ አትናቴዎስ!

የቴሌግራም ቻናል አርማ fnoteatnatewos — ፍኖተ አትናቴዎስ!
የቴሌግራም ቻናል አርማ fnoteatnatewos — ፍኖተ አትናቴዎስ!
የሰርጥ አድራሻ: @fnoteatnatewos
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 11
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል ውስጥ ከማንኛውም ቤተ እምነት፦
👉ከእስልምና
👉ከተሃድሶ መናፍቃን
እንዲሁም ከሌሎች በኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነታችን ለሚነሱ ማንኛውም ጥያቄዎች መልስ ይሰጥበታል።
ለፌስቡክ፦ fb.com/fnoteatnatewos

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-26 12:22:09 ⨳ በእንተ ዮሐንስ 7:53-8:11 ⨳ የዘማዊቷን ታሪክ የማይቀበሉ ሰዎች የሚያነሱት አንዱ ሙግት ታሪኩ በሁለተኛውና ሦሥተኛው ክፍለዘመን ጀምሮ ይታወቅ የነበረ ቢሆንም በዮሐንስ ወንጌል ላይ የተጨመረው ግን ቆይቶ ነው የሚል ነው። ይህንን ሀሳባቸውን ለመደገፍም የዘማዊቷ ታሪክ በአንዳንድ እደ-ክታባት ውስጥ ከትክክለኛ ቦታው (7:52 እና 8:12 መሃል) ወጥቶ በሌሎች የወንጌላት ክፍሎች መገኘቱን እንደ ማስረጃ…
231 views09:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-21 07:36:14 [7] van Lopik, T.(1995). Once again: floating words, their significance for textual criticism in NT studies Volume 41.p.291.

[8] St.Augustine. Tractate on the Gospel of John.33.5.

@Jacobite_apologetics27
317 views04:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-21 07:36:14 ⨳ በእንተ ዮሐንስ 7:53-8:11 ⨳

የዘማዊቷን ታሪክ የማይቀበሉ ሰዎች የሚያነሱት አንዱ ሙግት ታሪኩ በሁለተኛውና ሦሥተኛው ክፍለዘመን ጀምሮ ይታወቅ የነበረ ቢሆንም በዮሐንስ ወንጌል ላይ የተጨመረው ግን ቆይቶ ነው የሚል ነው። ይህንን ሀሳባቸውን ለመደገፍም የዘማዊቷ ታሪክ በአንዳንድ እደ-ክታባት ውስጥ ከትክክለኛ ቦታው (7:52 እና 8:12 መሃል) ወጥቶ በሌሎች የወንጌላት ክፍሎች መገኘቱን እንደ ማስረጃ ያነሳሉ። ለምሳሌ Miniscule 225 በተሰኘው እደ-ክታብ ላይ የዘማዊቷ ታሪክ በ 7:36 እና 7:37 መካከል ሲገኝ በአንዳንድ እደ-ክታባት ደግሞ ከ 8:12 በኋላ ይገኛል ፤ በዮሐንስ ወንጌል መጨረሻና በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ ሃያ አንድም ታሪኩን የሚጽፉ እደ-ክታባት አሉ። ትችት አቅራቢዎቹ ይህን እውነታ በመያዝ ይህ የሆነው የዘማዊቷ ታሪክ ገና ቋሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ቦታ ስላልነበረው ነው ፤ ይህም የታሪኩን ቀዳማይ አለመሆን ያረጋግጣል የሚል ድምዳሜ ላይ ይደርሳሉ።

ይህ ሙግት ግን የዘማዊቷ ታሪክ የሚገኝባቸውን የእደ-ክታባቱን ክፍሎች ስናጤን ስሑት መሆኑ ፍንትው ብሎ ይታያል። በድሮ ዘመን የነበሩ ክርስቲያኖች እንዳሁን ዘመን ክርስቲያኖች ሁሉ ቅዳሴና በቅዳሴው መሃል የሚደረግ የወንጌል ንባብ የነበራቸው ቢሆንም ለዚህ ተብሎ የተዘጋጀ የወንጌል መጽሐፍ ግን ስላልነበራቸው የወንጌላቱ እደ-ክታብ ላይ ለዕለቱ የተደነገገውን የወንጌል ንባብ ምልክት በማድረግ ይጠቀሙ ነበር። አብዛኞቹ የቅዳሴ መጽሐፍት ታዲያ ለበዓለ አምሳ (Pentecost) ክብረ በዓል የሚደነግጉት የወንጌል ንባብ የዮሐንስ ወንጌል 7:37-7:52 እና 8:12 ነው።[1] ይህ ማለት አንባቢው ከ 7:37 ጀምሮ እስከ 7:52 ያነብና የዘማዊቷን ታሪክ ዘልሎ ወደ 8:12 ይሄዳል። ስለዚህ የ Miniscule 225 ጸሐፊ የወንጌል ንባቡን ለአንባቢው ቀላል ለማድረግና አንባቢው በቅዳሴ መሃል ንባቡን አቋርጦ 8:12 ን በመፈለግ ጊዜ እንዳያጠፋ ሲል የዘማዊቷን ታሪክ ከነበረበት ቦታ አውጥቶ ከበዓለ አምሳ ንባብ መጀመሪያ (7:37) በፊት አስቀምጦታል።[2] ሌሎች እደ-ክታባትም (GA 145 GA 476 GA 1349) በተመሳሳይ የዘማዊቷን ታሪክ ከቦታው አውጥተው ከበዓለ አምሳ ንባብ ማለቂያ (8:12) በኋላ ያስቀምጡታል። ይህ ከላይ እንደገለጽነው የወንጌል ንባቡን ቀላል ለማድረግ ሆን ተብሎ የተደረገ እንጂ የዘማዊቷ ታሪክ በጊዜው የተረጋገጠ ቦታ ስላልነበረው የተደረገ አይደለም። በወንጌላት እደ-ክታባት ውስጥ ለቅዳሴ ንባቦች ሲባል መሰል የቦታ ቅያሬዎች ሆን ተብለው ይደረጉ እንደነበር ብዙ ምሁራን የሚስማማሙበት ጉዳይ ነው።[3][4][5][6]

