Get Mystery Box with random crypto!

#ብፁዕ_ወቅዱስ_ፓትርያርክ_አቡነ_ማትያስ_በውጭ_ሲከታተሉት_የቆዩትን_ሕክምና_አጠናቅቀው_ጳጉሜን_1_ | ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት

#ብፁዕ_ወቅዱስ_ፓትርያርክ_አቡነ_ማትያስ_በውጭ_ሲከታተሉት_የቆዩትን_ሕክምና_አጠናቅቀው_ጳጉሜን_1_ቀን_2014 ዓ.ም ወደ ሀገረ ኢትዮጵያ ይገባሉ !!!
++++++++++++++++++++++++++++++++++++
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በሀገረ አሜሪካ ሲከታተሉት የቆዩትን ሕክምና አጠናቅቀው የፊታችን ማክሰኞ ጳጉሜን 1 ቀን 2014 ዓ.ም ወደ ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ እንደሚመለሱ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት አስታውቋል።

ቅዱስነታቸው ከሐምሌ 19 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ በቅዱስ ሲኖዶስ መልካም ፈቃድ ካለባቸው የጤና እክል አኳያ በአሜሪካ ሕክምናቸውን ለመከታተል ጉዞ ማድረጋቸው ይታወሳል።

የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ጤንነት በመልካም ሁኔታ ላይ የሚገኝ ሲሆን ከጳጉሜን 1 ቀን ጀምሮ ወደ መንበራቸው እንደሚመለሱ ታውቋል።
#ምንጭ
ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል
እውነተኛ የተዋሕዶ ድምፅ