Get Mystery Box with random crypto!

Fikir Eske Mekabir

የቴሌግራም ቻናል አርማ fikireskemekabirtireka — Fikir Eske Mekabir F
የቴሌግራም ቻናል አርማ fikireskemekabirtireka — Fikir Eske Mekabir
የሰርጥ አድራሻ: @fikireskemekabirtireka
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 849
የሰርጥ መግለጫ

ke teleyayu channaloch lay yetewesedu
@fikireskemekabirtireka

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-08 23:16:43
74 views20:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 21:55:35 Amelewerk Design Order now https://t.me/ameleddesign
188 views18:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 21:31:52 Amelewerk Design
Order now
https://t.me/ameleddesign
167 views18:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 20:41:42 Fikir Eske Mekabir pinned « ሰሞንኛ ጨዋታ (በእውቀቱ ስዩም) . . . ትናንት ቀለል ያለ ራት ለመብላት ፈለግሁ ፤ እናም” ባጫ ህንጻ “ ውስጥ በሚገኘው የ” አማራ ባንክ” ቅርንጫፍ ጎራ ብየ በርከት ያሉ ሁለት መቶ ብሮችን ሸመጠጥሁ፤ ምግብ ቤት ገብቼ ፥ ምግቡ አላግባብ ውድ ከሆነብኝ ሂሳብ ለማካካስ ብዙ ነገሮች እጠቀማለሁ፤ ለምሳሌ ሬስት ሩም ገብቼ ለረጅም ጊዜ እቆያለሁ፤ ባጭሩ ፥ሬስት ሩምን ርስት ሩም አደርገዋለሁ፤ ያን…»
17:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 20:41:17 ሰሞንኛ ጨዋታ

(በእውቀቱ ስዩም)
.
.
.
ትናንት ቀለል ያለ ራት ለመብላት ፈለግሁ ፤ እናም” ባጫ ህንጻ “ ውስጥ
በሚገኘው የ” አማራ ባንክ” ቅርንጫፍ ጎራ ብየ በርከት ያሉ ሁለት መቶ ብሮችን
ሸመጠጥሁ፤ ምግብ ቤት ገብቼ ፥ ምግቡ አላግባብ ውድ ከሆነብኝ ሂሳብ
ለማካካስ ብዙ ነገሮች እጠቀማለሁ፤ ለምሳሌ ሬስት ሩም ገብቼ ለረጅም ጊዜ
እቆያለሁ፤ ባጭሩ ፥ሬስት ሩምን ርስት ሩም አደርገዋለሁ፤ ያን ቀን ወደ ቤተ-ሰገራ
ወሽንቤቱ ስራመድ መብራት ድርግምም አለ፤ ከግማሽ ሰአት የፈጀ ዘለግ ያለ
ሽንት ሸንቸ ሳበቃ እያፍዋጨሁ ስወጣ የጽዳት ሰራተኛዋ ፥

