Get Mystery Box with random crypto!

ፍቅርን በደብዳቤ @ fkrn bedebdabe

የቴሌግራም ቻናል አርማ fkrnbedebdabe — ፍቅርን በደብዳቤ @ fkrn bedebdabe
የቴሌግራም ቻናል አርማ fkrnbedebdabe — ፍቅርን በደብዳቤ @ fkrn bedebdabe
የሰርጥ አድራሻ: @fkrnbedebdabe
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 307
የሰርጥ መግለጫ

ፍቅር ያሸንፋል

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2021-09-27 23:28:22  በሳተላይቶች ዙርያ ማወቅ የሚገባዎ ሰባት አስደናቂ እውነታዎችን

በመሬት ዙርያ የሚሾሩ ሳተላይቶች ቁጥራቸው ስንት ይደርስ ይሆን? ደግሞስ እርስ በርስ እንዴት አይጋጩም? ደግሞስ እንዴት ወደ መሬት አይፈጠፈጡም?

ለመሆኑ ስንት ሳተላይቶች ሕዋ ላይ እንዳሉ ይታወቃል? ደግሞስ ማንም ተነስቶ ወደ ሕዋ ሊያመጥቃቸው ይችላል? ወይስ ፍቃድ ያሻል? ፍቃድ ካስፈለገ ፍቃድ ሰጪው ማን ነው? ሳተላይቶች እርስበርስ ሊላተሙ የሚችሉበት አጋጣሚስ ይኖር ይሆን?
ለመኾኑ በመሬት ምህዋር የሚዘዋወሩ ሰው ሰራሽ ሳተላይቶች ስንት ይሆናሉ ብለው ይገምታሉ? መቶ? ሺህ? 10ሺህ?

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአውተር ስፔስ ጉዳዮች ቢሮ UNOOSA እንደተገለጸው ዛሬ ላይ ወደ አምስት ሺህ የሚጠጉ ሳተላይቶች ይገኛሉ። ቁጥሩን በትክክል ለማስቀመጥ ያህል 4921 ሳተላይቶች ምድርን እየተሽከረከሩ ነው።
ነገር ግን ሁሉም በሥራ ላይ ናቸው ማለት አይደለም። ከሥራ ውጭ የሆኑት 2600 ሲሆኑ በሕዋ ላይ እነዚህን ሳተላይቶች ጨምሮ 17ሺህ የሚጠጉ የተለያዩ ሳተላይት ያልሆኑ መሣሪያዎች ይገኛሉ ይላል በደቡብ ካሊፎርኒያ ዩኒቨርስቲ የሕዋ ተመራማሪው ዴቪድ ባርን ሀት። እነዚህ ቁሳቁሶች በድምሩ 7600 ቶን ይመዝናሉ። ሁሉም የሚገኙት ታዲያ ከመሬት እስከ 35 ሺህ ኪሎሜትር ርቀት ላይ ነው።

1. የሳተላይቶቹ መጠን ምን ያህል ነው?

ሳተላይትን ስናስብ መጀመርያ ወደ አእምሯችን የሚመጣው እጅግ ግዙፍና እጅግ ከባድ ከሆኑ ቁሳቁሶች የተሠራ በጣም ትልቅ ቁስ ሊሆን ይችላል።
ነገር ግን ሁሉም ሳተላይቶች እንደዚያ አይደሉም። መጠናቸውም ቢሆን ይለያያል። ትንሽ የዳቦ ቅርጫት ከሚያክሉት አንስቶ የከተማ አውቶቡስ እስከሚያህሉት ድረስ አሉ። አንድ መለስተኛ የእግር ኳስ ሜዳ የሚያክሉ ሳተላይቶችም ይገኛሉ።

2. ሳተላይት አገልግሎቱ ምንድነው?

ሁሉም ሳተላይቶች ወደ ምድር አጎንብሰው የመሬት አካልን ፎቶ የሚያነሱ አይደሉም። ዘርፈ ብዙ አገልግሎትን ይሰጣሉ። የኮሚኒኬሽን ሥራ አንዱ ነው። የስልክ ግንኙነትን፣ የዳታ ስርጭትን የምናገኘው በሳተላይቶች አማካኝነት ነው።
የመሬት ቅኝትና ምልከታን (የጂፒኤስ ሥርዓትን ይጨምራል) የምናውቀው ሳተላይቶች ስላሉ ነው።
የሕዋ ጥናትን እንዲሁም የፕላኔት ጥናትን የሚያካሄዱ መልከ ብዙ ሳተላይቶችም ይገኛሉ።

ነገ አዲስ አበባ ይዘንብ ይሆን ወይስ ደመናማ ይሆናል ለማለት የሳተላይት ምስሎች ያስፈልጉናል። የባህር ወጀብን ሳይቀር ምስል አንስቶ የሚልከው ሳተላይት ነው።
የዓለማችን ሳንባ የሚባለው አማዞን ጫካ ውስጥ ምን ያህል ምንጣሮ እየተካሄደ እንደሆነ፣ ቻይና በረሃ ውስጥ አፈናና ግድያ የሚፈጸምበት ማጎርያ እየተገነባ ይሁን አይሁን ሳተላይቶች ፍንጭ ያቀብሉናል። በቤታችን ቁጭ ብለን የምንኮመኩማቸው የቴሌቪዥን ስርጭቶችና የራዲዮ ሞገዶች የሳተላይት እገዛን የሚሹ ሊሆኑ ይችላሉ።

3. እንዴት ነው ሳተላይት በምህዋሩ መቆየት የሚችለው?

