Get Mystery Box with random crypto!

❖ አንድ ' ግዩር ' እንዲህ ይመክራል ❖ ሥለ እግዚአብሔር ብለን ሰውን እንውደድ እንጅ ስለ ሰው | ✞ ፍኖተ ጽድቅ ✞

❖ አንድ " ግዩር " እንዲህ ይመክራል ❖

ሥለ እግዚአብሔር ብለን ሰውን እንውደድ እንጅ ስለ ሰው ብለን እግዚአብሔርን መውደድ አይገባንም። በእግዚአብሔር ፊት ሰውን መውደድህን ይገለጥልህ እንጅ በሰው ፊት የእግዚአብሔር ወዳጅ ለመምሰል ብለህ የምትኖር አትሁን። ለሰዎች ብለህ እንደወደድከው ለሰዎች ብለህ ልትጠላው ትችላለህ እና።
----------------------------------------------------------------
የእግዚአብሔር ሰው መሆን ማለት እግዚአብሔርን መመገብ እንጅ እግዚአብሔርን ማወቅ አይደለም። ለመዳን ብለህ እወቅ እንጅ በእውቀትህ የምትድን አይምሰልህ። የማታውቀውን የምታውቀው ልትኖረው እንጅ እውቀቱ በክርስቶስ ቀኝ ሊያቆምህ አይምሰልህ። በጎ ነገርን ያወቅሃት ዕለት ብቻ ደስ አይበልህ፥ የሠራሃት ዕለት እንጅ፥ በመሥራትህም አትመካ አልፈጸምካትምና። ከእግዚአብሔር ያወቅሃትን መልካም ነገር ወዲያው ሥራት፥ እየሠራሃት ያለችህን መልካም ነገር አትልቀቃት። እየኖርክ ተማር እንጅ እየተማርክ ብቻ ዘመንህን እንዳትፈጽም ተጠንንቀቅ። ያለ ዕውቀት ብትኖር ከፍርድ የምታመልጥ አይደለምና መቼም ቢሆን ከቤተክርስቲያን ጉባዔያት አትታጣ፥ በማወቅህ ፍርድ አይቀርልህምና ያወቅኸውን ፈጥነህ ሥራ።

ብቻየን ለፋሁበት ብለህ ገንዘብህን ብቻህን አትጨርሰው። ከምታገኘው ሁሉ ለመድኀኔዓለም ድርሻ አስቀምጥ። የለመነህን ሰው አትመርምረው ቢቻልህ ስጠው ባይቻልህ እዘንለት እንጅ። ለስንፍናህ ሁሉ ምክንያት አታብጅለት። መልካሙን ነገርም ዛሬ ሥራው፥ ክፉውን ነገርም ዛሬ ተናዘዘው። #እያንዳንዱ_የጊዜ_ሽርፍራፊ_የገነት_የሲዖል_ሰው_ለመሆንህ_ዋጋ_እንዳለው_እወቅ።


#ይቆየን
መልካም የሆነ እግዚአብሔር ለመልካም የሚሳብ መልካምን የሚያደርግ በመልካሞ የሚጸና በጎ ሕሊና ይስጠን!!!

✞ መልካም እለተ ሰንበት ✞

ሼር በማድረግ ለሌሎች ያካፍሉ!!
@finote_tsidk
@finote_tsidk