Get Mystery Box with random crypto!

ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት

የቴሌግራም ቻናል አርማ finottebirhan — ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት
የቴሌግራም ቻናል አርማ finottebirhan — ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት
የሰርጥ አድራሻ: @finottebirhan
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.16K
የሰርጥ መግለጫ

የአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ለማንኛውም ጥያቄ
@Finotebrhan

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-20 17:51:24 +++በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን +++


አድርሺኝ አልኳት አደረሰችኝ
አፄ ዮስጦስ

ከጎንደር መካነ ስብሐት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን መተከል ጋር በተያያዘ በጎንደር ከተማ ውስጥ የሚካሔድ አንድ ሥርዓት አለ፡፡ ይህም ሥርዓት አድርሺኝ በመባል ይጠራል፡፡ ሥርዓቱ የሚከናወነው በፍልሰታ ጾም ወቅት ነው፡፡ ስለ ሥርዓቱ አጀማመር አባቶች ሲናገሩ፣ ዐፄ ዮስጦስ ወደ ጦርነት ሲዘምቱ “ጦርነቱን በልደታ ለማርያም ምልጃ ተደግፌአሸንፌ ከተመለስኩ በፍልሰታ ለማርያም ሱባኤ ማታ ማታካህናቱን፤ መኳንንቱንና ምእመናንን ሰብስቤ ግብዣ አደርጋለሁ” በማለት ብፅዐት ይገባሉ፡፡ እርሳቸውም ድል አድርገው ተመለሱ፤ በቃላቸውም መሠረት ግብዣ አደረጉ፡፡ ሕዝበ ክርስቲያኑም እርሳቸውን ተከትሎ በጾመ ፍልሰታ ወቅት ይህን ሥርዓት ይተገብሩት ጀመር፤ ስያሜውም “አድርሺኝ” ተባለ፡፡ አድርሺኝ በመላው ጎንደር እስከ ዛሬ ድረስ በየቤተክርስቲያኑና በየአካባቢው በፍልሰታ ጾም ወቅት ይከናወናል፡፡
ምእመናን ከቅዳሴ መልስ ሱባኤው እስኪያልቅ በመረጡት አንድ ቤት ውስጥ ተሰብስበው ቆሎና ጠላ ተዘጋጅቶ በእመቤታችን ስም ጽዋ ይጠጣሉ። በተለይ መነኮሳያት እናቶች በሚታደሙበት ጽዋ ላይ “ኦ! ማርያም” የሚለውን የተማጽኖ መዝሙር ይዘምራሉ። ይህ መዝሙር በሚዘመርበት
ጊዜ እመቤታችን ፊት ለፊት ስለምትቆም በፍፁም ተመስጦና መንበርከክ ያከናውኑታል። በዋነኛነት የመካነ ስብሐት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤት ይህንን የተቀደሰ ተግባር በማስተባበርና በማስፈጸም እንዲሁም
ትውፊቱ እንደጠበቀ ለተተኪው ትውልድ እንዲተላለፍ በማድረግ እየሠራ ይገኛል፡፡

አምላከ ቅዱሳን ጾሙን የሰላም የፍቅር የንስሐና የበረከት ያድርግልን።

ከታሪኩ ጋር የሚገናኘውን ይሄንን መዝሙር ተጋበዙልኝ
376 views14:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 09:29:03
◃▸◃▸◃▸ ደብረ ታቦር የቤት ለቤት አገልግሎት ◃▸◃▸◃▸
▭▭▭▭ ◎⃝ ◎⃝ ⃟ ◎⃝ ◎⃝ ▭▭▭▭
ዩቲዩብ ገፅ፡ https://youtube.com/channel/
@finote brhan
ቲክቶክ፦ http://tiktok.com/@
@finotebrhan
ቴሌግራም ገፅ፦
ትምህርትና መረጃዎች፡ t.me/@finotebrhan
ፌስቡክ ገፅ፡ fb.me/@finotebrhan
570 views06:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 19:02:44 #አጋፋሪ_ይደግሳል

፩ኛ ትርጕም አጋፋሪ፤ አሁን በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ደረጃ የማኅሌቱን ሥርዐት ፥ የዝክር ሁኔታን የሚያስተባብር አጋፋሪ ሲባል፤ ምክትሉ መጨኔ ይባላል
፪ኛ ትርጕሙ፤ አጋፋሪ፤ በቀድሞ ዘመን በሃገራችን በተለይም በቤተ መንግሥት ያለ ሹመት ሲሆን፤ (በጎንደር ፥ በሸዋ ፥ በትግሬ ፥ በወለጋ፥ በአሊባቡር፥ በሐረርጌ፥ በጅማ፥ በወሎ አጋፋሪ ተብሎ ሲጠራ በጎጃም መጨኔ ይባላል/
ሁለቱንም በቀድሞ ዘመንም ሆነ አሁን ባለው ሁኔታ ትርጕሙን እናያለን ፤