ታሪኩን በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 21 ማለቂያ ላይ የሚጽፉ እደ-ክታባትንም ስንመለከት ተመሳሳይ ምክንያት እንዳላቸው ማረጋገጥ እንችላለን። እነዚህ እደ-ክታባትን ይጠቀሙ የነበሩ ክርስቲያኖች ሰርጊየስና ባከስ የተባሉ ሰማዕታትን በሚያስቡበት ቀን (ጥቅምት 7 እ.ኤ.አ.) የሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ ሃያ አንድን ሲያነብቡ የቅድስት ፔላጊያ ዘአንጾኪያን አመታዊ በዓል በሚያከብሩበት ቀጣዩ ቀን (ጥቅምት 8) ደግሞ የዘማዊቷ ታሪክ ይነበባል።[7] ስለዚህ የእነዚህ እደ-ክታባት ጸሐፊ የሁለቱን ተከታታይ ቀናት ንባቦች በቅደም ተከተል ለማስቀመጥ ሲል የዘማዊቷን ታሪክ ከቦታው አውጥቶ በሉቃስ 21 መጨረሻ ላይ አስቀምጦታል።

ታሪኩን በዮሐንስ ወንጌል መጨረሻ ላይ የሚያስቀምጡ እደ-ክታባት መኖራቸውም የራሱ ማብራሪያ ስላለው ታሪኩ የተረጋገጠ ቦታ የሌለው እንደነበረ አያሳይም። GA 1 እና GA 1582 የተባሉት እደ-ክታባት ለምሳሌ ለምን ይህንን ክፍል በወንጌሉ መጨረሻ እንዳስቀመጡት ይገልጻሉ-

"የዘማዊቷ ታሪክ በአብዛኞቹ እደ-ክታቦቻችን አይገኝም ፤ እንደ ዮሐንስ አፈወርቅና ቄርሎስ ዘእስክንድርያ የመሰሉ አባቶችም አስተያየት አይሰጡበትም።...ስለዚህ በሌሎች የተወሰኑ ቅጂዎች ከሚገኝበት ቦታ (ማለትም "ነቢይ ከገሊላ እንዳይነሣ መርምርና እይ" ከሚለው አንቀጽ በኋላ) እንዲወጣ ሊደረግ ችሏል።"

ስለዚህ በነዚህ ቅጂዎች የዘማዊቷ ታሪክ በዮሐንስ ወንጌል መጨረሻ ላይ መገኘት ታሪኩ የተረጋገጠ ቦታ እንዳልነበረው የሚያሳይ ሳይሆን (ከዮሐንስ 7:52 በኋላ እንደሚገኝ አብዛኞቹ እደ-ክታባት ይመሰክራሉ) እነዚህን እደ-ክታባት የያዙ ሰዎች የታሪኩ እውነተኛነት ላይ ጥርጣሬ እንደነበራቸው ብቻ የሚያመለክት ነው። GA 105 የተሰኘው እደ-ክታብ በአንጻሩ ታሪኩን በዮሐንስ ወንጌል መጨረሻ ላይ ካስቀመጠው በኋላ በገጹ ግርጌ በምን ቀን መነበብ ያለበት የወንጌል ንባብ እንደሆነ ይናገራል። ይህ የሚያሳየው የዚህ እደ-ክታብ ጸሐፊ የታሪኩን እውነተኛነት ተጠራጥሮ ወይም የት ቦታ እንደሚገባ ስላላወቀ ያደረገው ሳይሆን ከላይ እንደተጠቀሱት እደ-ክታባት ሁሉ የበዓለ አምሳ ንባብ (7:37-8:12) እንዳይቋረጥ ሆን ብሎ ያደረገው መሆኑን ነው። ከዚህ ባለፈ ሳይነሳ መታለፍ የማይገባው እውነታ የዘማዊቷን ታሪክ ከቦታው የሚለውጡት ሁሉም እደ-ክታባት ከአስረኛው ክፍለዘመን በኋላ የተጻፉ ሲሆኑ ከነዚህ ቅጂዎች መጻፍ አምስትና ስድስት መቶ ዓመታት በፊት የኖሩት እንደ ሊቁ አውግስጢኖስ ፣ አምብሮስዮስና ይሩማሲስ የመሰሉ አባቶች ግን ታሪኩ በትክክለኛ ቦታው (7:52 እና 8:12 መካከል) እንደነበር ይመሰክራሉ።[8] ይህንን ታሪክ የሚይዘው የቀደመ የሚባለው በ 400AD አካባቢ የተጻፈው Codex Bezae በተመሳሳይ ታሪኩን በዚሁ ቦታ ያስቀምጠዋል። ስለዚህ የዮሐንስ ወንጌል 7:53-8:11 መግቢያ ቦታ አጥቶ ሲዞር የነበረ ታሪክ ሳይሆን ከጥንትም ጀምሮ አሁን በምናውቀው ቦታ ላይ ተጽፎ የነበረ ታሪክ መሆኑ እርግጥ ነው።

[1] Wikgren, Alan P.(1934). The lectionary text of the pericope in Journal of Biblical literature. Volume 53 No.2.pp.188-9. The society of biblical literature.