"ሴቶች ሽንት ቤት ውስጥ መሽናትህ የሚያሳፍር ነው “ አለችኝ ::
“ በዚህ ጨለማ ፥ ኪችን ውስጥ ባለመሽናቴ ልታደንቂኝ ይገባል “ ስላት ፈገግ
አለችልኝ ፤ (ግን ጨለማ ከሆነ ፈገግታዋ እንዴት ሊታየኝ ይችላል ? ሰው ምን
ይለኛል አይባልም? )
ባጭር ጊዜ የሌለ ተመቻቸን ፤መጨረሻ ላይ ቁጥርሽ ስንት ነው ?” ስላት፤ “
የጫማየ ወይስ የወገቤ” ብላ ስለመለሰችልኝ አጥብቆ ደበረኝ!
ድብርቴን ለማባረር የሚከተሉትን ሁለት ቀደዳዎች አስታወስኩ፥
ጉዋደኛየ ባለፈው ለአለቃው ‘ የሞተር መኪና አደጋ ስለደረሰብኝ ዛሬ መምጣት
አልችልም “ ብሎ ለአለቃው መልክት ሰደደለት፤ አለቅየው “ ይገርማል፤ ዛሬ
በጀት መዝጊያ ስለተቃረበ በመስርያ ቤታችን ውስጥ ሰርፕራይዝ ፓርቲ
አዘጋጅተን ነበር ፤ ለሰራተኞች ዳጎስ ያለ የገንዘብ ስጦታም አሰናድተናል፤
እንዲሁም ዳጎስ ዳጎስ ያለ መቀመጫ ያላቸው ሴቶች ፓርቲውን ያደምቁታል ፤
በዚህ ዝግጅት ተሳታፊ ባለመሆንህ የተሰማኝ ደስታ ማለቴ ሀዘን ወሰን የለውም
፤ ለማንኛውም ነፍስ ይማር፤ I mean እግዜር ይማርህ” ብሎ መለሰለት፤
ግብዣው በመጦፍ ላይ እያለ ረፍት የጠየቀው ጉዋደኛየ እንደቆሰለ አርበኛ
በሁለት ወንድሞቹ ግራናቀኝ ተደግፎ ከች አለ፤
አለቅየው እንዳየው ምን አለ ?
“ እያመመው መጣ! “
በዙ ጊዜ የሰይፉ ሾውን ስመለከት የራሴን ፈጠራ ነስነስ አደርግበታለሁ፤ ባለፈው
ሰይፉ የሀይሌ ገብረስላሴን ፊት ይዞ የተፈጠረ ሰውየ አቀረበ፤ ሰውየው ሀይሌን
እንዳገኘው “ ወንድሜ ! ብሎ እንደበረኛ ተጠመጠመበት ፥
ሀይሌ;- ወል እንግድ ! በአርባ ደቂቃ ውስጥ ለሚ ኩራ ደርሰህ ከተመለስህ
ወንድሜ መሆንህን እቀበላለሁ”
ሰውየው;- “ እሺ! አውቶቢስ ልያዝ ወይስ ራይድ ትጠሩልኛላችሁ? “
በመጨረሻ የዲኤን ኤ ምርመራ ተደርጎ ውጤቱ መጣ
;
ሰውየው ;- በምርመራው መሰረት ወንድምህ መሆኔ ተረጋግጧል ፥ የሆነ ነገር
አታካፍለኝም?”
ሀይልሽ፤- ነገ ቢሮ ብቅ በልና የህይወት ልምዴን አካፍልሀለሁ”