ሳተላይቶች በምድር ዙርያ ሊሾሩ የሚችሉት የመሬት ስበትን ለመቋቋም በሚያስችል ፍጥነት ላይ እንዲሆኑ ስለተደረጉ ነው። አለበለዚያ ወደ መሬት ይወድቁ ነበር። ይህን ለመረዳት ትንሽ ውስብስብ ቢሆንም በቀላሉ አንድ መድፍ በከፍተኛ ጉልበት በ180 ዲግሪ ቢተኮስ መሬት ላይ ከመውደቁ በፊት በሆነ አቅጣጫ የተወሰኑ ርቀቶችን ይጓዛል። ወደ መሬት የመውደቅ ርቀቱ የሚወሰነው በሚኖረው የፍጥነት ጉልበት ነው። ሳተላይቶችም ለመሬት ስበት እጅ የማይሰጡበት ምክንያት ፍጥነታቸው ነው።

4. የሳተላይቶችን ዕድሜ ምን ያህል ነው?

ሮኬቶች ሳተላይትን ጭነው ወደ ሕዋ ያመጥቁና ለሳተላይቱ ከተሰናዳለት ቦታ ያኖሩታል። የተስተካከለ ርቀቱን እስኪያገኝ ወራትን ሊወስድ ይችላል። በመጨረሻም ሳተላይቱን በምህዋሩ ላይ ይቀመጣል። ሳተላይቱ ተሸክሞት ከሄደው ሮኬት ቀስ በቀስ በሚለያይበት ወቅት የሚኖረው ፍጥነት በመሬት ዙርያ ለመቶ ዓመት መሽከርከር ያስችለዋል ይላሉ ባለሞያዎች። ዋናው ሳተላይት በሕዋ ላይ እንዲቆይ የሚያደርገው ምስጢር የመሳሳብ ፊዚክስ ሲሆን በመሬት ስበት እንዳይወድቅ የሚያግደው ብቸኛው ጉዳይ የእሽክርክሪት ፍጥነቱ ነው።

ለዚያም ነው ከመሬት በቅርብ ርቀት የሚገኙት ሳተላይቶች የሚሾሩበት ፍጥነት ከመሬት ራቅ ብለው ከሚገኙት ይልቅ ፈጣን የሆነው። ሳተላይቶች የእሽክርክሪት ምህዋራቸውን መለወጥ ቢያስፈልግ እና እርስበርስም እንዳይጋጩ እንዲረዳ የየራሳቸውን ነዳጅ ተጭኖላቸዋል።
ሳተላይቶች ከ5 እስከ 15 ዓመታት አገልግሎት ላይ ሊቆዩ ይችላሉ። ዕድሜያቸው ግን በሚሰጡት አገልግሎትና በሚታጠቁት የነዳጅ መጠን ይለያያል።

5. ሳተላይቶች ሊጋጩ ይችላሉ?

ሊጋጩ ይችላሉ፤ ነገር ግን ሁልጊዜ የሚሆን ነገር አይደለም። ምክንያቱም የሚሾሩበት መስመር ከመለያየቱም ባሻገር ሕዋ እጅግ ሰፊ አካል መሆኑ ግጭት እንዳይኖር ያደርጋል። ይህ ማለት ግን ግጭት በፍጹም አይከሰትም ማለት አይደለም። በአሁኑ ጊዜ እጅግ በርካታ ሳተላይቶችን የማምጠቅ ዕቅድ መኖሩ ሲታይ ግጭት የመከሰቱ ዕድል ዜሮ ነው ማለት አይቻልም።

በየካቲት፣ 2009 አንድ የአሜሪካና አንድ የራሺያ ሳተላይቶች ተላትመው ያውቃሉ። ይህ በታሪክ የተመዘገበ የመጀመርያው የሳተላይቶች ግጭት ነው።

6. ሳተላይቶችን ማን ነው የሚቆጣጠራቸው?

ሳተላይቶች በድርጅቶች ወይም በኩባንያዎች ወይም በመንግሥት አንዳንድ ጊዜም በግለሰቦች ባለቤትነት ሊያዙ ይችላሉ። በ1967 በተደረገው የአውተር ስፔስ ስምምነት መሠረት እያንዳንዱ ሳተላይት ያመጠቀ አገር የተወሰነ የመቆጣጠር ሥልጣን እንዲኖረው የተደረገው የሬዲዮ ልውውጥ መጠላለፍን ለማስቀረት ጭምር ነው።

በአሜሪካ ለምሳሌ የግል ኩባንያዎች በስፔስ አገልግሎት ላይ ለመሰማራት መጀመርያ ከፌዴራል መንግሥት ፍቃድ ማግኘት ይኖርባቸዋል።
ለኮሚኒኬሽንና ቴሌኮም ሳተላይት ግንኙነት ለማድረግ ከፌዴራል ኮሚኒኬሽን ኮሚሽን ፍቃድ መውሰድ ግድ ነው። ሳተላይትን ወደ ሕዋ ለማምጠቅ ደግሞ የፌዴራል አቪየሽን አስተዳደርን ፍቃድ ማግኘት ያሻል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ የተባበሩት መነግሥታት ድርጅት የአውተር ስፔስ ጉዳዮች በእንግሊዝኛ ምህጻሩ UNOOSA የሚባለው ኃላፊ መሥሪያ ቤት ነው። በሕዋ ጉዳዮች ዙርያ ሕግ ያረቃል ይቆጣጠራል።

7. ማንም ሳተላይት ወደ ሕዋ ማምጠቅ ይችላል?