፩ኛ አሁን ካለው የቤ/ክን አገልግሎት አንጻር፤ አጋፋሪ ማለት የማኅሌቱን ሥርዐት ፥ የዝክር ሁኔታን የሚያስተባብር ሲሆን ምክትሉ መጨኔ ይባላል፡፡ ይህ አጋፋሪ በደብረ ታቦር በዓል ላይም በቅዱስ ሚካኤል ተመስሎ፤ ‹‹ሆያ ሆዬ›› ይባላል ይኸውም
‹‹ሆያሆዬሆ››፤ ማለት ጌታው ሆዬ ፥ እሜቴ ሆዬ ለማለት ነው፡፡
‹‹እዚያ ማዶ ጢስ ይጤሳል›› የተባለው፤ እስራኤላውያን በበረሃ ለ40 ዓመታት ሲጓዙ ደመና እየጋረዳቸው (እየጤሰ) ስለመራቸው ነው

‹‹አጋፋሪ ይደግሳል››፤ የተባለው አጋፋሪው /አለቃው/ ቅዱስ ሚካኤል ሲሆን፤ ይደግሳል መባሉ እስራኤላውያንን ‹‹በዕደ መልአኩ ይዕቀበነ ፥ ሰላመ ዚአሁ የኀበነ›› እንዲል፤ በአምላክ ትዕዛዝ ቅዱስ ሚካኤል መናን ከደመናን ፥ ውኃን ከጭንጫ ዓለት እያፈለቀ (እየደገሰ) መርቷቸዋልና ነው

እንዲሁም የአብነት (የቆሎ) ተማሪዎች በክረምት ሲለምኑ የቆዩትን አጠራቅመው፤ የደብረ ታቦር ዕለት ብርሃነ መለኮቱን የገለጠ ጌታ ለኛም እንዲገልጥልን ብለው፤ ደግሰው ለሕዝቡ ያበላሉ ፥ ያጠጣሉ፡፡ /ይህ ሥርዐት በደብራችንም የሚከናወን ድርጊት ነው፡፡/
‹‹ያችን ድግስ ውጬ ውጬ››፤ የተባለውና በድግስ የተመሰለው መና ሲሆን፤ በደጋሹ ቅዱስ ሚካኤል አማካይነት እስራኤል 40 ዓመታት መመገባቸውን (መና መዋጣቸውን) መናገር ነው፡፡

‹‹ከድንክ አልጋተገልብጬ›› ፤ ድንክ አልጋ የምትመች እንደሆነች ሁሉ ፥ በድንክ የምትመሰለውንና የምትመቻቸውን ተስፋዪቱ ምድር ኢየሩሳሌምን መውረሳቸው መናገር ነው

‹‹ያቺ ድንክ አልጋ አመለኛ፥ ያለ አንድ ሰው አታስተኛ››፤ መባሉ እስራኤል ከግብጽ ሲወጡ 600,000 ሆነው ሲሆን፤ ሁሉም በምድረ በዳ አልቀው ኢየሩሳሌምን የወረሳት ሴትና ሕፃናት ሳይቈጠሩ፤ አንድ ኢያሱና አንድ ካሌብ ናቸው ለማለት ነው

፪ኛ አጋፈረ፤ግስ ሲሆን በቤተ መንግሥት ፥ በግብዣ ቦታ፥ …. በር ላይ ቆሞ የሚገባውንና የሚወጣውን ሰው አስተናበረ አስተናገደ አጋፋሪ፤ ቅጽል ሲሆን፤ ቃሉ የቀድሞ አማርኛ ሲሆን አስተናባሪ (ብዙውን ጊዜ በግብዣ ወይም በቤተ መንግሥት በር ላይ በመቆም ሥርዐት የሚያስከብር ማለት ነው

አጋፋሪ፤ የድግስ አለቃ ፥ አስተናጋጅ ነገሥታት ግብር ሲያገቡ (ግብዣ ሲጋብዙ ፥ ድግስ ሲደግሱ) ወደ አዳራሹ (ወደ ድግሱ) እንዲገቡ የሚፈቅድ ፥ የማይገባቸውንም የሚከለክል፤ ከገቡም በኋላ እንደ የክብራቸውና እንደየማዕርጋቸው አንተ በዚህ ሁን ፥ አንተ በዚህ ተቀመጥ እያለ የሚያስቀምጥ፤ ኋላ የድግሱ ምግብና መጠጥ መታደል ሲጀምርም፤ እንጀራና ጠጅ አሳላፊዎችን የሚያዝና የሚቈጣጠር ትልቅ ሹም ነው