[2] Robinson, Maurice A.(2000). Preliminary Observations Regarding the Pericope Adulterae Based upon Fresh Collations of Nearly All Continuous text Manuscripts and All Lectionary Manuscripts Containing the Passage.pp.43-45.

[3] Toensing, Holly Joan.(1998). The Politics of Insertion: The Pericope of the Adulterous Woman and Its Textual
History. pp.169-76. University of Vanderbilt.

[4] van Lopik, T.(1995). Once again: floating words, their significance for textual criticism in NT studies Volume 41.pp.287-291.

[5] Lindars, Barnabas.(1972).The Gospel of John.p.307. Oliphants publishing.

[6] Johnson, Alan F.(1964). A Re-examination of the Pericope Adulterae, John 7:53–8:11.p.62. Dallas Theological Seminary.
281 views04:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 21:46:10 ፨ በእንተ ማርቆስ 16:9-20 ፨ @Jacobite_apologetics27 ክፍል ፫ ከዚህ በፊት የማርቆስ ወንጌልን የመጨረሻ ክፍል ታሪካዊነት ውድቅ ለማድረግ የሚቀርቡ ማስረጃዎችን ደካማነትና የክፍሉን ታሪካዊነት የሚያሳዩ ማስረጃዎች አይተናል። ሌሎች ይህንን ክፍል የሚተቹ አካላት የሚጠቅሷቸውና በዚህ ክፍል የምናያቸው አባቶች ደግሞ አውሳብዮስ ዘቂሳርያና ይሩማሲስ (ጄሮም) ናቸው። አውሳብዮስ…
431 views18:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-07 04:30:29 ✟#መንፈስ_ቅዱስ✞ ክፍል 1 አንድ አምላክ በሚሆን በአብ ፡ በወልድ ፡ በመንፈስ ቅዱስ ስም! በትምህተ ሥላሴ ክፍላችን ላይ እንዳየነው ከሶስቱ ቅዱስ አንዱ ቅዱስ ፤ ከሶስቱ አካል አንዱ አካል መንፈስ ቅዱስ ነው። በዚህ እና በሌሎች ጽሁፎች ስለ መንፈስ ቅዱስ ብቻ የምንመለከት ሲሆን መንፈስ ቅዱስ አካላዊ ወይስ ዝርው ኋይል?ስለመንፈስ ቅዱስ አምላክነት መፅሀፍ ምን ይላል?እና ስለ ጰራቅሊጦስ…
308 viewsedited  01:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-22 06:48:23 ፨ በእንተ ማርቆስ 16:9-20 ፨ ክፍል ፪ ከዚህ ቀደም እንዳየነው በሁለተኛው ክፍለዘመን የተነሱ አባቶች የማርቆስ ወንጌልን የመጨረሻ ክፍል ከማወቅ አልፈው ለስብከት ይጠቀሙበት ነበር። የክፍሉን እውነተኛነት የሚጠረጥሩ አካላት የሚያቀርቧቸው ሁለት ኮዴክሶችን የተመሰረቱ ሙግቶች እጅግ ደካማ መሆናቸው ሲበዛ ግልጽ ነው። የዚህን የወንጌል ክፍል ታሪካዊነት የበለጠ የሚደግፈው ደግሞ…
524 views03:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-08 08:50:18 ቅዱሳት ሥዕላት (Icons) በመጀመሪያዎቹ የክርስትና ክ/ዘመናት [100-400 ክ/ዘመን]

[ክፍል-3]

በጥንቷ ቤተ ክርስቲያን ሥዕላትን የመቀበልና የማክበር ነገር አልነበረም ለማለት የፕሮቴስታንት ጸሐፊያን የሚያቀርቡት ሁለተኛው ሙግት የቤተ ክርስቲያን አባቶች ሥዕላትን ስለ መቀበል እና ስለ ማክበር አላስተማሩም የሚል ነው። በዚህ ብቻ ሳይገደቡ እንዲያውም የቤተ ክርስቲያን አባቶች ሥዕላትን መቀበል እንደሌለብን አስተምረዋል የሚል መከራከሪያ ነጥብ ያነሳሉ። የፕሬስባይቴራን ቤተ ክርስቲያን ፓስተር የሆነው ፕሮፌሰር ስቴፈን ዌጅዎርዝ ካልቪንስት ኢንተርናሽናል (Calvinist International) በተባለ መካነ ድር ላይ "ግልጽ በሆነ ሁኔታ ሥዕላትን የሚቃወም የአባቶች ምስክርነት አለ" በማለት ጽፏል። እንደ ማስረጃ የጠቀሳቸው ሀሳቦች "Is There Really a Patristic Critique of Icons" በሚል ርዕስ Orthodoxy and Heterodoxy በተሰኘ ብሎግ ላይ "Ancient Faith Ministries" አምድ ላይ የማያፈናፍን ሰፋ ያለ መልስ ተሰቶታል። በተጨማሪም በካቶሊክ ኢይሳይክሎፒዲያ ላይ "Veneration of Icon" በሚለው አምድ ላይ ይሄንን በሚመለከት የተጻፈውን ማየቱ ጠቃሚ ነው። በዚህ ጽሑፍ "የቤተ ክርስቲያን አባቶች ሥዕላትን ስለ ማክበር ምንም አላስተማሩም" የሚለውን ሙግት እንፈትሽው!