Share


@fikireskemekabirtireka
173 viewsedited  17:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 01:28:33 Fikir Eske Mekabir pinned «ፍቅር በዚያ ወራት  ክፍል 2 (ሚካኤል .አ) የክፍላችን በር ጋር እስክደርስ የነበረኝ በራስ መተማመን ስሜት እምን ጉድጓድ እንደገባ አላውቅም። ዶክተር ዛኪን ሳየው ልቤ በአፌ ልትወጣ ታገለችኝ።  እንደ ልማዱ ፅድት ብሎ መጥቷል። (በጣም የሚገርመኝ ነገር ጫማው ላይ እንኳ ብናኝ አቧራ የለምኮ ) ... ለነገሩ ከቤቱ ወጥቶ በኔ ልብ ላይ ተራምዶ ክፍል እየደረሰ በየት በኩል አቧራ ሊነካው ይችላል? …»
22:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 01:28:15 ፍቅር በዚያ ወራት
(ሚካኤል.አ)
#ክፍል 3
ከንፈሮቹን ልጎርሳቸው ተጠጋሁት.. ወደ ከናፍሩ ስጠጋ የውብ ትንፋሹ መዓዛ አወደኝ ። የተቀባው ሽቶ በአፉ ከሚያላምጠው ሜንት ማስቲካ ጋር ሲዳበል የገነት መግቢያው የሱ መዓዛ ነው ቢሉኝ ውሸት ነው አልልም።
ወድያው "አይዞሽ ውዴ! " የሚል ድምፅ ሰማሁ ።
ሺት !
የፈራኋት ጣውንቴ መጣች ። የነጃት ጥላቻዬ አስራ አንድ በመቶ ሲያድግ ተሰማኝ (ፖለቲካ አይደለም !)... በሷ ቤት አንድ ቀን ኒቃቧ ከፊቷ ሲወርድ ቀድሜ ስለደረስኩላት በችግሬ ጊዜ ቀድማኝ መድረሷ ነው። ችግሬ እሷ እንደሆነች ብታውቅ ስል ተመኘሁ።
"ነጅዬ እባክሽ handle " አድርጊያት ብሎ ዶክተር ወደ ክፍሉ ገባ። ነጅዬ ሲላት ደግሞ ነብር ሆንኩኝ... ከየት መጣ ያልተባለ ቀዝቃዛ ውሀ ፊቴ ላይ ከነበለችብኝ።
የዛክዬን ከናፍር ከመጉረስ ስታግደኝ ነው መቀዝቀዝ የጀመርኩት ።
"ተረጋጊ እንጅ ፀጉሬን ..." ብዬ ጮህኩባት ።
እሷ እንኳን ልትደነግጥ ወገቤ ስር ገብታ አነሳችኝ ። በጥፊ ጉንጯን ባቀላው ስሜቴ ነው ።
እሷና ጓደኞቿ አንከብክበው ጥላ ያላት አፀደ ስር አኖሩኝ ። ንፋሱ ከውሀው ቅዝቃዜ ጋር ተዳብሎ በረደኝ ።
ጥርሶቼ በእልህና ቅዝቃዜ ተንገራገጩ።
"አይዞሽ ንፁህ.. . "
ራስሽ አይዞሽ ብዬ ልመልስላት ይሆን?
አይኖቿ የሚስቁለት.. .ነፍሷ የምትፈነጥዝለት ዛኪን ልቀማት መሆኑን ማን ሹክ ባላት ?
...
ከዛ ክስተት በኋላ ወደ መደበቂያዬ ሮጥኩ !
ክለብ.. .
ጠጣሁ.. . አምሮቴ ንቅል እስኪልልኝ ጠጣሁ ።
ሞቅ እንዳለኝ ያየ አንድ ጎረምሳ የሚያጨሰውን ሺሻ ትቶ ወደኔ አቅጣጫ መጣ።
"ቆንጆ ነሽ" አለኝ።
ዝም!
"ምነው የከፋሽ ነገር አለ ?"
ዝም!
ምናለ ከዛኪ በስተቀር የዓለም ወንዶች ሁሉ ባያናግሩኝ? አባቴና ወንድሜ እንኳ እንዲያናግሩኝ የምፈልግ አይመስለኝም።
አሁን ይሄ የሰማይ ስባሪ የሚያህል ወደል እንዴት ያናግረኛል ?
ጠጪ ...አጫሽ ወንድ ነው ያስጠላኝ።
ያዘነ ለመምሰል ሞከረ !
ውሸት.. . አይኖቹ ውሸት! ...ሳቁ ውሸት...ንግግሩ ውሸት ...
ቆንጆ ነሽ ሲለኝ አመሰግናለሁ ቢለኝ ...አብረን እንፍታታ ብሎ ይቀጥላል ።
እሺ ብለው እኔ ጋር ለማስመሰል ውስኪ ያወርዳል።
ምድር ላይ ያፈቀራት ሴት እኔ ብቻ የሆንኩኝ ያህል አስመስሎ ይንከባከበኛል...ከዛ መተኛት !
አንዴ ጭኔ ስር ገብቶ በለሴን ከቀጠፈ እኮ በነጋታው ስልክ አያነሳልኝም።
ይሄ ህይወት ሰልችቶኛል.. . ነፍሴ ዛኪ ጉያ ገብታ መሸሸግ ትፈልጋለች ።
ሀጥያቴ የሚጠራው በሱ ላቦት ነው።
"ማሬ አመልሽም ?"
"ማርህን ጎዣም ፈልግ !" አንባረቅሁበት ። ከመቅፅበት ከስሬ በሮ ጠፋ ። ፈሪ ወንድ !
አሁን ይሄ ነው የኔን ጀንታላ ዛክ የሚተካልኝ?
ሌላ ብስጭት.. .
መጠጥ.. . ሻት ...
በቃ ራሴን አጣሁት ። የክለቡ ብልጭ ድርግም መብራት ...መጠጡ.. .ሙዚቃው ናላዬን አዞረኝ ።
ምንም ሆንኩ !
እንደምንም ተንገዳግጄ ሰው መሀል ገብቼ ጨፈርኩ።
እንደ ልማዴ የሰው ሆንኩ...ሳቄ ...ደስታዬ ሁሉ የሰው ሊሆኑ ራሳቸውን ከመቃብር ቀስቅሰው ተነሱ።
ከሩቅ ለሚያየኝ ሰው ደስተኛ ነኝ...ነፈዝኩ...ነጎድኩ ...ብንንንንንንንንንን....
አላልኩም ?
ስጠጣ የሰው ነኝ ብዬ አልነበረምን ?
ማልዶ ስነሳ ራሴን ከሰው ጋር አገኘሁት ።
አንሶላዬን ገልጬ ተስፈንጥሬ ተነሳሁ ።
አብሮኝ ያደረው ወንድ እንደ ጆንያ ተንደባሎ ፊቱን ወደኔ አዞረ?
እንዴ?
ይሄ የኢኮኖሚክስ መምህሩ እዘዝ ነው እንዴ?
ዛኪ የነፍስና ገላዬን መርከስ አይቶ የጠላኝ መሰለኝ...
"አንተ ማነህ ?"
.
(ይቀጥላል)

