Get Mystery Box with random crypto!

#ምሬት ምሬት ሲበዛ ሰዉ መኖር ይደክመዋል፡፡ ፍቅር ሲበዛ ደግሞ መኖር መኖር ያሰኘዋል... | ፍልስፍና ከፈላስፎች💆

#ምሬት

ምሬት ሲበዛ ሰዉ መኖር ይደክመዋል፡፡ ፍቅር ሲበዛ ደግሞ መኖር መኖር ያሰኘዋል...ነገን ይናፍቃል፡፡ በዚህ እልህ አስጨራሽ የምድር ኑሮ ይብዛም ይነስም ምሬቶቻችን አያሌ ናቸዉ፡፡

ከእንጀራና ወጥ ጀምሮ እስከ ሃገር ብዙ ነውጦች በልባችን ይከሰታሉ፡፡ ልባችን ብዙ ሲበጠበጥና ማረፍ ሲሳነዉ እዚህም እዚያም እያለ ያስቸግራል...ልብ ማስቸገር ከጀመረ ደግሞ እንደህፀን ልጅ በል ተዉ! ብለን በቀላሉ አንገታዉም፡፡

ልብ አሸባሪ ነዉ...በሚያየዉና በሚሰማዉ እያንዳንዱ ነገር ይሸበራል...ቀን እየገፋ ሲመጣ በህይወት የሚሰለችና ቶሎ የሚመረር ልብ በየቦታዉ እየበዛና፣ እየጨመረ፣ እየፈላ ይመጣል፡፡

የምሬት ዋናዉ መድሃኒት ብዙ ነገሮችን ማሳለፍ ይመስለኛል፡፡ ባየነዉና በሰማነዉ ነገር ሁሉ ልባችን እየተራገመና ደማችን ከፍ እያለ ከሄደ ብዙ የህይወት አቅጣጫችንን ማበላሸት እንጀምራለን፡፡

እራሳችን ያወላገድነዉን ኑሮ ደግሞ ማንም ሊያቃናልን አይችልም፡፡ አንድ ሰዉ እንደተናገረዉ “መንገድ ላይ በሚጮህብህ ዉሻ ላይ ሁሉ ድንጋይህን አትወርውር” እንዳለዉ በያንዳንዱ ቅፅበት ያለንን ማንነት አላፊ አግዳሚዉ ባወራዉ ላይ ሁሉ መሳተፍ እፈልጋለሁ ካልን ትልቅ ኪሳራ ዉስጥ እንገባለን፡፡

እንደኛ እንጀራ ለመብላት ደፋ ቀና በሚል ህዝብ መካከል ምሬቶቻችንን ብንዘረግፈዉ አዉርተን ዝንት አለም አንጨርሰዉም፣ ነገር ግን መልካሙን፣ ተስፋ የሚሰጥበትን፣ ብሩሁን ከዚህ ጨለማ ዉስጥ ሻማችንን አብርተን እንፈልግ!

#እኔው_ነኝ_ወንድማችሁ.!

https://t.me/filsifina_kefelasfoch
https://t.me/filsifina_kefelasfoch
https://t.me/filsifina_kefelasfoch
https://t.me/filsifina_kefelasfoch