አዎ! ዛሬ ማንኛውም ሰው ሳተላይትን ወደ ሕዋ ማምጠቅ የሚችለበት ደረጃ ተደርሷል። የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ሳይቀሩ ሳተላይት ገንብተው በማምጠቅ ፕሮግራማቸውን ከሌሎች መንግሥታዊ ተቋማት ጋር ይጋራሉ።
ከመቼውም ጊዜ በላይ የንግድ ኩባንያዎች ሳተላይት የሚያመጥቁበት ጊዜ ላይ እንገኛለን። ኾኖም ከፍ ያለ በጀት የሚጠይቅ ጉዳይ ነው። ይህ የሳተላይት ኢንዱስትሪም በቢሊዮን ዶላር ይገመታል።

አስተያየት ካልዎት በ ፍኖተ፥አእምሮ ያድርሱን !!!
@fkrn bedebdabe
469 viewsĶåš ŧęĸłů, 20:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-27 23:19:56 #ሄፕኖሲስ (አፍዝ አደንግዝ)
ሄፕኖሲስ ይባላል ሰዎችን የማደንዘዝ ጥበብ።ይህ ጥንቆላ ወይም ድግምት
አይደለም…በሳይንስ የተረጋገጠ ነገር እንጂ። ሄፕኖሲስ አድራጊው ሰው
በሰዎች ህቡዕ ህሊና ውስጥ ሃሳብን ይቀብራል። እነዚህ ሰዎች አንዴ ሄፕኖታይዝ ከተደረጉ በኋላ እርሱ (ሄፕኖታይዝ አድራጊው) የነገራቸውን ሁሉ ያምናሉ።ይህ የሚነድ ከሰል ነው ብሎ በረዶ በእጃቸው ላይ ቢያደርግ፤ አቃጠለን ብለው ይጮሃሉ።በረዶ የሚያቃጥላቸው በአእምሯቸው ላይ ብቻ አይደለም፤ የምርም ልክ ከሰል እንደጠበሰው ሆኖ እጃቸው ላይ የቃጠሎ ጠባሳ ይቀራል።

#ይህ_እንዴት_ይሆናል ?
ሄፕኖሲስ መሰረቱን ያደረገው Suggestion (ቅድመ ነገራ) ላይ ነው። ለምሳሌ ሙዚቃን ስታዳምጥ በሃሳብ ወደሌላ ቦታ ተጉዘህ አታውቅም? ወደ ልጅነትህ ተመልሰህ…የኩበት ሽታ፣ የአበቦች መዓዛ፣ የሰዎች ጫጫታን ሁሉ በአንድ ሙዚቃ ምክንያት ታስታውሳቸዋለህ።ይህ ሙዚቃም አንተን ሄፕኖታይዝ አድርጎ ወደ ሌላ አለም ይወስድሃል።በተመሳሳይም ሄፕኖሲስ አድራጊውም ቃላትን ለህቡዕ ህሊናህ ይነግረዋል።ለምሳሌ ከዚህች ደቂቃ ጀምሮ ስምህን አታስታውስውም ካለህ…ስምህን ትረሳዋልለውህ። እግርህን ማንቀሳቀስ አትችልም ካለህ… እግሮችህ ከመሬት ጋር ይጣበቃሉ የእርሱ ቃላት የአንተን አእምሮ ይቆጣጠሩታል።

ይህ እንዲሆን ግን አንድ ቅድመ ሁኔታ ያስፈልጋል…ይህም አእምሮህ አሁን
ካለበት የአልፋ ሁነት…ወደ ስክነት (ቴታ ሁነት) መግባት ይኖርበታል።
እንዴት ወደ ቴታ ሁነት መግባት ይቻላል? እንዴትስ ራሳችንን ሄፕኖታይዝ አድርገን
የሚደንቅ ለውጥን በህወታችን ላይ ማምጣት እንችላለን? #ተአምረኛው_አእምሮህ መጽሐፍ ራሳችንን ሄፕኖታይዝ አድርገን በህይወታችን ለውጥ የምናመጣበትን ጥበብ ያስተምረናል።
ምንጭ፦Book Land

@fkrnbedebdabe
415 viewsĶåš ŧęĸłů, 20:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-26 13:13:42 ሰው እንዴት ያለ አምላኩ መገኘት በሰላም ሊኖር ይችላል? ፈጣሪ የሌለበት ህይወትስ እንዴት ስኬት ይባላል?
-
አምላክን የምትፈልጊው ፃድቅ ስለሆንሽ አይደለም::
-
አምላክን የምትፈልጊው ፃዲቅ ለመሆን ነው::
-
እያንዳንዱ ፃዲቅ አምላኩ ይቅር ያለለት የትላንት ሀጥያት አለው::
-
እያንዳንዱ ሀጥያተኛም በንስሃ ፃዲቅ የሚሆንበት ነገ አለው::
-
ከሀጥያት ሁሉ የከፋው ሀጥያት አምላክን መርሳት እና ከእርሱ ጋር ያለን የአባት እና የልጅ ግንኙነትን ማቋረጥ ነው::
-

ሰው እንዴት ያለ አምላኩ መገኘት በሰላም ሊኖር ይችላል? ፈጣሪ የሌለበት ህይወትስ እንዴት ስኬት ይባላል?

