Get Mystery Box with random crypto!

ፍቅርን በደብዳቤ @ fkrn bedebdabe

የቴሌግራም ቻናል አርማ fkrnbedebdabe — ፍቅርን በደብዳቤ @ fkrn bedebdabe
የቴሌግራም ቻናል አርማ fkrnbedebdabe — ፍቅርን በደብዳቤ @ fkrn bedebdabe
የሰርጥ አድራሻ: @fkrnbedebdabe
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 307
የሰርጥ መግለጫ

ፍቅር ያሸንፋል

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-04 09:21:57
ከሌላ ሰው መጽሐፍ የተቀነጨበ

ከህመሞች ትልቁ ህመም ካንሰር ወይም ኤድስ ሊመስለን ይችላል። እውነቱ ግን እንደ ስብእና መዛባት የከፋ ህመም የለም። ውጫዊ መልክ የሰው የገጽ ሽፉን ነው።

ስብእና ግን የሰው እውነተኛ መልክ ነው።
በየእለቱ አብረን የምንኖረው ሰው እውነተኛና የማያረጅ ዘላቂ ማንነታችን ስብእናችን ነው።

በአይናችን የማናየው እውነተኛ መልካችን
በውስጥ ማንነታችን ውስጥ ተቀብሮ ያለው ስብእናችን ነው። የስብእና ስንኩልነት ፣ ጠባሳዎችና መዛባቶች ቤት ያፈርሳሉ፤ አገር ይንዳሉ፤ ግንኙነትን ይመርዛሉ። ለማከምና ለማዳን ብቻ ሳይሆን ለማየትና ሕመሙን ለመረዳትም አዳጋች ነው።

ስብእና በልጅነት እንደ ተቦካ ሲሚንቶ ፣ በአዋቂነት ደግሞ እንደ ደረቀ አርማታ ነው።
የብዙ ሰው ስብእና እንደ ተቦካ ሲሚንቶ በልጅነቱ በትክክል የሚቀርጸው ካላገኘ ተንሻፎና ተዛብቶ ያድጋል። እድሜው ከገፋ በኋላ ደርቆ ስለሚጠነክር ፣ ብዙ ጊዜ ለምክራ መዶሻና ለምክር መጥረቢያ አዳግቶ አገር ያጠፉል።