@fikireskemekabirtireka
304 viewsedited  22:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-17 00:21:58 ፍቅር በዚያ ወራት 

ክፍል 2

(ሚካኤል .አ)

የክፍላችን በር ጋር እስክደርስ የነበረኝ በራስ መተማመን ስሜት እምን ጉድጓድ እንደገባ አላውቅም። ዶክተር ዛኪን ሳየው ልቤ በአፌ ልትወጣ ታገለችኝ። 

እንደ ልማዱ ፅድት ብሎ መጥቷል። (በጣም የሚገርመኝ ነገር ጫማው ላይ እንኳ ብናኝ አቧራ የለምኮ ) ... ለነገሩ ከቤቱ ወጥቶ በኔ ልብ ላይ ተራምዶ ክፍል እየደረሰ በየት በኩል አቧራ ሊነካው ይችላል?

በማስተማሩ በፊት ሁላችንንም በስስት እያየ ሰላምታ ይሰጠናል...ጨዋታ አዋቂ ነው። 

ቢያንስ ፊት ለፊት ከሚቀመጡ አንድ ሁለት ልጆች ጋር ሳይጨዋወት ወደ ማስተማሩ አይገባም። ሲስቅ ከልቡ ነው ... ነጭ ባይሆንም ፈዛዛ ሽሮ መልክ ያላቸው ስድር ጥርሶች አሉት ። ድዱ በእጅ ሳይወቀር ተፈጥሮ አሽሞንሙና ሰርታዋለች ። 

እሱ ይስቃል.. .ልቤ ታለቅሳለች ። ስድር ጥርሶቹ የኔን ነፍስ የሚያጠፋባቸው ድርድር ጥይቶች መሆናቸውን ማን በነገረው ?

ፈገግታው ደስም ይለኛል.. .ያስቀናኛልም። 

በተለይ ለነጃት ሲስቅላት እነዳለሁ ።

ደግነቱ እንደዚህ አይነት አክራሪ ክርስትያን ሙስሊሟን ነጃት ሊወድ ስለማይችል ለራሴ ቅናት መፅናኛ አላጣም።

ይሁንና ግን ይሄን አስቤ እንኳ ልቤ እርፍ አትልልኝም...ያቺ ጣውንቴ አይኖቿ ያምራሉ ...ሰውነቷ ከኔ ይበልጥ የሚስቡ ይመስለኛል...ብዙ ጊዜ ዛኪ አቀርቅሮ ትምህርት ሲተነትን እነዛ ሎጋ የእግር ጣቶቿን እያየ ስለሚመስለኝ እበሽቃለሁ ።

የሆነ ቀን ላይ የፊት ኒቃቧ ሲወርድ መልኳን አየሁት ...ለክፋቱ ደግሞ ዶክተር ፊትለፊታችን ነው። መልኳን ሲያይ መደንገጡን አይቼበታለሁ ...(ድንገትም ስለማፈቅረው መስሎኝም ሊሆን ይችላል )

ከሁሉም ተማሪ በላይ ዘልዬ ፊቷን የሸፈንኩላት እኔ ነኝ። ሙስሊም ጓደኞቿ አላህ ይባርክሽ ብለው መረቁኝ... (ይሄን ያደረኩት ከነጃት የውበት ፆር ዛኪዬን ለመደበቅ መሆኑን የሚያውቀው አላህ ሲባርከኝ እኮ ታየኝ !)