-
ሀጥያትሽ ዝሙትሽ ወይም ስርቆትሽ ወይም በአለም በኩል ደስታን መፈለግሽ ወይም ህግ መተላለፍሽ አይደለም::
-
ሀጥያትሽ የህይወት ምንጭ እና በረከት የሆነውን አምላክን መርሳትሽ ነው::
-
እስቲ በራቅሽው ሰዓት የተሰማሽን ፍርሃት: ራስን መጥላት: ጭንቀት: ከንቱነትና ድብርት አስቢው::
-
ለምን የአለማችን ከንቱ ፍጥረት አድርገሽ ራስሽን የምትመለከቺ ይመስልሻል? የአለም እፁብ ድንቅ ፍጥረት አድርጎ የፈጠረሽ አምላክን ስለዘነጋሽው አይደል?
-
አምላክሽ ግን አሁንም ሆነ መቼም በአንቺ ተስፋ አይቆርጥም::እርሱ እንደሰው አይደለምና ያደረግሽውን አይቶ አይቀየምም::ሁልጊዜ በፍቅር ሊያኖርሽ እደጅሽ ላይ ቆሞ እያንኳኳ ነው::
-
እባክሽን እደጅ አታስጠኚው::ቆሻሻ ሀሳብ : ስሜትና ምግባርሽን አራግፊው::እርሱ ወደ ልብሽ ንፁህ አዳራሽ ይግባ::ባንቺ የልብ መንፃት ሀሴትን ያድርግ::በመልካምነትሽ ይደሰት::አብሮሽም እንዲሰራ ፈቀጅለት::ያንቺ እና የአምላክ ጥምረት ያንቺን ትንሺዬ ችግር ይቅርና የአለምን ሁሉ ግድፈት ያቀናል::
-
እርሱ ካንቺ ጋር ሊሰራ ሁሌም ዝግጁ ነው....አንቺስ??

#መልካም ቀን

@fkrnbedebdabe
403 viewsĶåš ŧęĸłů, 10:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-24 15:55:57 ከጠጠሮች ተርታ ወጠህ ከአልማዞች ጎራ መሰለፍ ትሻለህ?
እንግዲያስ የሚያጠነክር ፈተናን እና መከራ ስጠኝ ይሁን ፆለትህ.....

አልማዝ በተፈጥሮ መንገድ እንዴት እንደሚሰራ ልንገራችሁ። አልማዝ የሚሰራው HPHT በሚባል Process ነው። HPHT ማለት High Pressure High Temperature ማለት ነው። አንድ አልማዝ አልማዝ ከመሆኑ በፊት አራት ደራጃዎችን ማለፍ ይኖርበታል። አንደኛ ከምድር በታች ከ300 እስከ 600 ኪሎ ሜትር ዝቅ ብሎ መቀመጥ። ሁለተኛ ከፍተኛ ሙቀት መታደል፣ ከ1200 ዲግሪ ሴንቲ ግሬት ቃጠሎ ውስጥ መቀመጥ። ሶስተኛ ከፍተኛ ጭነት ማግኘት። አራተኛ ለረዥም ጊዜ ውስጥ በነዚህ ሁኔታ ውስጥ መቆየት ! እንግዲህ አንድን የድንጋይ ከሰል ወስዳችሁ ከምድር በታች 600 ኪሎ ሜትር ብታወርዱት፣ 1200 ዲግሬ ስንቲ ግሬት ቃጦሎ ውስጥ ብታኖሩት፣ በከፍተኛ ፕሬዠር ውስጥ ብታስቀምጡት እና ለረዥም ጊዚያት በዚህ ሁኔታ ውስጥ ብትተዉት። ከሱሉ አልማዝ ይሆናል ! ከሰሉ ወደ ዳይመንድ ይለወጣል።

አንዳንዶቻችሁ በህይወታችሁ ግራ ይገባችኋል፣ በጣም የሚወዳችሁ አምላካችሁ ከጓደኞቻችሁ በታች 600 ኪሎ ሜትር አውርዷችሁ ይሆናል። በማይገባችሁ ፈተና 1200 degree cent great ቃጠሎ ውስጥ አስቀምጧችሁ ፤ በማጣት፣ በመገለል፣ በመገፋት ለረዥም ጊዚያት እየፈተናችሁ "ምንድነው እየተካሄደ ያለው" ብላችሁ እስክትጠይቁ ድረስ ለአምስት አመት፣ ለአስር አመት ከሰው፣ ከወዳጅ፣ ከዘመድ፣ ከጓደኛ ዝቅ አድርጓችሁ ይሆናል። ....

"ምን ማለት ነው የሚወደኝ አምላክ ይሄን የሚፈቅደው" ስትሉ .... አልማዝ አድርጎ ሊሰራችሁ፣ ውብ አድርጎ፣ ሊሰራችሁ፣ የምታበሩ አድርጎ ሊያበጃችሁ፣ እንቁ፣ ዳይመንድ፣ አልማዝ ሊያደርጋችሁ ስላሰበ ነው !