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@fkrnbedebdabe
56 viewsĶåš ŧęĸłů, 06:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-20 20:52:58 እስቲ ስንመኝ የቱን ያህል መመኘት እንችላለን ???
ከመሆን በፊት ለመሆን ያሰቡት ይቀድማል ብዬ ነው ። ብዙዎቻችን ጥሩ ሰው ስናይ ምነው ያን ሰው በሆንኩ ብለን እንመኛለን ። ለምሳሌ አባትዋን በጣም የምትወድ ልጅ እንደ አባቷ አይነት ባል እንዲሰጣት ፈጣሪዋን ትለምናለች እናቱን የሚወድ እንደ እናቱ አይነት ሚስት እንዲሰጠው ፈጣሪውን ይለምናል ግና ይሄ ልክ ይሆን ???
" የቱንም ያህል አባትሽን ብትወጂ እንደ አባትሽ አይነት ባል እንዲሰጥሽ አጠይቂው አባትሽን በአባትነት ወደር የሌለው ሊሆን ይችላል በባልነት ግን ልታውቂ አትችዪም ምናልባት ለሚስቱ ብቁ ላይሆን ይችላል ። አንተም ወዳጄ እናትህን ውደዳት እንጂ እንደ እናትህ ሚስት አትመኝ እናትነቷ ላንተ ነው በሚስትነቷ የምትወድቃቸው ፈተናዎች ይኖራሉ ። የምንወዳቸውን ሰዎች ከመሆን ይልቅ ከነሱ የተሻልን እንዲያረገን እንመኝ መቼስ ልጆቹን አብዝቶ የሚወድ ነገር ግን ላንቺ ግድ የሌለው ባል እንዲኖርሽ አትፈልጊም አንተም አትፈልግም …የነሱን ጎዶሎ ሞልቶ ከነሱ የተሻለ እንዲያረገን እንመኝ ። እነሱ የተሳሳቱትን ስህተት እነሱን ሆነን ለመድገም አንድከም …አጉል ምኞት ትርፉ ወቀሳ ነው " ።
*
ወደህ ካስጠጋኸው አብልጠህ ውደደኝ
ቸኩዬ ባጠፋ ይቅር እንድትለኝ ። @fkrnbedebdabe
314 viewsĶåš ŧęĸłů, 17:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-26 21:25:21 የጊዜ አጠቃቀም ዘይቤአችን ሲቃኝ!
ዛሬ የምኖረው ኑሮዬ የብዙ ነገር ድምር ነው፡፡ በአንድ ጎኑ የግሌ ጸባይና ዝንባሌ
ጠብታ ሲኖርበት በሌላ ጎኑ ደግሞ በልጅነቴ በምሳሌነት ከመሩኝ ቤተሰቦቼና
አስተማሪዎቼ አይቼና ቀስሜ ያደኩትም ጠብታ አለበት፡፡
እነዚህ ሁኔታዎች ተደምረው የዛሬውን በጊዜ ላይ ያለኝን ግንዛቤ ወደመኖር
አምጥተውታል፡፡ ስለዚህም ካለፈው ሕይወቴ ተጽእኖ የተነሳ የጨበጥኩትን
የጊዜ አያያዝ ሁኔታ ለመገንዘብ ራሴን ማየት መልካም ጅማሬ ነው፡፡
የሚከተሉትን የተለመዱ የጊዜ አያያዝ ዝንባሌዎች እናጢን፡፡
“አቶ የአደጋ ጊዜ ተጠሪ”
ልክ የእሳት አደጋ መከላከያ ሰራተኞች ተግባራቸው በየቦታው እየበረሩ የተነሳን
እሳት ማጥፋት እንደሆነ “አቶ የአደጋ ጊዜ ተጠሪ” እዚህና እዚያ ብቅ ለሚሉ
ሁኔታዎች ምላሽ በመስጠት ጊዜውን የሚያሳልፍሰው ነው፡፡ ለተለያዩ ችግሮች
ምላሽ በመስጠት ከመሯሯጡ የተነሳ ቁጭ ብሎ ጊዜውን በሚገባ ለመጠቀም
የሚረዳውን እቅድ ለማውጣት “ጊዜ” የለውም፡፡ ልክ የእሳት አደጋ ተከላካዮች
ከዚህኛው ወደዚያኛው እሳት እንደሚጣደፉ፣ እንዲህ አይነቱ ሰው ብዙውን ጊዜ
ከስፍራ ወደ ስፍራ በፍጥነት ሲዘዋወርና በወቅቱ ሃሳቡን ለሳበው ችግር ምላሽ
ለመስጠት ሲሯሯጥ ይታያል፡፡
ይህ አይነቱ ዝንባሌ አብዛኛውን ጊዜ ምንጩ የአስተዳደግ ሁኔታ ነው፡፡ አንድ ሰው
ለተደወለው ስልክና ተከሰተ ለተባለው ችግር ሁሉ በድንገት ብድግ በማለት
በሚሮጡ ቤተሰቦች መካከል ካደገ ያንንው ተምሮ ነው የሚያድገው፡፡
“አቶ አስደሳች”
የ“አቶ አስደሳች” ችግር “እምቢ” ለማለት ያለመቻል ችግር ነው፡፡ አንድ ሰው
አንድን ነገር እንዲያደርግለት ከጠየቀው፣ ጊዜ ባይኖረው እንኳ “እሺ” በማለት
ቃል ይገባል፡፡ ሰውን ሁሉ የመሸኘቱ፣ ለቸገረው ሁሉ ገንዘብ አበዳሪነቱ፣ ከአቅሙ
በላይ ቢሆንም እንኳ የተጠየቀውን ስራ ሁሉ በእሺታ የመቀበሉ ዝንባሌ ጊዜ
አጠቃሙን ከመስመር አውጥቶበታል፡፡
“አቶ አስደሳች” በተመሳሳይ ሰዓት ላይ ከሁለትና ከሶስት ሰዎች ጋር ቀጠሮ
ሊይዝ ይችላል - በመዘንጋት ሳይሆን እምቢ የማለት የፈቃድ ጉልበት በማጣት፡፡
እንዲህ አይነት ሰው ከአምስትና ከስድስት ኮሚቴዎች በላይ አባል ሆኖ ራሱን
ሊያገኘው ይችላል፡፡እንዲህ አይነቱ ዝንባሌ ከዝቅተኝነት ስሜትና ተቀባይነት
ለማግኘት ከሚኖር የውስጥ ምኞት ወይም ደግሞ የሰውን ስሜት ላለመጉዳት
ካለ ጽኑ ፍላጎት ሊመነጭ ይችላል፡፡ “አቶ አስደሳች” ብዙ ጊዜ ከሰዎች ሲደበቅ
ይታያል - ይህንን አድርግልኝ ተብሎ ተጠይቆ እምቢ ከሚል መደበቁን
ይመርጣል፡፡
“አቶ ጊዜ አለኝ”
“አቶ ጊዜ አለኝ” አንድን ነገር የሚተገብረው ሲመቸው ወይም “ሙዱን” ሲያገኝ
ነው፡፡ ዘና ያለ፣ መጨናነቅ የማይወድና ብዙውን ጊዜ እግሩን ጠረጴዛ ላይ ሰቅሎ
የሚታይ ሰው ነው፡፡ ተግባሮቹን ቅደም ተከተል የማስያዝ ልማድ ባይኖረውም
በውስጥ ታዋቂነት ግን ማድረግ ደስ ከሚለው ተግባር መጀመር እንደሚወድ
እውቅ ነው፡፡ አንድ ነገር ደስ የሚለው ከሆነ ጊዜ አያጣለትም፡፡ በመቀጠልም
ለማድረግ ቀለል ያለውን የመምረጥ ዝንባሌ አለው፡፡ አንድ የጀመረውን ነገር
ለማስተላለፍ ወይም ለማቆም ትንሽ “እንቅፋት” በቂ ነው፡፡
“አቶ ጊዜ አለኝ” የኑሮው መፈክር፣ “ስደርስ እደርስበታለሁ” ነው፡፡ አብዛኛውን
ጊዜ በጊዜው ያልተከናወነ ተግባር ሊያደርስ የሚችለውን መዘዝም ሆነ ሊጎዳ
የሚችለውን ሰው የማየት ብቃት የለውም፡፡ እንዲሁ በመላ-ምት ስለሚኖር
ከራሱ አልፎ ቤተሰቡንም ሆነ መስሪያ ቤቱን የሚጎትት ታላቅ የስኬት ጠንቅ
ነው፡፡
“ወ/ሪት ማሕበረሰብ”
“ወ/ሪት ማሕበረሰብ” የተወለደችው ከሰዎች ጋር ለመሰባሰብ እንደሆነ
የሚያስመስልባት ማንነት አላት፡፡
@fkrnbedebdabe
438 viewsĶåš ŧęĸłů, 18:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-27 13:19:35 የስሜት ብልህነት ልህቀት