አጋፋሪ፤ የሚለው መጠሪያ በ17ኛወና በ18ኛው ክፍለ ዘመን የታወቀ የቤተ መንግሥት ሹም መጠሪያ ነው፡፡ ‹‹ህዱግ ራስ›› በመባል የሚታወቅም ነው፤ በቤተመንግሥት የሚካሄዱ ሥራዎችንና የፍርድ ሂደቶች ያስተባብራል፤ አንዳንዴ ደግሞ የክፍላተ ሃገር የፍርድ ሰጪ ሰዎች ስም ሆኖም ያገለግላል፤ የስሜን (ከጎንደር በስተሰሜን የሚገኝ ግዛት ነው) አስተዳደር የሚገዛ ሰው ደግሞ የሰሜን አጋፋሪ እየተባለም ይጠራል፤ (ለምሳሌም አፄ ሱስንዮስ ልጃቸውን ፋሲለደስን የስሜን አጋፋሪ ብለው ሹመወት ነበር፤ ይህ የስሜን አጋፋሪ የሚለው ሹመትም እስከ 20ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ ቆይቶ ነበር፡፡

ቡሄ
ቡሄ ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጸበት የነሐሴ 13 ቀን መጠሪያ ስሙ ነው የሚሉ ሊቃውንት እንዳሉ ሁሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ፤ ቡሄ የሚባለው፤ ከነሐሴ 13 በኋላ እስከ መስከረም 17 መስቀል ድረስ ሲሆን፤ በተለይም ይህ በዓል የሚታወቀው በሸዋና ወሎ /እስከ ጋይንት ጫፍ መጋጠሚያ) ድረስ ሲሆን፤ በዚህ ወቅትም ክርስትና አባት ለክርስትና ልጁ ተማሪ ከሆነ መጻሕፍትን (ዳዊት፣ …)፣ እንዲሁም አልባሳትን፣ በግና ሙክት ፍየልን የሚሰጥበት ነው፡፡ ሕፃናትና ወጣቱም ‹‹ቡሄ ፥ ሆ ….. ›› እያለ ይጨፍራል ፤ የሚሰጠውንም ሙክትና በግ እስከ መሰቅል ድረስ ሲያጠራቅም ከርሞ ለመስቀል ዕለት አርዶ ይበላል ፥ ደስታን ያደርጋል

ምንጭ፤ የቃል ትምህርት
/የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት/

@finotebrhan
@finotebrhan
@finotebrhan
467 views16:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 16:41:43 ቡሄ ማለት ምን ማለት ነው ? ችቦ ለምን እና መቼ ይበራል? ሙልሙል ልምን ይታደላል? በቡሄ ወቅት ጅራፍ ለምን ይጮሃል ?

#ቡሄ
ቡሄ ማለት ብራ፣ ብርሃን፣ ደማቅ ማለት ነው፡፡ ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት በዓል የሚዘከርበት እና ለበዓሉም ችቦ ስለሚበራ የብርሃን በዓል በማለት የቡሄ በዓል እንላለን፡፡ ወቅቱ የክረምት ፤ጨለማ አልፎ የብርሃን የሚወጣበት፤ ሰማይ ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚለወጥበት የመሸጋገሪያ ወቅት ነው፡፡ “ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት፤ ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት” እንዲሉ፡፡ በሌላ በኩልም “ቡኮ/ሊጥ” ተቦክቶ ዳቦ የሚጋገርበት “#ሙልሙል” የሚታደልበት በዓል በመሆኑ ቡሄ ተብሏል፡፡

#ጅራፍ
በደብረ ታቦር በዓል በትውፊታዊ መልኩ የሚታየው ምስጢር፤ በኢየሩሳሌም ስለሚሆነው የጌታችን ምስጢራዊ ሞቱ ነው፡፡ ጅራፍ መገመድ(መጥለፍ) እና ጅራፍ ማጮኽ ሁለት ዓይነት ምስጢር የያዘ ትውፊታዊ ተግባር ነው፡፡ የመጀመሪያው ግርፋቱንና ሞቱን እናስብበታለን፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ፤ድምፁን ስንሰማ የባሕርይ አባቱን የአብን ምስክርነት ቃል፤ እንደ ነጎድጓድ ድምፅ ያስታውሰናል፡፡
የጅራፍ ትውፊታዊነት /ውርስ/፣ መጽሐፋዊ ትምህርትና ምስጢር ጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ ለማድረግ ጨዋታውን በተራራማ አካባቢ፣ ከመኖሪያ ቤት ርቆና፣ በሜዳ ማድረጉ ጠቃሚ ነው፡፡ ጅራፍን #በርችት መቀየር የሚያመጣውን የምስጢር ተፋልሶ ብቻ መመልከት ከማኅበራዊ ጎጂ ገጽታው በላይ እንድናስወግደው ያስገድደናል