ቅዱስ ሜቶዲየስ (St Methodius Olympus)

"የነገሥታቶቻችንን ሥዕል እጅግ ውድ በሆኑት በወርቅና በብር ባይሰሩ እንኳን ሁላችንም እናከብረዋለን። እነዚህ ሥዕሎች ከውድ ነገሮች ቢሰሩም ሆነ ባይሰሩም ሥዕላቱን አናከብርም ብንል ተቃዋሚ የምንሆነው ሥዕላቱ ከተሰሩበት ዕቃ ጋር ሳይሆን ከንጉሡ ጋር ነው። ስለዚህ ለእግዚአብሔር መልአክ ሥዕል ክብር እንሰጣለን" (Discourse on the Resurrection, 2)

ቅዱስ ባስልዮስ (St. Basil the Great)

" ስለ ንጉሥና ስለ ንጉሡ ሥዕል ስንናገር ስለ ሁለት የተለያዩ ነገሥታት መናገራችን አይደለም። የንጉሡ ግርማ እና ክብር ለሁለት አይከፈልም። ምክንያቱም ለሥዕሉ የምንሰጠው ክብር ወደ ሥዕሉ ባለቤት የሚያልፍ ነው።" (On the Holy Spirit, 18.45)

ይህንን አይነት ትምህርት ስለ ሰማዕታት በደረሰው ድርሳኑ ከሰማዕታቱ ሥዕል ጋር በተያያዘ አስተምሮታል። በተጨማሪም ትንቢተ ኢሳይያስን በተረጎመበት ድርሳኑም ሥዕላትን ስለ ማክበር አስቀምጦልናል።[1]

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ (St John Chrysostom)

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ቅዱስ ሜልቲዮስ (St Meletios) ከሞተ በኋላ ምዕመናን የቅዱሱን ሥዕል መሳላቸው ለቅድስናው ማስረጃ አድርጎ ይጠቅሰዋል። (Homily on Praise of Saint Meletios) ይህ የጥንት ክርስቲያኖች የቅዱሳንን ሥዕል የመሳል ልማድ እንደነበራቸው ማረጋገጫ የሚሰጥ ነው። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በሌላ ትምህርቱ አንድ በጦርነት ድል ያደረገን ሰው ሁሉም ሰው በሚችለው መልኩ ሊያከብረው እንደሚችል ይናገራል። በንግግር፣ በመጽሐፍ፣ በሥዕል ይህ ሊደረግ ይችላል። ነገር ግን የተሸነፈ ሰው ሥዕል ማንም ሊያከብረው አይችልም" በማለት ይናገራል። (Conversation on Psalm 3) አይደለም ቅዱሳት ሥዕላት በተለያየ መልኩ የሚከበሩ ሰዎች ሥዕልም መከበር ሊከበር እንደሚችል ይነግረናል።

ቅዱስ አትናቴዎስ (St. Athanasius the Great)

"...የአንድ ገዢን ሥዕል ብንወስድ ሥዕሉ የገዢውን ሁኔታ ይገልጽልናል። ሥዕል የገዢው ምሳሌ(ውክል) ነው። ስለዚህ ያንን ሥዕል የሚመለከት ገዢውን በውስጡ ያያል። እንዲሁም ገዢውን የሚመለከት በሥዕል ውስጥ ያየውን ሰው ያስታውሳል። ሥዕሉን የሚያከብር ገዢውን ያከብራል። ሥዕሉ ገዢው የሚገለጥበት ነውና" ( Discourse Againest the Arians, 3.5)

ቅዱስ አትናቴዎስ በቀጥታ (Explicitly) ቅዱሳት ሥዕላትን ስለ ማክበር ባይናገርም ሥዕላትን ማክበርን የሚቃወም ሰው እንዳልነበር እንረዳለን። ዓለማዊ የሆኑ ሥዕላትን ማክበር ማለት ምን ማለት እንደሆነ ካስተማረ ቅዱሳት ሥዕላትን ማክበርን ይቃወም ነበር የሚለው ሙግት አያስኬድም። በቅዱስ አትናቴዎስ ትምህርት መሠረት ሥዕላት የተሳለውን አካል የሚገልጹ ሲሆኑ ለሥዕሉ የሚሰጠው ክብር በቀጥታ ከሥዕሉ ባለቤት ጋር የሚገናኝ እንደሆነ አስተምሯል።

ቅዱስ አትናቴዎስ በሌላ ሥራው " እኛ ግሪካውያን እንደሚያደርጉት ሥዕላትን እንደ ጣዖት አናመልክም። ይሄ በእግዚአብሔር የተከለከለ ነው። ዋነኛው ዓላማችን የምንወደውን አካል ነጸብራቅ በሥዕላቱ ውስጥ ማየት ነው። ልጆችንን ወይም ወላጆቻችንን በልባችን ያለውን ፍቅር ለማሳየት እንደምንስማቸው ሥዕላቱን እንስማለን።" [2] በማለት ይናገራል።