ጥናቶች እንደሚነግሩን ከሆነ በስራም ሆነ በማንኛውም የማህበራዊ ኑሮ 80 በመቶው ስኬታችን የሚመጣው ከስሜት ብልህነት ሲሆን፣ የአእምሮ ብልህነት የሚሰጠን የስኬት መጠን ግን 20 በመቶ ብቻ ነው፡፡ በሌላ አባባል ከፍ ያለ የአእምሮ ብልህነት (IQ) ኖሮህና አእምሮህ በብዙ እውቀት ተሞልቶ ሳለ፣ ስሜታዊ ብልህነት ከሌለህና የራስህንና የሌሎች ሰዎችን ስሜት አያያዝ ካላወቅህበት የአእምሮ እውቀትህ ብቻውን የትም አያደርስህም፡፡

የስሜት ብልህነት ያላቸው ሰዎች ምልክቶች፡-

• አስቸጋሪ ሰዎችንና ሁኔታዎችን በስሜታማ መልኩ አያያዝ
• ራሳቸውን ግልጽ በሆነ መልኩ የመግለጽ ብቃት
• በሰዎች የሚከበር ማንነትን ማንጸባረቅ
• በሰዎች ላይ ተጽእኖ የማምጣት ብቃት
• ሰዎች እንዲደግፏቸው የማነሳሳት ብቃት
• በውጥረት ውስጥ የውስጥን መረጋጋትና ሚዛናዊነትን አለማጣት
• ለሰዎችና ለሁኔታዎች የሚሰጡትን ስሜታዊ ምላሽ ማወቅና ለመቆጣጠር መብቃት
• የተፈለገውን ውጤት ለማግኘት ትክክለኛውን ነገር መናገርና ተገቢውን ነገር ማድረግ
• በድርድር ጊዜ ተገቢውን አቀራረብ በመምረጥ ራሳቸውንም ሆነ ሌላኛውን ሰው መምራት
• አንድን ነገር ከግቡ ለማድረስ ራስን ማነሳሳት
• በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሲያልፉ እንኳ አዎንታዊ ሆኖ መቆየት

አንድ ሰው ምንም ያህል በአእምሮ ብልህነት ቢበስል የስሜት ብልህነት መጠኑ አናሳ ከሆነ በውስጡ ያለው እውቀትና ችሎታ የሚወጣበትና የሚገለጥበት “መስኮት” የለውም፡፡ ስሜት ሲወድቅ፣ ሲዘጋ፣ ሲዛባም ሆነ አላግባብ ሲገለጥ በአንድ ሰው ውስጥ ያለውን ብቃት የመጨቆን ወይም ደግሞ ተቀባይነት እንዳያገኝ የማድረግ ተጽእኖ አለው፡፡ ከዚህ እውነታ አንጻር ነው የስሜት ብልህነት በአእምሮ ብልህነት ላይ የበላይነት አለው የሚባለው፡፡