አልማዝ ሰባት ባህሪዎች አሉት። አንደኛ ጠንካራ ነው። ወስዳችሁ በድንጋይ ቀጥቅጡት አይሰበርም። በሰይፍ ምቱት አይሰነጠቅም። በመጋዝ ገዝግዙት አይቆረጥም። በአልመዝ ግን ብረት ይቆረጣል፣ በአልማዝ ግን ሰይፍ ይቆረጣል። በአልማዝ ግን ድንጋይ ይፈርሳል። አልማዝ የሚቆረጠው በሌላ አልማዝ ነው። ሁለተኛ የአልማዝ ባህሪ ልንገራችሁ። ከፍተኛ የማንጸባረቅ ባህሪ አለው። refractive index ይባላል። የተቀበለውን ብርሃን መልሶ የማብራት ባህሪ አለው። ያንጸባርቃል። ሶስተኛው የአልማዝ ባህሪ የተቀበለውን የጸሐይ ብርሃን፣ ነጩን ብርሃን ወደ ተለያዩ በርካታ ቀለማት የመበተን ችሎታ አለው። አራተኛ የአልማዝ ባህሪ ልንገራችሁ። እጅግ በጣም ንጹህ ነው። አልማዝ የሚታወቀው በነጹህነቱ ነው። አምስተኛ የአልማዝ ባህሪ ልንገራችሁ። አልማዝ በእሳት አይቃጠልም። አንድ ቤት ውስጥ አልማዝ አለ እንበል ያ አልማዝ ያለበት ቤት ሙሉ ለሙሉ ቢቃጠል አልማዙ ምንም አይሆንም። ምንም። በነበረው ቅርጹ፣ በነበረው ንጽህናው እናገኘዋለን። የሚያስገርመኝን ስድስተኛውን የአልማዝን ባህሪ ልንገራችሁ። ወርቅ ላይ አሲድ ድፉበት ወርቁ ይበላሻል። አልማዝ ላይ አሲድ አፍስሱበት ምንም አይሆንም። አይበላሽም። የመጨረሻው እና ሰባተኛው የአልማዝ ባህሪ በጣም ውድ ነው። በጣም ውድ ነው። የአውራጣትህን ራስ የምታክል ዳይመንድ አንድ ትልቅ ፎቅ ይገዛል። በጣም ውድ ነው።

ከጓደኞቻችሁ በታች 600 ኪሎ ሜትር ወርዳችሁ ፣ በ1200 ዲግሪ ሴንቲ ግሬት ስቃይ ውስጥ ያለፋችሁ፣ በፕሬዠር ውስጥ ለበርካታ አመታት ያለፋችሁ እናንተ አልማዝ ሁናችሁ የተሰራችሁ ሰዎች ናችሁ። ሰዎች ጠጠር ብትመስሏቸውም አልማዞች ናችሁ። ዋጋችሁ በጣም ውድ ነው። ... ከተማሩ ሰዎች ይልቅ፣ ብዙ ድግሪ ከተሳካላቸው ሰዎች ይልቅ፤ በመከራ ያለፉ ሰዎችን አከብራለሁ። ዋጋ የከፈሉ ሰዎችን አከብራለሁ። በስቃይ ውስጥ ያለፉ ሰዎችን አከብራለሁ። ምክንያቱም ዋጋቸው በጣም ውድ ነው።

...........ዶ/ር ወዳጄነህ..........
@fkrnbedebdabe
392 viewsĶåš ŧęĸłů, 12:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-22 12:19:12 " ◈ ያለምክንያት ከሄድክ በምክንያት አትምጣ"◈

በህይወት ሰልፍ ውስጥ ሳለህ ልብ ልትላቸው የሚገቡ
እነኚህን 10 ነጥቦች በአጽንኦት አንብባቸው

➊."ያለፈ ነገር እንደማይቀየር አትርሳ!" ላወቀበት ሰው ግን
ያለፈው ለወደፊቱ የራሱ የሆነ ትምህርት አለው፤ ካለፈው ነገርህ ተማር እንጅ በፍፁም አታማርር፤
ማማረር ነገህን በጎ አያደርገውም።

➋.የሰዎች ሃሳብ የአንተን ማንነት አይገልፅም! ማንነትህ አንተ ውስጥ ነው ያለው፤ መልካም አድርግ ሌላውን እርሳው የሁሉም ሰው የህይወት መንገድ (ጉዞ) ይለያያል፤ ለሁሉም ጊዜ አለውና ጊዜው በደረሰ ሰው ሁኔታ አትቅና።

➌.መኪና ገዛ ብለህ "እኔስ" አትበል! ጊዜህ ሲደርስ መኪናዎች ወይም ‘አውሮፕላን’ ትገዛለህ ፣ ያውም ለመኖር አስፈላጊ ከሆነ ደግሞስ እንዴት እንደገዛው የት ታውቃለህ? እርሱን ተወውና በራስህ ላይ አተኩር ፣ ያለህ ነገር በቂ ነው።

