Get Mystery Box with random crypto!

#Dr._Eyob_Mamo ሳትገደዱ ለውጡ! በሕይወታችሁ ለውጥ የሚባለው ነገር የማይቀር ሂደት ነው፡ | ፍቅርን በደብዳቤ @ fkrn bedebdabe

#Dr._Eyob_Mamo
ሳትገደዱ ለውጡ!

በሕይወታችሁ ለውጥ የሚባለው ነገር የማይቀር ሂደት ነው፡፡ የኑሮ እውነታ ይለወጣል . . . የሰው ሁኔታ ይለወጣል . . . ሌላው ቀርቶ የእናንተው ሁኔታ ይለወጣል፡፡ በዚህ ከለውጥ በማያመልጥ የሕይወት ጎዳና ውስጥ የለውጥን ባህሪይ መገንዘብ የግድ ነው፡፡
ሶስት አይነት የለወጥ መንገዶች አሉ፡፡ እነዚህ መንገዶች ጉዳት (Pain)፣ ግፊት (Pressure)፣ ከራእይ የሚመጣ ጉጉትና ደስታ (Pleasure) በመባል ይታወቃሉ፡፡

1. ጉዳት (Pain)
አንዳንድ ሰዎች በሕይወታቸው ለውጥ ማምጣት እንዳለባቸው ቢያውቁትም ሰዎች ወይም ሁኔታዎች በጣም እስከሚጎዷቸው ይጠብቃሉ፡፡ ይህ የሚሆንበት ምክንያት ለውጥን ለማምጣት ብቃት እንደሌላቸው በማሰብ፣ ለውጥን ቢያመጡ የሚያስከፍላቸውን ዋጋ በመፍራት ወይም ደግሞ ከነገ ነገ እንቀሳቀሳለሁ በማለት የማስተላለፍ ዝንባሌ ሊሆን ይችላል፡፡

2. ግፊት (Pressure)
አንዳንድ ሰዎች በሕይወታቸው ለውጥ ማምጣት እንዳለባቸው ቢያውቁትም ውስጣዊ ወይም ውጫዊ ግፊት እስከሚያስገድዳቸው ድረስ ንቅንቅ አይሉም፡፡ ውስጣዊ ግፊት እንደ ጭንቀት፣ ፍርሃት፣ መረበሽና የመሳሰሉትን ሲያመለክት፤ ውጫዊ ግፊት ደግሞ በዚያው ሁኔታ መቆየት እስከማይችሉ ድረስ የነገሮች መለዋወጥና ተገፍቶ ጠርዙ ላይ የመድረስን ሁኔታ አመልካች ነው፡፡

3. ከራእይ የሚመጣ ጉጉትና ደስታ (Pleasure)
አንዳንድ ሰዎች በሕይወታቸው ለውጥ ማምጣት እንዳለባቸው በሚገባ ሲገባቸው ያንን ለውጥ የሚያገናኙት ለነገው ካላቸው ራእይ ወይም ዓላማ ጋር ነው፡፡ እንደዚህ አይነት ሰዎች ካለማቃረጥ ወደ ራእያቸው የሚወስዳቸውን ለውጥ ለማስተናገድም ሆነ እነሱው አነሳስተው ለማምጣት ከማሰብና ከመንቀሳቀስ አርፈው አያውቁም፡፡ ለእነሱ ለውጥን ለማምጣ የወደፊት ራእይን ዓላማ በቂ ነው፡፡ እስኪጎዱና ሁኔታቸው እላያቸው ላይ ጊዜው እስኪያልፍበት (Expire እስከሚያደርግ) አይጠብቁም፡፡

አንድን ነገር ላስታውሳችሁ፡- ስለለውጥ የማሰቢያው ጊዜ ችግር ሲከፋና ከአቅም በላይ ሲሆን፣ ሰዎች ሲለዋወጡ፣ ስንጎዳ . . . ብቻ አይደለም፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ሳይለውጡ ከመቅረት በጉዳትና በግፊትም ቢሆን መለወጥ የተሻለ ቢሆንም፣ ከሁሉም የላቀው መንገድ ግን የነገ ራእችሁን ቀን በቀን በማሰብና በማሰላሰል በየእለቱ ማድረግ ስለሚገባችሁ ለውጥ የማሰብ ውሳኔና ብቃት ማዳበር ነው፡፡

የለውጥ ሰው ሁኑ!
ሠናይ ቀን
@fkrnbedebdabe