በሕይወታችን የሚገጥመንን ከባድ ጊዜ የምናልፈው በስሜት ብልህነት ልቆ በመገኘት ነው፡፡

“የስሜት ብልህነት”ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ


ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@fkrnbedebdabe
500 viewsĶåš ŧęĸłů, 10:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-29 18:27:41 ​​ ፍቅርን የሚያጠነክሩ 5 ጠቃሚ ምክሮች

​​❶. በፍቅር አይን መተያየት:- በተለይ የባለትዳሮችን የህይወት ጓዳ ድረስ የመዝለቅ፣ የትዳርን ሳንካዎች በመካፈል የመቆልመምን ዕድል ለበርካታ ዓመታት ለታደሉት አማካሪዎች የትዳር ህይወት የተለየ ትንታኔ አለው፡፡ የትዳር ህይወት በገሀዱ ዓለም የጓዳ መድረክ የሚከወን የመንትዮች ተውኔት ሌላ ምዕራፍ ሲሆን ከእነዚህ መንትዮች የታዳሚነት ድርሻን ብቻ ጠቅልሎ መያዝ ብቻ ሳይሆን የሚጠበቀው የተዋናይም የታዳሚንም ድርሻ መያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
ይህ በባለሙያዎቹ አይን ሲታይ የራስንም የተጓዳኝንም የክወና ብቃት በትዳር ህይወት ውስጥ ለመፈተሽና ስለ አንደኛው አጋር ያለ አመለካከት ሁለቱንም ወገን ያስተያየና ያገናዘበ እንዲሆን ይረዳል፡፡ የተጓዳኝ የእርስ በርስ አመለካከት ሳንካን ሲያስከትል የሚያስተውለው በአብዛኛው ወደ ትዳር ከተገባ በኋላ ነው፡፡ በተለይ ‹‹ከመጋባታችን በፊት የነበረው ያ ሁሉ እንክብካቤ ያ ሁሉ ጉርሻ፤ ያ ሁሉ በሞቴ… ያ ሁሉ ቁልምጫ… ኧረ እጅና ጓንት ነበር የሚሉን… የዛሬን አያደርገውና ክንዶቹ ከቦታቸው ቢታጡ ቢታጡ ቀሪ አድራሻቸው ከወገቤ ነበር…›› የሚል የባለትዳር ሴቶች ስሞታ ከትዳር አማካሪዎቹ ጆሮ በተደጋጋሚ ለመድረስ አለመቦዘኑ እውነታውንና ችግሩን
አጉልቶ ያሳያል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ልክ ከሁለቱም ወገን እንዳልታየ የዳኝነት ውጤት ‹‹ያብዬን ወደ እምዬ›› ላለመለጠፍ መጠንቀቅና የተጓዳኝ ድክመቶች አነጣጥሮ በማየት አቃቂር ከመፈለግ ‹‹በአንተ ትብስ…›› በጥላቻ አይን መተያየቱ ትዳርን ከማናጋት አይመለስም፡፡ በፍቅር አይን መተያየት በራስና በተጓዳኝ ውስጥ ያሉትን የፍቅር ችሮታዎች ትክክለኛ ገፅታ በቅጡና በትኩረት በመመልከት ለግድፈቶች የሚሰጥን ትኩረት በማቅለል እውነተኛ ፍቅርን በእውነተኛ ገፅታው ማቆም ይቻላል፡፡ ስለዚህ በፍቅር አይን በመተያየትና የሚያፈቃቅሩ ሁኔታዎችን በማመቻቸት ጥንዶች እውነተኛን ፍቅር በአይናቸው ለማየት እንደሚችሉ ሊያውቁ ይገባል፡፡