➍."ለሰዎች ለደስታቸው እንጂ ለሀዘናቸው መንስዔ አትሁን!"
►በሰዎች ደስታ→ደስ ይበልህ!
►ለሰዎች→ክፉ አትመኝ፣
►በሃዘናቸውም→አብረህ እዘን፣
►ሰዎች ሲያዝኑ→አትደሰት፣
►ሰው ከሆንክ→የሰው ነገር ይሰማህ፣ ይህ ማለት ግን ተንኮል
እየሰሩ ከሚደሰቱ ሰዎች ጋር ተደሰት ማለት አይደለም።
ሰው እያስከፋ ብሎም እየገደለ የሚደሰት አለ ፣ አንተ ከተጎዳው
ሰው ጋ ሁን፣ አስተውል።
➎."በጊዜ ስራ እንጂ ጊዜ ባንተ ላይ አይስራ!" ጊዜ
የማይፈውሰውና የማይቀይረው ነገር የለም። አንተንም ጊዜው
ይቀይርህ ዘንድ ፍቀድለት፤
በተሰጠህ ጊዜ ለመልካም ነገር ሱሰኛ ሁን።
➏. "መክሊትህን ፈልግ!"
ውስጥህ የሚችለውና የሚያምንበት ተሰጥኦ ምን አለህ? ምን
አይነት ስራ መስራት ትችላለህ? አስተውል ጓደኛህን አትመልከት
፣ ትለያያላችሁና። አለማችን በትምህርት ብቻ ወይም በጥበባት
ብቻ ወይም በተወሰኑ ዘርፎች አይደለም እየኖረች ያለችው።
በጣም ብዙ ነገሮች ናቸው እየደገፏት ያቆሟት። አንተም
ጥቂትም ብትሆን ያለህን ችሎታ ፈልገውና አውጣው። ቁፋሮ
ነው ወይስ ቾክ ይዞ ማስተማር ነው ወይስ መምከር መገሰፅ
ነው? ቆንጆ ሽሮ ወጥ እየሰሩ መሸጥ ነው? ድንጋይ ቅርፅ
(ኮብልስቶን) እየሰሩ መኖር ነው? ምንድነው? እባክህ ፈልገው
አጎልብተው ጀምረው፣ "ምን ይሻለኛል?" እያልክ ጊዜህ
እንዳያልቅ። በእርግጥ ጊዜህ ሳይሆን አንተ ነህ የምታልቀው።
➐. "መልካም ነገር ሁሉ ከፈጣሪ መጥፎ ነገር ሁሉ ደግሞ
ከሰይጣን እንዳልሆነ አስተውል!" ፈጣሪ መጥፎን ወደ መልካም
የመቀየር ብቃት አለው። ሰይጣንም ያጠፋህ ዘንድ መልካም
የሚመስል ነገር ሊያዘጋጅልህ ይችላል። መልካም ማሰብና
መልካም መሆን መልካም ነገር እንዲገጥምህ ማመቻቸት ነው፤
መጥፎነት ከአንተ ይራቅ፤ ለአንተም ሆነ ለሰዎች ጉዳት እንጅ
ጥቅም የለውም።
➑. "ሰው የዘራውን ያጭዳል" የሚለውን አባባል አስታውስ፤
የሰራኸውና የምትሰራው ነገር የሆነ ጊዜ ላይ ዞሮ ያገኝሃል፤
መጥፎ ከሰራህ እንደስራህ፤ መልካም ከሰራህም እንደዚያው
ይገጥምሃል። ክፉ ነገር እየዘራህ መልካም ነገር አትጠብቅ፤
ራስህን አትሸውድ። ጤፍ ዘርተህ ባቄላ አትጠብቅ፤ ጤፍ የዘራ
ገበሬ ጤፍ እንደሚያጭድ ሁሉ አንተም የዘራኸውን በእጥፍ
ታጭዳለህ።
➒. "ለራስህ ስትል መልካም ሁን፣ በጎውንም አስብ!" ለራስ
ማሰብ ማስተዋል እንጅ ራስ ወዳድነት አይደለም። ራሱን
የማይወድ ሰው ሌላውን አይወድም።
➓. "በማንም ላይ አትፍረድ!"
ፍርድ የፈጣሪ ነው። ፍጥረት ሁሉ እንከን አለበት። የተሻለ ሀሳብ
አለኝ ብለህ ካሰብክና ከቻልክ ምከር ካልሆነ ዝም በል።
*ለውጥ ከራስ ይጀመራል! እናም አሁኑኑ መለወጥ ጀምር።
መልካም ቀን ይሁንልን!! አሜን
@fkrnbedebdabe
424 viewsĶåš ŧęĸłů, 09:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-12 13:01:52 ካለፈው ህይወትህ ተማር ፣ ዛሬን በሚገባ እንደዛሬ ብቻ ኑር ፣ ዛሬ የኖርከው ለነገህ መንገድህ ነውና አቅድ ፡፡ ከትናንት ስንማር ፣ ዛሬን በሚገባ ስንኖር ፣ ለነገ ብዙ አናቅድ የህልም ሰዎች ስንሆን በህይወታችን ብዙ ነገር ይመጣሉ ፡፡ በተለይ የተፈጠርንበትን ዓላማ ተገንዝበን ወደ #ዓላማ ህይወት ስንገባ ፣ ገብተንም ራዕይ ስንሰንቅ በህይወታችን ብዙ ትችትና ዘለፋ ይደርስብናል ፡፡ እሄ ትችት ደግሞ የሚመጣው ዓላማ ከሌላቸውና ራዕይ ካልሰነቁ በመኖር ውስጥ ሳይሆን ባለመኖር ውስጥ ባሉ የነገን ከማያውቁ ሰዎች ነው
ሰላም ፍቅር አንድነት
እግዚአብሔር ይስጠን ሀገራችንን ሰላም ያድርግልኝ
@fkrnbedebdabe
406 viewsĶåš ŧęĸłů, 10:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-11 20:48:20
410 viewsĶåš ŧęĸłů, 17:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-07 07:12:38 የውሳኔ ስሌት!