ቅዱስ አምብሮስ ዘሚላን (St. Ambrose of Milan)

ቅዱስ አምብሮስ ቅዱስ ጳውሎስ አስቀድሞ በሥዕል በሚያቀው መልኩ እንደተገለጠለት ይናገራል። ( Epistle to the Italians)

አውሳብዮስ ዘቂሳርያ (Eusebius of Caesarea)

አውሳብዮስ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ መጽሐፉ በወቅቱ የኢየሱስ ክርስቶስ ሥዕል እንደነበረ፣ በተጨማሪም የቅዱስ ጴጥሮስና የቅዱስ ጳውሎስም ሥዕል እንደ ተመለከተ ጽፏል። በዚህም አንዳንድ ቅዱሳት ሥዕላት ያደርጉ የነበረውን ተአምር እና ለሥዕላት የሚሰጠውን ክብር ጽፎልናል። (Church History , 7.18)

በተጨማሪም ዛሬም ድረስ ሕያው ሆነው በሚገኙ የክርስትና ጽሑፎች (Inscription) ውስጥ ለሥዕላት ይደረግ የነበረውን ክብር የሚያሳዩ ሥራዎች ይገኛሉ። ለዚህም በተቀደሰው ሥፍራ የድንግል ማርያምን ሥዕል ያከብሩ እንደነበሩ የሚያሳዩ ጽሑፎች አሉ። [3] ከላይ የጠቀስናቸው አባቶች ለሥዕል የሚደረገው ክብር በቀጥታ ከሥዕሉ ባለቤት ጋር የሚገናኝ እንደሆነ መረዳት የነበራቸው ናቸው። በክፍል-1 ጽሑፍ በመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን ዘንድ የነበረውን የሥዕል አቀባበል የተመለከትን ሲሆን በዚህ ጽሑፍ ደግሞ መቀበል ብቻ ሳይሆን የሥዕላት ክብር (Veneration of Icons) እንደነበረም ለመዳሰስ ሞክረናል። የፕሮቴስታንት ጸሐፊያን በጥልቀት የአባቶችን ትምህርት እንዲያጠኑም ግብዣዬ ነው።

ማጣቀሻዎች

[1] Homily on the Forty Martyrs, 2 and Commentary on Isaiah 13.3

[2] Hundred Chapters to Antiochus the perfect , Ch. 38

[3] Early Christian Attitudes toward Images, p. 100-102

ስብሐት ለእግዚአብሔር!
633 views05:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-07 13:16:02 ቅዱሳት ሥዕላት (Icons) በመጀመሪያዎቹ የክርስትና ክ/ዘመናት [100-400 ክ/ዘመን]

[ክፍል-2]

በጥንቷ ቤተ ክርስቲያን ቅዱሳት ሥዕላትን የመጠቀም እና የማክበር ነገር እንዳልነበር የፕሮቴስታንት ጸሐፊያን ይናገራሉ። ሀንስ ቤልቲንግ የተባለ አንድ የተሃድሶ አቀንቃኝ "በመጀመሪያ የክርስትና ሃይማኖት ሥዕላትን ሙሉ ለሙሉ እንደማይቀበል፣ በተለይም ሥዕላትን ማክበር የተከለከለ እንደሆነ ሁሌም አዕምሮአችን ውስጥ መቀመጥ አለበት" በማለት ይናገራል። [1] ለዚህም በዋናነት ሁለት ምክንያቶችን ይጠቅሳሉ። የመጀመሪያው አይሁድ ፀረ-ሥዕል (Icnophobic) ናቸው የሚል መነሻን የሚያስቀምጥ ነው።[2] ሙግታቸውን በአመክንዮ ስንደረድረው እንዲህ ይቀመጣል።

Premise 1: የሙሴ ሕግ የተሰጠው ለአይሁድ ነው። የሙሴ ሕግ ሥዕላትን እንዳንጠቀም ይከለክላል።

Premise 2: አይሁድ በሙሴ በኩል በተሰጠው ሕግ መሠረት ሥዕላትን አይቀበሉም።.

Premise 3: አብዛኛዎቹ የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች ከአይሁድ ወደ ክርስትና የመጡ ነበሩ።

መደምደሚያ (Conclusion): በመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን ሥዕል ተቀባይነት አልነበረውም።

ይህ የፕሮቴስታንት ጸሐፊያን ሙግት በመጽሐፍ ቅዱስ፣ በታሪክ እንዲሁም በሥነ-ቁፋሮ ግኝቶች ( archeological Findings) ሲመዘን ውድቅ ነው። በተለይ ከ 20ኛው ክ/ዘመን በኋላ የተገኙ የሥነ-ቁፋሮ ግኝቶች ምስክር ከመሆናቸው በፊት ከላይ የተጠቀሰው የፕሮቴስታንት ጸሐፊያን ሙግት የበረታ ነበር። "የተቀረጸ ምስል ለአንተ አታድርግ" (ዘጸ20:4) የሚለው ሕግን አይሁዳውያን በምን መልኩ ተጠቀሙበት? በመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን ዘመን የነበሩ አይሁድ የሥዕል አቀባበል ምን ይመስል ነበር? የሚለው የትኩረት ነጥብ ሆነው ተዳሰዋል።