❷. የአመለካከት ልዩነቶችን ከአንድነት ውስጥ ማውጣት:- በተጓዳኞች ግንኙነት ውስጥ ሊከሰቱ የሚችሉ በርካታ
የአንድነት ልዩነቶች በአመለካከት መለያየት አስታከው ከተፍ ማለታቸው
አይቀርም፡፡ ከባለትዳሮች የትዳር ጎጆ እግር የጣለውንና ይህን መሰል ፅዋ
እየተጎነጨ የደረሰ ወይም የደረሰበት ሁሉ የልዩነቶቹን ጣዕም በቅጡ
ያውቃቸዋል፡፡ አንደኛው ወገን የሌላኛውን አመለካከት ለመቀየርና ለማሳመን የራሱን
አመለካከት አክርሮ በመያዝ ‹‹እኔ ያልኩት ብቻ›› የሚልን አቋም ሲያራምድ
ይስተዋላል፡፡ በተለይ ወረት ያላየውና እውነተኛን ፍቅር ጋልበው ከትዳሩ ዓለም
መግባት ለሚሹት ጎጆን ከመቀለሳቸው አስቀድመው በመካከላቸው አንድነታቸውን የሚወስኑና ሁለትነታቸውን ብቻ የሚያመለክቱ በርካታ የህይወት
ፍልስፍናዎች (እውነታዎች) በየግላቸው እንዲያዙ የሚያደርጉ አሉ፡፡ ከዚህ በኋላ ነው እንግዲህ የአመለካከት ልዩነቶች ከቀለሱት ጎጆ በር ሲያንኳኩ እንዳመጣጣቸው ለማስተናገድና ለመሸኘት የማይዳግታቸው፡፡ በተጨማሪም ፍቅርና ትዳር የመማማርና በመተራረም ሂደት የሚያሳድጉት እንደሆነ ቀስ በቀስ የሚረዱትና በሙሉ እርግጠኝነትና ተስፋ የዘላቂ የፍቅር ደጀን የሚሆናቸው፡፡

❸. ለእውነተኛ ፍቅር አሸናፊነት መጣር:-
በመፈቃቀር የጥንድነትን ጉልበት መግለጥና የፍቅርን ፍቱን ኃይል መጋበዝ
የሚቻለው ከሁለቱም ወገን በተውጣጣ የፍቅር ኃይል ነው፡፡ ጥንዶች ከየግላቸው
የሚያዋጡት የፍቅር መስዋዕት ከአንድ መዋሉ ደግሞ ታላቅ የፍቅር
ኃይልን በመፍጠር ለእውነተኛ ፍቅር ዘላለማዊ ጉልበትን ይቸራል፡፡
‹‹ከመቀበል ይልቅ መስጠትን ማስቀደም›› የፍቅር ቀዳሚ መርሆ እንደመሆኑ መጠን ፍቅርን ለመቀበል ፍቅር መስጠትን በማስቀደም ‹‹ከእኔነት›› በቀደመ ይልቁንም በ‹‹እኛነት›› የሚፀናውን እውነተኛ ፍቅር ከእጅ ማስገባቱ አይዳግትም፡፡ በትዳር ዓለም እያሉ ለዚህ ትዳር ዘለቄታ ይነስም ይብዛ ደፋ ቀና ማለት አይቀርም፤ በዚህን ወቅት ፍቅርን መስጠት ማስቀደሙ በፍቅር ህይወት የሚከሰቱ አለመግባባቶችን በፍቅር ኃይል በመግዛት ለመፍታት ፍቱን ጉልበትን ይሰጣል፡፡ የትዳር ህይወትን በአሸናፊነት ለመወጣት አንደኛ ወገን ሌላውን ለማሸነፍ (ለመግዛት) ከመሽቀዳደም ይልቅ በእውነተኛ ፍቅር (የመፈቃቀር) ጉልበት ለትዳሩ ለመገዛትና ለፍቅር አሸናፊነት ቅድሚያን መስጠቱ ይመረጣል፡፡ በእነዚህና መሰል የፍቅር ሀሳቦች ውስጥ መስዋዕት የሆኑለት ራሱ ፍቅር ነገ እነሱን መልሶ በፍቅር ይጠግናቸውና ፍቅር በፍቅር ያደርጋቸዋል፡፡ የፍቅር ሰዎችም ሆነን እንደ ምሳሌ የምንነሳ ያደርገናል፡፡ ለተጋቢዎችም ለአዲስ ተፈቃቃሪዎችም መልካም ፍቅር ይሁንላችሁ፡፡

,,,,,,,,,,,, ,,,,,,,,,,,
••●◉Join us share◉●••
@fkrnbedebdabe
━━━━━━━✦ ✿ ✦━━━━━━━
567 viewsĶåš ŧęĸłů, 15:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-18 07:37:30 #Dr._Eyob_Mamo
ሳትገደዱ ለውጡ!

