Get Mystery Box with random crypto!

ፍካሬ እዉነት ( በእውቀቱ ስዩም ) ሰማዩ እንዲ እንደዛሬ ርቆ ሳይወረወር ሁሉ እንዳሻዉ የሚቆር | ፍቅርን በደብዳቤ @ fkrn bedebdabe

ፍካሬ እዉነት ( በእውቀቱ ስዩም )

ሰማዩ እንዲ እንደዛሬ ርቆ ሳይወረወር
ሁሉ እንዳሻዉ የሚቆርሰው
ሁሉ እንዳሻዉ የሚጎርሰዉ
ግዙፍ እንጀራ ነበር
ብለሽ የነገርሽን
እዉነት ነዉ ተቀብያለዉ
ምክኒያቱም እወድሻለዉ
አያቴ ሶስት መቶ አመታት ኖሩ
የመቶ አመት ሰዉ እያሉ ብርቱ ፅኑ ነበሩ
ዝሆን በጥፊ ጣሉ
አንድ ጥይት ተኩሰዉ ሶስት ነበሮች ገደሉ
ብለሽ የነገርሽን
እዉነት ነዉ ተቀብያለዉ
ምክኒያቱም እወድሻለዉ
አባቴ ከሰዎች ሁሉ ይለያል
በዓይኖቹ ብቻ ሳይሆን በማጅራቱም ያያል
ብለሽ የነገርሽኝን
እዉነት ነዉ ተቀብያለዉ
ምክኒያቱም እወድሻለዉ
ግና ሞኝ እንዳልመስልሽ አይደለሁም ተላላ
በርግጥ በእጄ በእጄ ብላሻለች ነብሴ ሁሉን ተቀብላ
እዉነት ማለት ከሚወዱት መስማማት እንጂ አደለምና ሌላ።
@fkrnbedebdabe