"የተቀረጸ ምስል ለአንተ አታድርግ" የሚለው ቃል ለእስራኤላውያን የተሰጠው በተደጋጋሚ በጣዖት አምልኮ ይወድቁ ስለ ነበር ነው። እግዚአብሔር በተለያዩ ጊዜዎች ሥዕላት እንዲሳሉ እና እንዲቀረጹ ማዘዙ ይህ ሕግ በቀጥታ የሚመለከተው የአሕዛብን ጣዖታት እንደሆነ የሚያስረዳ ነው። ሥዕለ ኪሩብ በታቦቱ ላይ (ዘጸ25:18)፣ በድንኳኑ መጋረጃ ላይ (ዘጸ26:1)፣ በቤተ መቅደስ ውስጥ (1ነገ6:23)፣ በቤተ መቅደስ ግርግዳዎች ላይ (1ነገ6:29) እንዲሰራ እግዚአብሔር አዟል። እዚህ ላይ የፕሮቴስታንት ጸሐፊያን ሁለት አማራጭ አላቸው። የመጀመሪያው ሥዕለ ኪሩብ ጣዖት ነው ብሎ መደምደም ሲሆን ሁለተኛው አማራጭ ደግሞ በጣዖት እና በሥዕላት መካከል ልዩነት እንዳለ መረዳት ነው። ሥዕለ ኪሩብ በእግዚአብሔር ትዕዘዝ የተሰራ እንደመሆኑ የመጀመሪያው አማራጭ የሚያስኬድ አይደለም። በሰሎሞን ቤተ መቅደስ ውስጥ የኪሩቤል፣ የዘንባባ ዛፍ እና የፈነዳ አበባ ሥዕል ነበር። (1ነገ6:21-29) እሥራኤላውያን ከደዌያቸው የዳኑበት የነሐሱ እባብ የተቀረጸ ምስል ነበር። (ዘኁ27:8-9) ነቢዩ ሕዝቅኤል በጡብ ላይ የእየሩሳሌምን ከተማ እንዲሥል ተነገሮት ነበር። (ሕዝ4:1) የቃል ኪዳኑ ታቦት እራሱ የተቀረጸ ምስል ነው!

የተቀረጸ ምሥል ለአንተ አታድርግ ከሚለው ሕግ ጋር ከግብጽ ምድር ያወጣኹህ አምላክህ እግዚአብሔር እኔ ነኝ፣ በላይ በሰማይ ፣ በምድርም በታች፣ በምድርም በታች በውኃ ካሉት የማናቸውም ምሣሌ ለአንተ አታድርግ የሚል ቃል አብሮ ተቀምጧል። በዚህ ቦታ ላይ በመሠረታዊነት ሦስት ቦታዎችን (በሰማይ፣ በምድር፣ በውኃ) የጠቀሰ ሲሆን አብሮ ግብጽንም ያነሳታል። በግብጽ ምድር በነበረው የጣዖት አምልኮ በሰማይ ካሉት Horus (god of the Sky) ፣ Ra ( god of sun) ፣ Khonsu (god of the moon) ፣ Nut (Sky goddess) የሚባሉ ጣዖታት ይመለኩ ነበር። በምድር ካሉት ደግሞ Geb (god of earth) ፣ Aker (god of earth) ይመለኩ ነበር። ከምድር በታች በውኃ ካሉት Bairthy (goddess of the water) ፣ Osiris (god of the water) የሚባሉ ጣዖታት ይመለኩ ነበር። [3] ይህ የግብጾችን የጣዖት አምልኮ አጠቃላይ ሁኔታን የሚገልጽ ነው። ለእስራኤላውያን የተሰጠው የሙሴ ሕግ በግብጽ ምድር የተመለከቷቸውን ጣዖታት እንዳይሰሩ የሚከለክል እንደነበር መገንዘብ ቀላል ነው። ይሄንን እግዚአብሔር በነቢዩ ሕዝቅኤል አድሮ በተናገረው ቃል ማረጋገጥ የሚቻል ነው።

"በዚያ ቀን ከግብጽ ምድር ወዳዘጋጀሁላቸው፥ ወተትና ማር ወደምታፈስሰው፥ የምድርም ሁሉ ጌጥ ወደምትሆን ምድር አወጣቸው ዘንድ ማልሁላቸው፤
እኔም። ከእናንተ እያንዳንዱ የዓይኑን ርኵሰት ይጣል፥ በግብጽም ጣዖታት አትርከሱ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ አልኋቸው።" (ሕዝ20:6-7)

በአጠቃላይ ዘጸ20:4 በቀጥታ የግብጽ ጣዖታትን የሚመለከት ቃል እንደሆነ ከላይ በተጠቀሰው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል መረዳት የሚቻል ነው። አይሁድ በዘጸ20:4 ምክንያት ሙሉ ለሙሉ ሥዕላትን ሊቀበሉ የማይችሉ ናቸው የሚለው ሙግትም እውነት ያልሆነ ሀሰት ነው። ሌላኛው የትኩረት ነጥባችን በመጀመሪያዎቹ የክርስትና ክ/ዘመናት አይሁድ ለሥዕላት የነበራቸው አቀባበል እንዴት ነበር? የሚለው ይሆናል።