በሕይወታችሁ ለውጥ የሚባለው ነገር የማይቀር ሂደት ነው፡፡ የኑሮ እውነታ ይለወጣል . . . የሰው ሁኔታ ይለወጣል . . . ሌላው ቀርቶ የእናንተው ሁኔታ ይለወጣል፡፡ በዚህ ከለውጥ በማያመልጥ የሕይወት ጎዳና ውስጥ የለውጥን ባህሪይ መገንዘብ የግድ ነው፡፡
ሶስት አይነት የለወጥ መንገዶች አሉ፡፡ እነዚህ መንገዶች ጉዳት (Pain)፣ ግፊት (Pressure)፣ ከራእይ የሚመጣ ጉጉትና ደስታ (Pleasure) በመባል ይታወቃሉ፡፡

1. ጉዳት (Pain)
አንዳንድ ሰዎች በሕይወታቸው ለውጥ ማምጣት እንዳለባቸው ቢያውቁትም ሰዎች ወይም ሁኔታዎች በጣም እስከሚጎዷቸው ይጠብቃሉ፡፡ ይህ የሚሆንበት ምክንያት ለውጥን ለማምጣት ብቃት እንደሌላቸው በማሰብ፣ ለውጥን ቢያመጡ የሚያስከፍላቸውን ዋጋ በመፍራት ወይም ደግሞ ከነገ ነገ እንቀሳቀሳለሁ በማለት የማስተላለፍ ዝንባሌ ሊሆን ይችላል፡፡

2. ግፊት (Pressure)
አንዳንድ ሰዎች በሕይወታቸው ለውጥ ማምጣት እንዳለባቸው ቢያውቁትም ውስጣዊ ወይም ውጫዊ ግፊት እስከሚያስገድዳቸው ድረስ ንቅንቅ አይሉም፡፡ ውስጣዊ ግፊት እንደ ጭንቀት፣ ፍርሃት፣ መረበሽና የመሳሰሉትን ሲያመለክት፤ ውጫዊ ግፊት ደግሞ በዚያው ሁኔታ መቆየት እስከማይችሉ ድረስ የነገሮች መለዋወጥና ተገፍቶ ጠርዙ ላይ የመድረስን ሁኔታ አመልካች ነው፡፡

3. ከራእይ የሚመጣ ጉጉትና ደስታ (Pleasure)
አንዳንድ ሰዎች በሕይወታቸው ለውጥ ማምጣት እንዳለባቸው በሚገባ ሲገባቸው ያንን ለውጥ የሚያገናኙት ለነገው ካላቸው ራእይ ወይም ዓላማ ጋር ነው፡፡ እንደዚህ አይነት ሰዎች ካለማቃረጥ ወደ ራእያቸው የሚወስዳቸውን ለውጥ ለማስተናገድም ሆነ እነሱው አነሳስተው ለማምጣት ከማሰብና ከመንቀሳቀስ አርፈው አያውቁም፡፡ ለእነሱ ለውጥን ለማምጣ የወደፊት ራእይን ዓላማ በቂ ነው፡፡ እስኪጎዱና ሁኔታቸው እላያቸው ላይ ጊዜው እስኪያልፍበት (Expire እስከሚያደርግ) አይጠብቁም፡፡

አንድን ነገር ላስታውሳችሁ፡- ስለለውጥ የማሰቢያው ጊዜ ችግር ሲከፋና ከአቅም በላይ ሲሆን፣ ሰዎች ሲለዋወጡ፣ ስንጎዳ . . . ብቻ አይደለም፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ሳይለውጡ ከመቅረት በጉዳትና በግፊትም ቢሆን መለወጥ የተሻለ ቢሆንም፣ ከሁሉም የላቀው መንገድ ግን የነገ ራእችሁን ቀን በቀን በማሰብና በማሰላሰል በየእለቱ ማድረግ ስለሚገባችሁ ለውጥ የማሰብ ውሳኔና ብቃት ማዳበር ነው፡፡

የለውጥ ሰው ሁኑ!
ሠናይ ቀን
@fkrnbedebdabe
528 viewsĶåš ŧęĸłů, 04:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-14 09:42:26 ፍካሬ እዉነት ( በእውቀቱ ስዩም )