በቃ ከዛን ቀን በኋላ አይኖቼ ሁለቱንም ይከታተላቸዋል። ለሴት ልጅ ውበት ግድ አልባው ዛኪ ለነጃት ግን የተመየ ስሜት ያሳደረ ይመስለኛል....። ክፍል ውስጥ ፊትለፊት ስለምትቀመጥ ሳያሳስቃት ምንም ነገር አይጀምርም። 

ደግሞ ሌላ የሚያበሽቀኝ ነገር የሷ ሳቅ ነው። ስታየው ገና አይኖቿ ይበራሉ.. .ትንሽ ያወራት ጊዜማ ነፍስያዋ ትዘላለች) 

በዚህ ቅናት ተነሳስቼ እኔም እንደሌሎች ቸካይ ተማሪዎች ፊትለፊት ሄጄ ተቀመጥኩ ።

ብዙ አልምጥ ጓደኞቼ ተሳለቁብኝ። ትምህርት እንደሚደብረኝ ብቻ ሳይሆን እኔም ትምህርትን እንደምደብረው ሁሉም በዙሪያዬ ያሉ ልጆች ያውቃሉ። የኔ ፊት ወንበር ሄዶ መቀመጥ ተማሪውን ብቻ ሳይሆን መምህሬንም ገርሞታል ።

"ዛሬ እንዴት ነው? ... የመማር ሞራልሽ መጥቷል ማለት ነው" ፈገግ አለልኝ ።

ሞትኩለት !

ክለብ ለክለብ የሚቅለበለበው ምላሴ ጉሮሮዬ ላይ ገብቶ ተሰነቀረ ።

የሆነ ቅጥ የሌለው መልስ መለስኩኝ.. .

"አ....አ......መ...ሰ....ለ....እ....ኝ "

ስደናበር ነጃትና ጓደኞቿ ተያይተው ሳቁብኝ። 

በቃ ጠመድኳት ይህችን ሴት !

"ንፁህ ምን ሆነሻል እጅሽ እየተንቀጠቀጠ ነው እኮ!  አመመሽ እንዴ? "

"አዎ ቲቸር !" 

ይኸው የኔ ትሁት ዛኪ ደገፍ አድርጎ ከክፍል እንድወጣ ዕድል ሰጠኝ ።

አለንጋ ጣቶቹ ወገቤን ሲይዙኝ የእውነት ታመምኩለት ...ሰውነቴን እሱ ላይ ጣልኩት ።

የክፍሉን በር ከፍቶ ወጣን ።

"አይዞሽ ንፁህ.. ."

እንዲህ ሲለኝ የነጃት የቅናት ዛር አናቴ ላይ ተፈናጠጠ ።

በድፍረት ከናፍሩን ስሜ ፍቅሬን ልገልፅለት ደፈርኩ ...

አንድ 

ሁለት

ሶስ.....

     (ይቀጥላል)
@fikireskemekabirtireka
249 viewsedited  21:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-17 00:20:22 Fikir Eske Mekabir pinned «ፍቅር በዚያ ወራት ፤፤፤ ሚካኤል.አ ፤፤፤ (ክፍል 1) ስሜ ንፁህ ይባላል ። የስሜ እዳ አለብኝ። እንኳን ለሰው ልጅ ለመላዕክት እንኳ ያልተገባ መጠሪያ መያዜን ሳስበው እሸማቀቃለሁ። ከክፍል ጓደኞቼ ጋር እየጨፈርን.. .ሺሻ እያጨስን በምናሳልፋቸው ወቅቶች ስሜን የሚጠራኝ ሰው ባይኖር ስል እመኛለሁ። ደግሞ ማንም እንደሚያውቀው የትምህርት ቤት ህይወት (ላይፍ ይሉታል ጓደኞቼ በቋንቋቸው) ፈታኝ መሰናክሎች…»
21:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-15 01:19:04 ⇲ ⇲ ✘ አለማወቅ ✘ ⇲ ⇲
❏ ❐ ❑ ❒ ❏ ❐ ❏ ❐ ❑ ❒ ❏ ❐ ❏

ሰው ግን ለምንድን ነው ዝናብ ደበደበኝ የሚለው? የኛ ሀገር ሰው ለምንድን ነው በንግግሩ የሁሉም ነገር ተጠቂ ሆኖ የሚሰማው? ዝናብ ደበደበኝ ፣ ድጡ አዳለጠኝ ፣ ጎርፍ ወሰደኝ ፣ ብርድ እንዳይመታኝ ወይም መታኝ ጉንፋን ያዘኝ...። ቋንቋችን እንዲህ ተደረኩኝ ለምን ይበዛዋል? ፀሐዩ ጠፈጠፈኝ እሳቱ ለበለበኝ ፣ ተደረገብኝ አደረጉብኝ.....። ይገርማል!


ደራሲ ዶ/ር ዳዊት ወንድምአገኝ
አለማወቅ ገፅ 301
@fikireskemekabirtireka
232 viewsedited  22:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