በመጀመሪያዎች ክ/ዘመናት በአይሁድ እና በክርስቲያኖች ዘንድ ስለ ነበረው ሥርአተ አምልኮ ከሚታዩ ማስረጃዎች መካከል የጥንታዊቷ ዱራ ኢሮፖስ (Dura Europos) ግኝት ታዋቂው ነው። Dura Europos የአይሁድም የክርስቲያኖች ከተማ የነበረች ሲሆን በአሁኗ ሶሪያ ድንበር አካባቢ የምትገኝ ናት። በዚህ ከተማ የተገኙት ማስረጃዎች የፕሮቴስታንት ጸሐፊያንን ብዕር ማጠፍ የቻለ ነው። በ 233 A.D የነበረችው ጥንታዊት ከተማ የአይሁድ ማኅበር (Synagogue) ሕይወትን በግልጽ ታሳያለች። በዚች ጥንታዊት ከተማ ውስጥ የአይሁድ ማኅበር የነቢያት (የሙሴ፣ የዳዊት፣ የሕዝቅኤል፣ የኤልያስ) ሥዕል እንደነበራቸው የተገኙት ማስረጃዎች ያሳያሉ። የይስሐቅ መሥዋዕት፣ የአብርሃም ታሪክ የሚያሳዩ ሥዕላትም በዚው ሥፍራ ይገኛሉ። [4] ይህ ብቻ ሳይሆን የተለያዩ አይሁድ ማኅበራት (Synagogues) ሥዕላትን ይቀበሉ እንደነበር የሚያሳዩ የሥነ-ቁፋሮ ግኝቶች አሁንም ድረስ በመውጣት ላይ መሆናቸውን ማስረጃዎች ያሳያሉ። [5] አይሁድ ሙሉ ለሙሉ ሥዕላትን የማይቀበሉ (Aniconic) ናቸው የሚለው ሙግት ሀሰት መሆኑን እነዚህ ግኝቶች መስክረዋል።

በክፍል-3 ሁለተኛውንና የፕሮቴስታንት ጸሐፊያን የመቃወሚያ ሙግትን በሚመለከት ጽሑፍ ይዤ የምመለስ ይሆናል!

[1] Hans Belting, Likeness and Presence, 1990

[2] John B.Carpenter, Icons and the Eastern Orthodox Claim to Continuity with the Early Church p. 107-108

[3]Orthodoxidation, Icons or Idols? A Faulty Understanding of Exodus 20, 2021

[4] Fine, Steven, Art and Judaism in the Greco-Roman World: toward a New Jewish Archaeology, Cambridge Ch.11

[5] Urman, Dan, and Paul, Ancient Synagogues Historical Analysis and Archaeological Dicovery, Leid, 1998

ስብሐት ለእግዚአብሔር!
784 views10:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-06 09:51:16 ቅዱሳት ሥዕላት (Icons) በመጀመሪያዎቹ የክርስትና ክ/ዘመናት [100-400 ክ/ዘመን]

[ክፍል-1]

ቅዱሳት ሥዕላት በኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ሥርአተ አምልኮ እና በቤተ ክርስቲያን ሕይወት ውስጥ ጉልህ ድርሻ አላቸው። በዚህ ጽሑፍ ውስጥ በመጀመሪያዎቹ ክ/ዘመናት ውስጥ ቅዱሳት ሥዕላት በምን መልኩ እንደተገለጹ ታሪካዊ ዕድገቱን ለመዳሰስ ተሞክሯል። ስዕላትን ለማይቀበሉ ሰዎች ዕቅበተ እምነታዊ የመሆን ዕድልም አለው!

በመጀመሪያዎቹ ክ/ዘመናት የክርስቲያኖች ቤት ግድግዳ ውክላዊ(Symbolic) በሆኑ ሥዕሎች የተሞላ ነበር። የአሳ፣ የመርከብ፣ የበግ፣የእረኛ፣ የወይን፣ የዳቦ ሥዕሎች በጥንቷ ቤተ ክርስቲያን ሕይወት ውስጥ ይታይ ነበር። [1] ዋልተር ሎውሪ የተባለ የጥንቷን ቤተ ክርስቲያን የጥበብ ስራዎች ያጠና ሰው "Art in the Early Church" በተሰኘ መጽሐፉ እንዲህ ይላል:-

"የጥንቷ ቤተ ክርስቲያን ስነ ጽሑፍ እጅግ በጣም ውክላዊነት (Symbolical) እና ምሳሌያዊነት (Allegorical) የሚታይበት ነበር። [2]

የተለያዩ የክርስትና አስተምህሮዎች በእንስሳት ተወክለው ይቀርቡ ነበር። የዚህ ምክንያቱ በወቅቱ ታላቁ ግዛት የነበረው የሮም ኢምፓዬር እምነታቸውን በነጻነት እንዲገልጹ ስለ ማይፈቅድላቸው ነበር። በብሉይ ኪዳን የተጠቀሰው የበግ ጠቦት (ዘኁ28÷3) ለኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ሆኖ በጥንቷ ቤተ ክርስቲያን በብዛት ይወከል ነበር። ይኸውም የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ የሚለውን የሚያስረዳ ነው።(ዮሐ1:9፣ ራዕ14:1) ተራራ የቤተ ክርስቲያን ውክል ሆኖ ይታይ ነበር። አሳ በዋናነት ሁለት ነገሮችን ለማመልከት ጥቅም ላይ ይውል ነበር። የመጀመሪያው አሳን የሚገልጸው "ICHTHUS" የሚለው የግሪክ ቃል "Jesus Christ, Son of God, Savior - ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ አዳኝ" የሚለውን በመወከል ያገለግል ነበር። በሁለተኛ ደረጃ አሳ በውኃ ጥምቀት የሚገኘውን አዲስ ልደት ለመግለጽ በውክልና ይጠቀሙበት ነበር። ጠርጡልያን፣ የእስክንድርያው ቀሌምንጦስ፣ የሂጶው አውግስጢኖስ እና ቅዱስ ኤራንየስ በስራዎቻቸው ውስጥ አሳ በመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የታወቀ እንደነበረ ጠቁመዋል። [3] ቸር ጠባቂ የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በእረኛ ውክላዊ ሥዕል ይገልጡት ነበር። (ዮሐ10÷14)