ሰማዩ እንዲ እንደዛሬ ርቆ ሳይወረወር
ሁሉ እንዳሻዉ የሚቆርሰው
ሁሉ እንዳሻዉ የሚጎርሰዉ
ግዙፍ እንጀራ ነበር
ብለሽ የነገርሽን
እዉነት ነዉ ተቀብያለዉ
ምክኒያቱም እወድሻለዉ
አያቴ ሶስት መቶ አመታት ኖሩ
የመቶ አመት ሰዉ እያሉ ብርቱ ፅኑ ነበሩ
ዝሆን በጥፊ ጣሉ
አንድ ጥይት ተኩሰዉ ሶስት ነበሮች ገደሉ
ብለሽ የነገርሽን
እዉነት ነዉ ተቀብያለዉ
ምክኒያቱም እወድሻለዉ
አባቴ ከሰዎች ሁሉ ይለያል
በዓይኖቹ ብቻ ሳይሆን በማጅራቱም ያያል
ብለሽ የነገርሽኝን
እዉነት ነዉ ተቀብያለዉ
ምክኒያቱም እወድሻለዉ
ግና ሞኝ እንዳልመስልሽ አይደለሁም ተላላ
በርግጥ በእጄ በእጄ ብላሻለች ነብሴ ሁሉን ተቀብላ
እዉነት ማለት ከሚወዱት መስማማት እንጂ አደለምና ሌላ።
@fkrnbedebdabe
489 viewsĶåš ŧęĸłů, 06:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-10 10:03:47 ባንተ ውስጥ ያንተን እድገት የሚቃወም ጭራቅ አለ፡፡ከድህነት እንድታመልጥ አይፈልግም፡፡ከመጥፎ ጓደኞችህ ስትሸሽ ያመዋል፡፡ከሱስ ስትርቅ ይጨንቀዋል፡፡ፍላጎቱ ለጊዛዊ ደስታ ጊዜና ሐይልህን በከንቱ እንድታባክን ነው፡፡

በተለይ አዲስ ነገር ስትሞክር ይንጫጫል፡፡ ይህን ማድረግ አደጋ አለው!! ጎመን በጤና! ዋ! ትከስራለህ !ይሳቅብሃል!!" በማለት አዛኝ መስሎ እንደ ሐውልት ያስቆምሃል፡፡በጊዜ ሂደትም ወደኃላ ጎትቶ ይጥልሃል፡፡በገዛ ራስህ ህይወት አቅም ታጣለህ፡፡እሱ ንጉስ አንተ ባርያ ትሆናለህ::

ባርነት አልሰለቸህም? የራስህ ህይወት ንጉስ መሆን አላመማረህም? ከጭራቁ እስር ቤት ነጻ መውጣትስ? በፈለከው ሰዓት የፈለከውን ነገር ማድረግስ? የራስህን ህይወት መኪና መሪ መጨበጥስ? ህልምህን አሳክተህ ከስኬት ተራራ ጫፍ መሆንስ? አያጓጓህም? መልስህ "አዎ!" ከሆነ በመጀመርያ በውስጥህ ያንቀላፋውን ጀግና ቀስቅሰው፡፡

ባንተ ውስጥ ያንቀላፋ ምንም ነገር ማድረግ የሚችል ጀግና ሰው አለ፡፡ይህ ጀግና ገራሚ ሐይል ነው፡፡ይህንን ሐይል ማድመጥ ጀምር፡፡የጭራቁን አቅምና ሐይል ከውስጥህ ነቅሎ ይጥለዋል፡፡

ጭራቁ ማንነትህ ፈሪ ነው፡፡ጀግናው ማንነት #አማኝ ነው፡፡ጭራቁ ማንነትህ ሰነፍ ነው፡፡ጀግናው ማንነትህ #ለፊ ነው፡፡ጭራቁ ማንነትህ "ሰው ምን ይለኛል?" ይላል፡፡ስህተት ይፈራል፡፡ፍጹም መስሎ ለመታየት ይሞክራል፡፡ጀግናው ማንንትት ግን "እኔ ራሴን ምን እላለው? ፈጣሪስ ምን ይለኛል?" ይላል፡፡ፍጹም መስሎ የመታየት ምኞት የለውም፡፡እሱ የህይወት ዘመን ተማሪ ነው፡፡ ጭራቁ ማንነትህ ጊዛዊ ደስታን ብቻ ይፈልጋል፡፡ጀግናው ማንነትህ ግን ረጅሙን የውስጥ ሰላም፣ ፍቅር፣ ወሳጣዊ ደስታና ስኬት ይሻል። የላቀ አስተሳሰብና ክህሎት በማስቀደም ስኬትን መጎናጸፍ ።
መልካም ሰንበት
@fkrnbedebdabe
483 viewsĶåš ŧęĸłů, 07:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-08 18:08:15 የነጭ ሽንኩርት መድኃኒትነት

1. ነጭ ሽንኩርት ስራን በትክክል ለማከናወን፣ የሰውነት ሕዋሳትን ጤናማ ለማድረግ ፣ድካምን ለማስወገድ፣ዕድሜን ለመጨመር፣በአይጥና በልዩ ልዩ ተባዮች የሚመጡትን ተስቦ በሸታዎችን ለመከላከል ነጭ ሽንኩርት መብላት በጣም ጠቃሚ ነው፡፡

