Get Mystery Box with random crypto!

#የርቀት_ፍቅር ፍቅረኛዬን አንድ ጥያቄ ጠየቅኳት፡፡ እኔ ፡ ይህንን የርቀት ግንኙነታችንን | ፍልስፍና ከፈላስፎች💆

#የርቀት_ፍቅር

ፍቅረኛዬን አንድ ጥያቄ ጠየቅኳት፡፡


እኔ ፡ ይህንን የርቀት ግንኙነታችንን ምን ብናደርገዉ ይሻላል?

እሷ፡ እኔንጃ! እስኪ አንተ ንገረኝ?

እኔ፡ እኔንጃ! አንቺ ንገሪኝ እንጂ?

እሷ፡ በቃ ተወዉ!

እኔ፡ አንቺ ራስሽ ተይዉ!

እሷ፡ እንደዚህ ተራርቀን እንኳን መጨቃጨቅ ትፈልጋለህ አይደል?

እኔ፡ እንደዚህ ስንሆን ደስ ይለኛል

እሷ፡ ኤጭ!

እኔ፡ እወድሻለሁ! መቼ ነዉ የምትመጪዉ?

እሷ፡ ፍቅር በስልክ ሽቦ ያምርብናል...የምን መገናኘት ነዉ!

እኔ፡ እሺ

እሷ፡ ቅር አለህ ?

እኔ፡ አዎ!

እሷ፡ አይዞህ! አሁንማ ከ 700 ኪሎ ሜትር ወደ 200 ኪሎ ሜትር ቀርቤልሃለሁ

እኔ፡ ማለት?

እሷ፡ በቃ የስራ ቦታዉን ወደሌላ ከተማ ሊቀይሩኝ ነዉ ስለዚህ መምጣት ትችላለህ

እኔ፡ እንዴ! ያምራል በናትሽ!! ዋዉ እልልልልል!

እሷ፡ ግን ሌላ ባል እዚህ ሳላገኝ አልቀርም፡፡ ልፈነግልህ እያሰብኩ ነዉ፡፡ እራስህን አዘጋጅ

እኔ፡ አንቺንም ባልሽንም በጥይት ገድዬ እጄን ለፖሊስ እሰጣለሁ!

እሷ፡ ምን አይነቱ ጨካኝ ነዉ!

እኔ፡ እኔም ሌላ ሚስት እዚህ እያበሰልኩልሽ ነዉ... ፎንቃ ከጠለፈኝ አንቺን መካዴ የማይቀር ነዉ!

እሷ፡ ሞቼ ነዉ ቆሜ! አንገቷን በዘነዘና አንክቻት ወህኒ እወርዳታለሁ እንጂ አንተማ የኔ ነህ! የኔ መሆን መብት ሳይሆን ግዴታህ ነዉ!

እኔ፡ እሺ ማር

እሷ፡ በል ቀን ላይ ከደወልክ ላታገኘኝ ትችላለህ አዲሱ ባሌን ኑሮ እያለማመድኩት ነዉ

እኔ፡ እሺ በቃ ባልሽንም ሳሚልኝ፡፡ ሚስቴ እየጠራችኝ ነዉ በቃ ቻዎ

እሷ፡ አፈቅርሃለሁ፡፡ ቻዉ!!


https://t.me/filsifina_kefelasfoch

https://t.me/filsifina_kefelasfoch