Get Mystery Box with random crypto!

ክፍል.......5 (በእውነተኛ ታሪ የተመሰረተ) አዘጋጅ፦ ፍቅርን በቃላት . . | 💕 ፍቅርን በቃላት 💕

<<ጠይሙ ባሌ!>>


ክፍል.......5

(በእውነተኛ ታሪ የተመሰረተ)

አዘጋጅ፦ ፍቅርን በቃላት
.
.
.
.... ባሌ ፊት ለፊቴ ከጠረጴዛው ባሻገር አገጩን እጁ ላይ አስደግፎ: አንገቱን ደፍቶ ጠረጴዛውን እያየ ተቀምጦዋል...ሊያባብለኝ አልሞከረም...እኔም አልፈለኩም:: አሁን አንድ ቃል ቢናገረኝ: ወይም ሊነካኝ ቢሞክር ጉሮሮውን ሳልይዘው አልቀርም::

እንደምንም እራሴን አረጋጋሁና ለመናገር ሞከርኩ:: "ይ-ህ-ን-ን...ሁ-ሁ-ሉ...ስ-ስ-ስ-ታ-ደ-ር-ግ...ለ-ም-ም-ን... አ-ል-ል-ል-ነ-ገ-ር-ከ-ኝ-ም....አ-ን-ን-ተ-ተ...አ-ን-ተ..." ለሱ የሚገቡ ስድቦች ስላጣሁ ትንሽ ቆም አልኩና ቀጠልኩ... "ጨ-ካ-ካ-ኝ....እ-እ-እ...ቆ-ሻ-ሻ-ሻ"ቀና ብሎ አየኝ...አይኑ ላይ ምንም አይታይም...ቁጣም: ቁጭትም: ንዴትም: ፍቅርም: በቀልም: ጥላቻም...እንደው ምንም ምንም...አስፈራኝ:: 
"ሌ-ላ ሴ-ት ወደድክ እንዴ?" ያላሰበውን ጥያቄ ዱብ አደረኩለት::  "እ-ን-ዴ-ዴ-ዴ-ዴ..." ድንገት ነቃ አለ...እጆቹን የሚያደርግበት ቦታ ያጣ ይመስል አወራጫቸው "ምን አይነት ጥያቄ ነው?" ወንበሬ ላይ ተደላድዬ ተደግፌ ተቀመጥኩና እጆቼን አጣምሬ አፈጠጥኩበት::
ላቡ ግንባሩ ላይ አቸፈቸፈ...ምላሱ ግን ትንፋሽ እያጠረው ቀጠለ  "እንዴት ብትገምቺኝ ነው? ባለትዳር ሆኜ...."  አቁዋረጥኩት "ምነው ታዲያ አላበህ?" ሌላ ጥያቄ::  "ቤቱ ይሞቃል..." እየተደናበረ ተነስቶ ጃኬቱን አወለቀና ወንበሩ መደገፊያ ላይ አንጠለጠለው:: በህይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ባሌን ጠረጠርኩት::  "ለፍች ምን አስሮጠህ ግን?" ያንን ሁሉ ለቅሶ በድንገት አቁሜ ወደ መስቀልኛ ጥያቄ ገባሁ...ከላይ የተረጋጋሁ ልምሰል እንጂ ልቤ ብትንትኑ ወጥቶዋል::  "በቃ ልንስማማ አልቻልንም...ሁሌ መኩዋረፍ ነው:: በተለይ ልጆች ከወለድሽ በሁዋላ ለኔ ብዙም ጉዳይ የለሽም...ተለውጠሻል" 

"እ-ን-ዴ!" አልኩ በመገረም አፌን ይዤ "ያንተው ልጆች እኮ ናቸው"  "ቢሆኑም...ለኔ ምንም ጊዜ የለሽም"  "ታዲያ ስንት ጊዜ የቤት ስራ አግዘኝ: ደከምኩ ብዬ ጠየኩህ?"  "አ-ይ-ይ-ይ...." አለና አመነታ  "ጨርሰው እንጂ...አይ ምን?"  "እኔ ቤታችን ውስጥ ምንም እንዳይጎድል...እንደውም ሞልቶ እንዲትረፈረፍ በሳምንቱ ውስጥ አንዳንዴ ሰባቱንም ቀን እለፋለሁ...ቤቴ ስመጣ

