2022-06-15 01:19:04
የዕለቱ መልእክት
(ስለ ሰዎች.........
ከሰዎች ጋር መኖር ምን አልባት ከእንስሶች ጋር ከመኖር በእጅጉ የከበደ ይሆናል።
በጣም አሳዛኙ ሰው ሳይለወጥ የቀረ ነገር ግን በተለወጡት ላይ ትችት የሚያቀርብ ሰው ነው።
ስቆ ሚቀበልህ አቆላምጦ ሚጠራህ ሁሉ አክባሪህ አይደለም እልፍ እንዳልክ ብዙ ስም ሊያወጣልህ ዝግጁ ነው።
ሰዎች በየሔዱበት ስላንተ ካወሩ ወይ ይወዱሀል አልያም ይቀኑበሀል ወይ ደግሞ ይጠሉሀል። እውነታው ግን አንተ ሥራ ላይ ነህ።
ሰዎች በጨዋታ መካከል የውስጣቸውን ጣል አረገው ሊነኩህ ይፈልጋሉ። ያን ጊዜ አንተ ስቀህ እለፈው ነገር ግን ላንተ ያላቸውን ግምት መዝገበው። መስመር ለማበጀት ይረደሀል።
አበላሹት ከሚሉት ይልቅ እናስተካክለው ከሚሉት ጋር ወዳጅ ሁን። ጨለምተኞች ብርሀንን በጸሐይ ብቻ ነው የሚያቁት።
ለራሱ ትልቅ ግምት ካለው እና ለክብሩ ከሚጨነቅ ሰው ጋር ወዳጅ መሆን ማለት ጎመን በልቶ ተራራ እንደመውጣት ከባድ ነው። ከጓደኝነት ይልቅ ክብሩ ያሳስበዋልና።
ከአሰመሳይ አክባሪዎች ጋር ለደቂቃዎች ቆመህ አውራ ነገር ግን ሰፊ ጊዜ አትስጣቸው። ምክንያቱም እንዲህ ያሉ ሰዎች በንግግርህ ሊመዝኑህ ይፈልጋሉ።
እያዩህ ተራራ እስክታክል ድረስ በተሰጠህ ነገር ላይ ድከም። አንተ እየወጣህ ተቺዎቹህ ደግሞ እየወረዱ መንገድ ላይ ታገኛቸዋለህ።
በጣም የሚያስደንቁኝ ሰዎች ያለመንም ነቀፌታ ሁሉንም እኩል የሚወዱ ሰዎች ናቸው በሕይወታቸው ማይግባቡት እንጂ የሚጠሉት የላቸውም። እንዲህ ያሉ ሰዎች ምን አልባት በሕይወት ዘመንህ አንድ ጊዜ ሊያጋጥሙህ ይችላሉ።
@fikireskemekabirtireka
207 viewsedited 22:19