#ችቦ
ችቦ የጌታችንን ብርሃነ መለኮት መገለጥ የሚያመለክት ነው፡፡ በመሆኑም ችቦ ለኩሰን በዓሉን እናከብራለን፡፡ የዚህ ትውፊታዊ አመጣጥ በብርሃኑ ድምቀት የቀኑን መምሸት ያልተረዱ እረኞች በሜዳ ቀርተዋልና ወላጆች ከመንደር ችቦ ለኩሰው ልጆቻቸውን ፍለጋ ሔደዋልና ታሪኩን እያዘከርን በዓሉት እናከብራለን፡፡ የችቦው መንደድም ሌላ ትርጉም አለው፡፡ አንድ ምእመን ለሌላው ምእመን መካሪ አስተማሪ መሆኑን፣ መከራ እየተቀበለም አርአያ፣ ምሳሌ፣ ብርሃን መሆኑን ያሳያል፡፡ በሃይማኖትም አርአያ ምሳሌ ይሆንላቸዋል፡፡ ከዚህ ጋርም ተያይዘዞ ችቦ #በ13 ምሽት ይበራል ፣ብርሃኑ የተገለጠው በዚችው ዕለት ነውና ፡፡


#ሙልሙል
በችቦ ብርሃን ልጆቻቸውን ፍለጋ የወጡ ወላጆች ዳቦ ጋግረው ይዘውላቸው ወጥተዋል፡፡ ስጦታው ቤተሰባዊነትን፣ ፍቅርንና መተሳሰብን መግለጫ ነው፡፡ ወደ ቤታችን “ ቡሄ ” እያሉ ለሚመጡ አዳጊዎችም፤ ዘምረው እንዳበቁ የሚሰጥ “ሙልሙል” ዳቦ አለ፡፡ ሕፃናቱም ሊዘምሩ ሲመጡ ዳቦ መስጠት ልማዳዊ ብቻ አይደለም፡፡ ሕፃናቱ
የደቀመዛሙርት ምሳሌ ናቸው፡፡ መዝሙራቸው ደግሞ ሐዋርያት “የምሥራች” ይዘው የመምጣታቸው ምሳሌ ነው፡፡ ሐዋርያት በገቡበት አገር አስተምረው አጥምቀው የጸጋ ልጅነትን አሰጥተው በረከት አድለው እንደሚሔዱም፣ ልጆችም ዘምረው፣ አመስግነው፣ መርቀው “ውለዱ ክበዱ፣ ሀብት አግኙ፣ የመንግሥተ ሰማያት ወራሾች ያድርጋችሁ
….” ይላሉ
በአጠቃላይ በዓለ ደብረ ታቦር ከእነዚህ ምስክር ካላቸው ትምህርቶቹ፣ ምሥጢር ከሚራቀቅባቸው ትርጓሜያቱና ከትውልድ ትውልድ በቅብብል በተላለፈው ቅዱስ ትውፊት ጋር ሃይማኖታዊ ባሕል ሆኖ ሊቀጥል ይገባዋል፡፡ ይህን ማድረግ የሚቻለው ግን አዳጊዎች ሃይማኖታዊ ትውፊቱን ይዘው እንዲያድጉ ጥቆማ በመስጠት፣ ግጥም በመግጠምና
ምሥጢሩን በማብራራት የመጀመሪያዎቹ ባለድርሻዎች ወላጆች ናቸው፡፡ አንዳንድ ጊዜ የሚሰሙ ግጥሞች ስድብ፣ ፌዝና ሥላቅ የተቀላቀለባቸው ይሆናሉ፡፡ ሕፃናቱም ዝማሬውን ሲጀምሩ “ከሰጡን እንነሣ ከነሱን እናርዳ” ብለው ይጀምሩታል፡፡ ከሰጡን እንመርቃለን ካልሰጡን እንራገማለን በማለት፡፡ አሳሳቢው ነገር ደግሞ ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን ወደ ገንዘብ ማግኛነት የቀየሩ ሁኔታዎች መታየታቸው ነው፡፡