ደግሞ ማረፍ ነው የምፈልገው..." "ሰባቱንም ቀን ማን ስራ አለህ...ፈልገህ እኮ ነው...ያለን መቼ አነሰን?"  "አንቺ ባታመሰግኚኝም ለልጆቼ የተሻለ ህይወት ነው የምለፋውና ምንም አይደል...ሳረጅ አርፋለሁ"  "እና መፍትሄ ያልከው ከምትለፋላቸው ልጆች መለየቱን ነው?"  "ወድጄ አይደለም...አንቺ ነሽ የገፋሽኝ...አሁን ግን በቃ ወስኛለሁ" ውስጤ ሲግል ተሰማኝ::  "እና አሁን በዚህ በምሽት የት ነው የምትሄደው?" 

"ለጊዜው አንድ የስራ ጉዋደኛዬ ጋ እቆያለሁ" ሰበቡ ሁሉ አልጣመኝም...አላመንኩትም...ግን ደግሞ እሄዳለሁ ካለ ጥርግ...ኩራቴ አሸነፈኝ: አልተለማመጥኩትም:: ፊቴ የተቀመጠውን ወረቀት ማገላበጥ ጀመርኩ:: 
"ይሄንን መቼ ነው እንድፈርምልህ የምትፈልገው?" ወሬውን ድንገት ቀየርኩት::  አመነታ..."እ..ዛሬም ብትፈርሚው ደስ ይለኛል...እኔና አንቺ ፍርድ ቤት እየተጉዋተትን ገንዘባችንን ጠበቃ ከሚበላው በሰላም ብንጨርሰው አይሻልም?"  "ለምንድነው ባንክ ያለን ገንዘብ እሩቡ ብቻ የሚደርሰኝ?"
ኮስተር ብዬ ጠየኩ "ይህን ገንዘብ እንደሴቱ ማማር መሸቀርቀር ሳያምረኝ የቆጠብኩት ነውና ሌላው ቢቀር ግማሹ ይገባኛል" ከሞኝዋ ሚስቱ ያልጠበቀው ጥያቄ ነበርና ትንሽ አሰላሰለ::
 
"ቤቱንና አዲሱን መኪና ላንቺ ሰጠሁሽ እኮ:: ለልጆቹም በየወሩ በቂ ተቆራጭ ተመድቦልሻል...ለኔም አስቢልኝ እንጂ"  "ቤቱና መኪናውን እኮ ከነባንክ እዳው ነው ያሸከምከኝ...ጣቴን የምጠባ ህፃን አረከኝሳ......ተቆራጩም በግድህ ነው...ከፈለክ የጡረታ ምናምን ገንዘብህን ቀቅለህ ብላው" ፊቱ ላይ አሽቀነጠርኩለት...አቤት ፊቱ ላይ ያየሁት መደናገጥ...ልቤ ሞላች:: 
"ልጆቹን በሙሉ ሰጠሁሽ እኮ...ምን ያህል እንደምትሳሽላቸው..."  እንጣጥ ብዬ ቆምኩና ጠረጴዛውን ነረትኩት::  "ስማ አንተ ቆሻሻ...በደንብ ስማኝ" የድምፄ ውፍረት እንኩዋን እሱን እኔንም አስደነገጠኝ...ቀጠልኩ..."እበትም ትል ይወልዳል:: አንድ ቀን ዞር ብለህ ያላየሀቸውን ልጆች ዛሬ ካንቺ ልነጥል ብትል አለቀልህ...አላማዬ አንተን ማጥፋት ይሆናል"
አንጋጠው የሚያዩኝ አይኖቹ ላይ አፈጠጥኩባቸው "በመኪና ነው የምወጣብህ...አንዴ አይደለም...እየተመላለስኩ ሀያ ጊዜ...ለዛች ለድሀ እናትህ የሚላክ እሬሳ እስከሚታጣ ድረስ...ተግባባን?" እነዛ ኩሩ አይኖቹ በሽብር ተርበተበቱ...ምራቁን ሲውጥ የአዳም ፍሬው ወደላይ ወደታች ብሎ አሳበቀበት::

ይቀጥላል .....


የመወያያ ግሩፑን ይቀላቀሉን
@ethio_lifes_group
@ethio_lifes_group
@ethio_lifes_group


╔═══❖• •❖═══╗
@fkrn_be_kalat
╚═══❖• •❖═══╝
4 any comment
@fkrn_be_kalat_bot
❥❥________⚘_______❥❥