አንድን ውሳኔ በመወሰንና ባለመወሰን መካከል ስትዋዥቁ በአእምሯችሁ ብቅ ጥልቅ የሚሉ ሁለት ሃሳቦች አሉ፡፡ በአንድ በኩል ውሳኔው ትክክል ቢሆን የምታገኙት ጥቅም ሲሆን፣ በሌላ ጎኑ ግን ውሳኔው ስህተት ቢሆን የሚያስከትለው ችግር ነው፡፡ በተለይ እንድትወላውሉ የሚያደርጋችሁ ስሜት ሊያጋጥማችሁ የሚችለውን ችግር ስታስቡ መሆኑ ጥርጥር የለውም፡፡ ከአንዳንድ ውሳኔዎች በኋላ ምንም ጥቅም ባናገኝም እንኳን ሊደርስብን ከሚችል ችግርና ክስረት ተጠብቀን በዜሮ መገላገል የሚመረጥበት ጊዜ እንዳለ ሁላችንም እናውቀዋለን፡፡

ውሳኔያችሁን ከምታገኙት ጥቅም ብቻ አንጻር ማሰብ በአጓጉል ጉጉት እንድትንደረደሩ ያደርጋችሁና ከሚዛናዊነት ሊጋርዳችሁ ስለሚችል ጥቅማችሁን በሚገባ ካሰላችሁ በኋላ ውሳኔያችሁን ለመገምገም መነሳት ያለባችሁ ሊያስከትል ከሚችለው ችግር ወይም መዘዝ ቢሆን ይመረጣል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ለመወሰን የሚረዷችሁን ሶስት ወሳኝ ነጥቦች አስፍሬላችኋለሁ፡-

1. የምትወስኑት ውሳኔ ትክክል ካልሆነ የሚያደርስባቸችሁ ጉዳት ከምክንያታዊነትና ከተጨባጭ ሁኔታ አንጻር እውን ከሆነ …

2. የሚደርስባችሁ ጉዳት ከአካል ጤንነት፣ ከስነ-ልቦና ቀውስ፣ ከከባድ የገንዘብ ክስረትና ከመሳሰሉት ከባባድ ሁኔታዎች ጋር የሚገናኝ ከሆነ …

3. በተሳሳተው ውሳያኔችሁ ምክንያት ከሚደረስባቸሁ ችግርና መዘዝ ለመውጣት ቢያንስ አንድ አመትና ከዚያ በላይ የሚፈጅባችሁ ከሆነና ከአመታት መባከንና ከእድሜ መበላት ጋር የሚገናኝ ከሆነ፡፡

ካለይ በተዘነዘሩትን የስሌት ሃሳቦች አንጻር ውሳኔያችሁ ተመዝኖ ሚዛን ካልደፋ ስለውሳኔያችሁ በሚገባ እንድታስቡበትና ብትችሉ ከእናንተ ከቀደቡ ብሱል ሰዎች ምክርን እንድትቀበሉ ልምከራችሁ፡፡

@fkrnbedebdabe
441 viewsĶåš ŧęĸłů, 04:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-31 07:10:35 አደገኛው ስብእና /Narcissism/

እነዚህ አይነት ሰዎች:-

ሁልጊዜ ጥፋተኛ እንደሆናችሁ (እንድታስቡ) ያደርጋሉ። ለሚሰጧችሁ መጥፎ ምላሽም ተጠያቂው እናንተ መሆናችሁን ይናገራሉ።

የእነሱን ችግር እንጂ፤ ፈፅሞ የእናንተን ማዳመጥ እና መረዳት አይፈልጉም።

ለጥፋታቸው ሀላፊነት መውሰድ አይፈልጉም። ሁልጊዜ ትክክል ነኝ ብለው ስለሚያስቡ፤ ለተፈጠረው ችግር ሁሉ ምክንያቱ እናንተ እንደሆናችሁ እንዲሰማችሁ ያደርጋሉ።

ጉራቸው ከልክ ያለፈ። ታላቅነታቸውን፣ ችሎታቸውን፣ ተፈላጊነታቸውን እና የበላይነታቸውን ሁሌ የሚናገሩትን።
ከእናንተ የወሰዱትን ሀሳብ ጭምር የራሳቸው አድርገው የሚነግሯችሁን።

የሰውን ትኩረት ለመሳብ የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም። በእያንዳንዱ ንግግራቸው እኔ....እኔ....እኔ የሚሉትን።

ለሌላ ሰው ችሎታ እውቅና የማይሰጡና የሚቀብሩትን።

ሌሎችን በጣም የሚያሳንሱ። የእነሱ ትልቅነት የሚጎላው የሌላውን ውድቀት፣ድክመትና አለመሳካት ሲያወሩ የሚመስላቸውን።

ፈፅሞ አክብሮት የላቸውም። ተሳስቻለሁ....ይቅርታ የሚባል ነገር አይታሰብም። ለጥፋታቸው ሌላውን ተጠያቂ በማድረግ የሚያሸማቅቁትን።

እነሱ የሚፈልጉትን ሀሳብ እንድትቀበሉና በነሱ ቁጥጥር ስር እንድትሆኑ የሚያደርጉትን።

ምንም አይነት ፍቅርና ርህራሄ የሌላቸውን።

ክፋታቸውን ነቅታችሁ ስትርቋቸው ስማችሁን የሚያጠፉ። ሚስጥርና ድክመታችሁን ለሰው የሚያወሩተን። በሚችሉት ሁሉ ሊጎዷችሁ የሚሞክሩትን።

ይህንን ካነበቡ በኋላ ግንኙነቶችዎን ደግመው ይመርምሩ

ለሌሎችም ያጋሩ
@fkrnbedebdabe
446 viewsĶåš ŧęĸłů, 04:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-28 16:20:10 ጎባጣው ትዳሬ