ዳቦ /ሙልሙል/ ትምህርቱንም፣ ምስጢሩንም፣ ትውፊቱንም በአግባቡ ልንጠቀምበት ይገባል ከዚም ጋር ተያይዞ ሰንበት ት/ት ቤታችን ለበርካታ ዓመታት ሲወረድ የመጣውን የዝማሬ ሥርዓት ለአጥብያው ምእምን በየቤቱ በመሄድ የብሄን ዝማሬ ከነሥርዓቱ በመዘመር አገልግሎት ይሰጣል ፤የደብር ታቦርን በዓል በተመለከትም የወረቀት ጽሑፎችን ይበትናል በዝማሬ መኃል ያድላል ፡፡
ቤተክርስቲያን የምሥጢር ግምጃ ቤት ናት፤ የምታከናውነውን ሁሉ ከበቂ መረጃ ጋር ነው ተግባራዊ የምታደርገው

@finotebrhan
@finotebrhan
@finotebrhan
408 viewsedited  13:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 07:07:32
#ፆመ_ፍልሰታ
ፍልሰታ ለማርያም

ነሐሴ 12

ሚካኤል ሉቀ መላእክት ሰአል በእንቲአነ ወቅዱስ
ገብርኤል አዕርግ ጸሎተነ፡፡
#አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ


join us @finotebrhan
376 viewsedited  04:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 22:01:00 #ክርስቲያናዊ_ሥነ_ምግባር

ክፍል_2

#አታምልክ

ማምለክ ሲባል እምነትን ተስፋን ፍቅርን በአምላክ ላይ መጣል ነው ።1ሰው እምነቱን ተስፋውን ፍቅሩን ከእግዚአብሔር ላይ አንስቶ በሌሎች አማልክት ላይ ሲጥል ነው ሌላ አምላክ አመለከ የሚባለው ። #አምልኮት በተግባር የሚውለው በሚከተሉት ነገሮች ነው

#1በስግደት #2ጸሎት #3መስዋዕት #4ውዳሴ #5መገዛት #6ፍርሃት ወዘተ ስለዚህ እነዚህን ነገሮች ከእግዚአብሔር ውጪ ለሌላ ነገር ብንሰጣቸው ሌላ አመለክን ማለት ነው ። ይህን ህግ የሚያፈርሱ ሰዎች ብዙ ዓይነት በደል ይበድላሉ ። ይኸውም #1የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር የተባለውን ትዕዛዝ ይለውጣሉ

#2ከቤተክርስቲያን አንድነት ውጭ ይሆናሉ #3ተስፋ ቢስ ሁሉ የጨለመባቸው ሆነው ይገኛሉ ። #ሌሎች_አማልክት_የተባሉት ፦ ሰው እንደ እግዚአብሔር የሚያያቸውና ብቸኛውን የእግዚአብሔርን ባሕርይ የሚሰጣቸው ነገሮች ሁሉ አምላክ ሊሆኑበት ይችላሉ ። እነሱም ፦ #1 ገንዘብ ማቴ 6:24 #2የሰው ሃይል ኤር 17:5 #3የሰው ጥበብ እውቀት ኤር 9:23 #4ሆድ ራስ ወዳድነት #5 የምንታመንባቸው ሰዎች (ባለ ሃብት ባለ ስልጣን ) #6አባትና እናት #7ተድላ ደስታ #8የተቀረፀ ምስል ዘፀ 20:4 አምልኮ ከእግዚአብሔር ውጪ ለማንም አይሰጥም ። አክብሮትና የጸጋ ስግደት ግን ለቅዱሳን መላዕክት እና ለቅዱሳን ሁሉ ልናደርግ ይገባል

መጽሐፍ ቅዱስ ቅዱሳንን #አማልክት ይላቸዋል ። ለምሳሌ ሙሴን ለፈርኦን አምላክ አድርጌሃለው በማለት እግዚአብሔር ነግሮታል ። በቤተክርስቲያናችን ቅዱሳንን እናከብራለን ይህ ከትዕዛዙ ወይም ከህጉ ጋር አይጋጭም የእግዚአብሔርን አምልኮትና አክብሮት ለቅዱሳን አንሰጥምና ።እንዲያውም ለእነርሱ የምንሰጠው ክብር እግዚአብሔርን ማክበር ስለሆነ በብዙ ምስጋና ለእግዚአብሔር እናቀርባለን

Comment @finotebrhan

@finotebrhan
@finotebrhan
@finotebrhan
373 views19:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