ዘመነ ሰማዕታት በመባል በሚታወቀው የመጀመሪያዎቹ ሶስቱ የክርስትና ክ/ዘመናት ክርስቲያኖች እስክንድርያ እና በሮም በሚገኙ ዋሻዎች (Catacombs) ውስጥ ሥርአተ አምልኳቸውን ይፈጽሙ ነበር። በእነዚህ ዋሻዎች ውስጥ ዛሬም ድረስ ምስክር ሆነው የተቀመጡ ቅዱሳት ሥዕላት በመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን የነበረውን ሁኔታ ለመግለጥ ምስክር ናቸው። ቮን ፍሪከን የተባለ በሮም ዋሻዎች (Roman Catacombs) ላይ ጥናት ያደረገ አጥኚ "አብዛኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትረካዎች እና የኢየሱስ ክርስቶስ ተአምራት በሮማን ካታኮም ላይ ተሰለው ይታያሉ" በማለት ይናገራል። የድንግል ማርያም ሕይወት፣ ቅዱስ ቁርባን የተመሠረተበት ሥርአት፣ የአልአዛር ከሞት መነሳት፣ በደብረ ታቦር የጌታ በክብር መታየት፣ የጌታችን ትንሣኤ እና ዳግም መምጣት በእነዚህ ዋሻዎች ውስጥ ተስለው ይታያሉ።

የሚገርመው በእነዚህ ዋሻዎች ውስጥ በተደረጉ አርኬሎጂያዊ ግኝቶች የብሉይ ኪዳን ክስተቶችን እና የነቢያትን ታሪክ የሚገልጡ ሥዕሎች ተገኝተዋል። በይስሐቅ ፋንታ የተሰዋው መሥዋዕት (The catacomb of Merellin) ፣ የሙሴ ሕይወት፣ የዐለት ላይ ውኋ መመንጨቱ (Catacomb of Kallister)፣ ነቢዩ ኤልያስ (Catacomb of Priscilla)፣ ነቢዩ ዮናስ (Catacomb of Kallistas) ፣ ነቢዩ ዳንኤል (The Catacomb of Krilta Luisi) የሚገልጡ ስዕሎች ተገኝተዋል። (በእንግሊዘኛ በቅንፍ ውስጥ የተቀመጡት የዋሻዎቹ ስም እንደሆነ ልብ ይሏል!)

ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያ አንድ ቅዱሳት ሥዕላትን የሚስል ሰው ሰማዕታትን እንዲስልለት ስለ መጠየቁ በስራዎቹ ውስጥ ተመዝግቦ ይገኛል። [4] ቅዱስ ጎርጎሪዮስ ዘኑሲስ (St. Gregory of Nyssa) ከይስሐቅ እና ከመሥዋዕቱ ጋር የተያያዘውን ሥዕል ይወደው የነበረ ሲሆን ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የቅዱስ ጳውሎስ መልእክታትን ከማጥናቱ በፊት የቅዱስ ጳውሎስ ሥዕል ነበረው። [5] እነዚህ ነገሮች ሥዕል በመጀመሪያዎቹ የቤተ ክርስቲያን ዘመን የነበረውን ቦታ የሚያስረዱ ናቸው። ከቆስጠንጢኖስ መንገሥ ጋር ተያይዞ የክርስትና ሃይማኖት በይፋ መሰበክ ሲጀመር ቅድሳት ሥዕላት ከዋሻ ወተው ቤተ መቅደስ ውስጥ መሳል ጀምረዋል።

ማጣቀሻዎች

[1] Hagios Book Series, The Icon and Its Theology p. 23-25

[2] Water Lowrie, Art in the Early Church p. 8

[3] Hagios Book Series, The Icon and Its Theology p. 31

[4] St Basil, Homily On the Martyrdom of Barlaam. Qouted in 'The Orthodox Ethis' p. 15

[5] Hagios Book Series, The Icon and Its Theology p. 23

ስብሐት ለእግዚአብሔር!
819 viewsedited  06:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-06 07:25:51 ✟#መንፈስ_ቅዱስ✞ ክፍል 1 አንድ አምላክ በሚሆን በአብ ፡ በወልድ ፡ በመንፈስ ቅዱስ ስም! በትምህተ ሥላሴ ክፍላችን ላይ እንዳየነው ከሶስቱ ቅዱስ አንዱ ቅዱስ ፤ ከሶስቱ አካል አንዱ አካል መንፈስ ቅዱስ ነው። በዚህ እና በሌሎች ጽሁፎች ስለ መንፈስ ቅዱስ ብቻ የምንመለከት ሲሆን መንፈስ ቅዱስ አካላዊ ወይስ ዝርው ኋይል?ስለመንፈስ ቅዱስ አምላክነት መፅሀፍ ምን ይላል?እና ስለ ጰራቅሊጦስ…
387 viewsedited  04:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