በየሳምንቱ ቅዳሜ አንድ መርህ አለኝ ፤ ያገርቤትም ሆነ የውጭ አገር ፖለቲካ ዜና እጦማለሁ፤ ኪነጥበብና ማህበራዊ ጉዳይ ላይ እጣድና ነፍሴን አለመልማታለሁ፤ በዚህ መሰረት ፥ ቅድም ዩቲዩብ ላይ ስርመሰመስ ቆየሁ ::

በቀደም አንድ የሞሮኮ ዜጋ የሆነ ዘፋኝ “ ሊጋባው በየነ” የሚለውን ዘፈን በራሱ ቃና ዘፍኖ አስደምሞኝ ነበር ፤ ዛሬ ደግሞ ሸገር ውስጥ በስደተኝነት የሚኖር ሶርያዊ ዘፋኝ “ ለዚህ ለዚህማ ምናለኝ አገሬ “ የሚለውን የጌቴ አንላይን ዘፈን ዘፍኖ አስለቀሰኝ ::

ወደ ፌስቡክ ተመለስኩ፤ ባለፈው አንዱ “ ላጤ” የሚለውን ግሩፕ እንድቀላቀል መጥርያ ልኮልኝ ነበር ፤ ያለሁበትን ተጨባጭ ሁኔታ ለመሰለል ፈልጎ ይመስለኛል፤ እኔም ግሩፑን ቀስ ብየ በለሆሳስ እየተራመድኩ ሰለልኩት፤ ፍቅር የተራቡ ” ሆርኒ” ወጣቶች የተደራጁበት ቡድን መሆኑን ደረስኩበት፤ ብዙም ሳይቆይ አንዲት ወይዘሮ ‘ በትዳራችን ጉዳይ እንመካከር “ የሚል ግሩፕ ላይ እንድሳተፍ መጥርያ ሰደደችልኝ ፤ ይሄ ግሩፕ የመጨረሻ ተመቸኝ፤የመጀመርያም ተመቸኝ :: አብዛኞቹ የግሩፑ አባላት ፥ የፍቅር ታሪካቸውን ተርከው ፤ በትዳራቸው ላይ የገጠማቸውን ችግር ዘርዝረው፥ ካንባቢ ምክርና መፍትሄ ያማትራሉ፤ እንሆ እኔም ተሞክሮየን ለማካፈል ወሰንኩ ፥

በውቄ እባላለሁ፤ ከባለቤቴ ጋራ የተገናኘነው ባጋጣሚ ነው፤ በጊዜው እሷ ሚስ ኢትዯጵያ ተብላ በቁንጅና ስትመረጥ እኔ አወዳደሪው ነበርኩ:: የመጀመርያዎቹ ሀያ አመታት የትዳር ቆይታችን ጎረቤት የሚያስቀና ነበር :: ከቢሮ ስመጣ በደስታ በፈገግታና በውዝዋዜ ትቀበለኛለች፤ ኮቴን አውልቃ ወደላውንደሪው አፍ እየጨመረች “ ምሳ እስኪደርስ ፤ ክትፎ በቆጮ እየቀማመስክ ቆይ “ ትለኛለች:: ከምሳ በሁዋላ ሶፋው ሳፋ እሲከመስል ድረስ ፍቅር እንሰራለን፤

በዙም ሳይቆይ ጸነሰች ፤ ከዘጠኝ ወራት ላልበለጠ ጊዜ በርግዝና ቆየች :: ያለ ብዙ ምጥ ወንድ ልጅ ተገላገለች፤ ልጃችንም ያለ ብዙ ለቅሶ ተገረዘ ! ልጃቸን በተወለደ በአንድ አመቱ ዶንኪቲዩብ ላይ እየቀረበ ለኢትዮጵያ ህዝብ ጠቃሚ ምክር መለገስ እና አቅጣጫ ማስቀመጥ ጀመረ:: ሰባት አመት ሲሞላው ካሮጌ ቅጥቅጥ ሚኒባስ ሂሊኮፍተር ሰራ :: አሁን ካዲስ አበባ ብሾፍቱ ራይድ እየሰራበት ይገኛል ::

ከጥቂት ጊዜ በሁዋላ ባለቤቱ ጸባይ መቀየር ጀመረ:: የገቢ ምንጯና ለኔ ያላት ፍቅር በፍጥነት እየጨመረ ሄደ፤ ለልደቴ ፍልውሃ ያለውን ፓርክ ገዝታ በስጦታ አበረከተችልኝ ::

በዚህ አይነት ሁሉን የሚያስቀና ትዳር ውስጥ እየኖርን እጅግ የሚያሳዝን ነገር ተከሰተ፤ ሄቲ ውስጥ የመሬት መንቀጥቀጥ ደረሰ ! ታሊባን አፍጋኒስታን መልሶ ተቆጣጠረ፤ ይህ ግን በፍቅራችን ላይ የፈጠረው አሉታዊ ተጽኖ አልነበረውም ::

አንባቢ ሆይ !! ትዳራችን ፈረሰ የሚለውን ለመስማት፥ ምክርና ከንፈር መጠጣ ለማዋጣት ሰፍ ብለህ እየጠበቅህ ነውን ? በቃ ሼም የለህም? ለምን የሟርተኞችና የክፉ ታሪክ ናፋቂዎች ግሩፕ አታቋቁምም ?
በዕውቀቱ ስዩም
@fkrnbedebdabe
424 viewsĶåš ŧęĸłů, edited  13:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