2. ማንኛውም ሰው መጥፎ ሽታ ባለበት አካባቢ ለፅዳት ከመሰማራቱ በፊት ነጭ ሽንኩርት ከትፎ ቢበላ ከማንኛውም በሽታ ከሚያመጡ ተዋህሲያን ለመዳን ይቻላል፡፡

3. በቂ ሕክምና በሌለበት አካባቢ በቁስል ለሚሰቃይ ሕሙማን በነጭ ሽንኩርት ጭማቂ አጥቦ በቁስሉ ዙሪያ በመደምደም በፋሻ ወይም በንፁህ ጨርቅ በማሰር ሕመምተኛውን ለመፈወስ ይችላል፡፡

4. ነጭ ሽንኩርት ቀቅሎ እንፋሎቱን የካንሰርንና የቲቢ በሽታዎችን ለመከላከልና በሳንባ አካባቢ ብርድና ጉንፋን ለማዳን ፍቱን መድኃኒቱ ነው፡፡

5. ብርድ ብርድ በሚያሰኝ ሕመምና በተለይም በጥርስ ሕመም ለሚሰቃዩት ሕሙማን ሁለት ራስ ነጭ ሽንኩርት የውስጠኛውን ሽፋናቸውን በመላጥ በሁለቱም ጉንጫቸው በተለይም በተነቃነቀው ጥርስ በኩል ነክሰው ረዘም ላሉት ሰዓት ቢጠቀሙበት መልሶ መልሶ ይጠነክራል፡፡

6. ለአስም፣ ለጉሮሮ ክርካሪ ወይም ኮርታ ለተባለው በሽታ እንዲሁም ጉሮሮ ለማፅዳት የነጭ ሽንኩርት ጭማቂ በስኳር ወይም በማር መጠጣት የተፈተነ መድኃኒት ነው፡፡

7. ነጭ ሽንኩርት የራስ ምታትና የደም ብዛት ያለባቸው ሰዎች ከ3 እስከ 5 ቀናት በማከታተል ሦስት ሦስት ፍንካች በቀን ሦስት ጊዜ ቢበሉ ከድካምና ከደም ብዛት ሊፈወሱ ይችላሉ፡፡

8. በደም መርጋት ምክንያት ለሚሰቃዩ ፣የልብ በሽታን፣ የፊንጢጣ ኪንታሮትና የእግር ደም ሥር እብጠት varicose የተባሉትን በሽታዎች ለመከላከልና ለመዳን ነጭ ሽንኩርት በመብላት መፈወስ ይችላል፡፡

9. ነጭ ሽንኩርት የቆላ ቁስል፣ችፌን፣የጨጓራ በሽታን ወረርሽኝን ኮሌራን ሳይቲካን የቁርጥማትን ሕመምን እንደሚያድን የተረጋገጠ ነው፡፡

ሰላም እና ጤና ከእናተ ጋር ይሁን
@fkrnbedebdabe
470 viewsĶåš ŧęĸłů, 15:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-08 14:44:51 በመዳፍህ ላይ ያረፈ የዝናብ ጠብታ ንፁህ ከመሆኑ የተነሳ ሊጠጣ ይችላል። በቆሻሻ ቦታ ላይ ያረፈ የዝናብ ጠብታ እግርን እንኳ ለመታጠብ አይሆንም። በሞቃታማ ቦታ ላይ ያረፈ የዝናብ ጠብታ መድረቁ አይቀርም። በቅጠል ላይ ያረፈ የዝናብ ጠብታ እንደ እንቁ ያብረቀርቃል። የዝናቡ ጠብታ ተመሳሳይ ነው ነገርግን ቆይታውንና ጥቅሙን የሚወሰነው በሚያርፍበት ቦታ ነው። የምትውልበት ቦታና አብራኸው የምትውለው ሰው ልክ እንደ ዝናቡ ጠብታ ጠቃሚነትህንና ቆይታህን ልወስኑት ይችላሉ። አብረኸው የምትውለው ሰው ንፁህ ልብ ያለውና አላማውን ትልቅ ከሆነ የአንተም ስብዕና በበጎነት ይቀይረዋል። የምትውለው ሰው የወረደ ስብዕና ያለው ከሆነ የአንተም ስብዕና በመጥፎ ሊቀይረው ይችላልና ውሎህን መልካም ቦታና መልካም ሰው ጋር ይሁን።

ከfb መንደር
join and follow our channel
Share Share Share
@fkrnbedebdabe
432 viewsĶåš ŧęĸłů, 11:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