Get Mystery Box with random crypto!

ፍቃዱ ሲሳይ የተለያዩ መጣጥፎች፣ግጥሞች ፣ የአመታዊ ክብረ በዓላት ወረቦች እና ታሪካዊ ቦታዎች በምስል

የቴሌግራም ቻናል አርማ fikadu_sisay — ፍቃዱ ሲሳይ የተለያዩ መጣጥፎች፣ግጥሞች ፣ የአመታዊ ክብረ በዓላት ወረቦች እና ታሪካዊ ቦታዎች በምስል
የቴሌግራም ቻናል አርማ fikadu_sisay — ፍቃዱ ሲሳይ የተለያዩ መጣጥፎች፣ግጥሞች ፣ የአመታዊ ክብረ በዓላት ወረቦች እና ታሪካዊ ቦታዎች በምስል
የሰርጥ አድራሻ: @fikadu_sisay
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 303
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ኦርቶዶክሳዊ የሆኑ ልዩ ልዩ መጣጥፎች ፣ የአመታዊ ክብረ በዓላት ወረቦች ፣ ግጥሞች እና ሀገራዊ አጀንደዎችን የምንዳስስበት እና እርሶሞ የሚጋሩበት በባለቤቱ የተከፈተ ቻነል ነው!!!
@fikadu_sisay

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-07-25 13:50:35
107 views10:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 13:50:20
91 views10:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 13:49:33 ✤ ቅዱስ #ቂርቆስ እድሜው የሦስት ዓመት ሳለ እናቱ ቅድስት እየሉጣ ከሮሜ ወደ ሌላ ሃገር ሸሽታ ይዛው ሄደች በዚያም የሸሸችውን መኮንኑን አገኘችው። የሚያውቋትም ሰዎች ሸሽታ እንደመጣች ስለተረዱ ለመኮንኑ ነገር ሰሩባት። መኮንኑም ቅድስት አየሉጣን አስጠራትና ስለ አምልኮ ጠየቃት። ቅድስት ኢየሉጣም መኮንን ሆይ፡ እድሜው ሦስት አመት የሆነው ሕፃን አለ አማልክቶችህን ማምለክ መልካም እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ ያስረዳን ዘንድ እርሱን ጠይቅ አለችው። መኮንኑም ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስም ወደ አለበት ጭፍራውን ልኮ ወደ እርሱ አስመጣው ሕፃኑንም ፊቱ ብሩህና ደስተኛ እንደሆነ አየውና አንተ ደስተኛ ሕፃን ሆይ እንዴት ነህ አለው። ሕጻን ቅዱስ ቂርቆስም መለሰለት እንዲህም አለው። አዎ እኔ በጣም ደስተኛ ነኝ ደስታየም ተጠብቆልኛል ላንተ ግን ኀዘንና ለቅሶ ጥርስ ማፋጨትም ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስም ለዝንጉዎች ተድላ ደስታ የላቸውም ብሏልና አለው። እግዚአብሔር አምላክ ኃይልንና ንግግርን ሰጥቶታልና በዚያ ለተሰበሰቡት ሰዎች እስኪደነግጡ ድረስ ብዙ ተናገረ። ሕፃን ቅዱስ ቂርቆስም ንጉሱን መኳንንቱንና ጣዖታቱን ረገማቸው ከብርታቱም የተነሳ አደነቁ። መኮንኑም በአፈረ ጊዜ በየአይነቱ በሆነ ስቃይ፡ ታላላቆች አንኳ የማይችሉትን ታላቅ አስጨናቂ የሆነ ስቃይን አሰቃየው። እናቱ ቅድስት እየሉጣንምከእርሱ ጋር እንደ እርሱ በጣሙን አሰቃያት። እግዚአሔብሔር ግን ያለ ምንም ጉዳት ያነሳቸው ነበር። ብዙዎች አህዛብም ይህን አይተው አደነቁ ክብር ይግባውና በጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነት አምነው በሰማእትነት ሞቱ የሰማእትነትንም አክሊል ተቀበሉ። በሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ላይም የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ አደረበት። ታላላቅ ድንቅ ተአምራቶችንም ያደርግ ነበር። ብዙዎች በሽተኞችንም ያድናቸው ይፈውሳቸው ነበር

። ይህንን ያየ መኮንን በታላቅ የነሃስ ጋን ውስጥ ውሃ ጨምረው በእሳት ያፈሉት ዘንድ አዘዘ። የፍላቱም ድምጽ እንደ ክረምት ነጎድጓድ ሆነ ድምጹም በጣም ያስተጋባ ነበር። ይህን ያየችና የሰማች እናት ቅድስት እየሉጣም ፍርሃትና የሃይማኖት ጉድለት ታየባት። ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ግን እናቱ ቅድስት እየሉጣን ሁኔታዋን አይቶ ወደ አምላኩ እግዚአብሔር ጸለየ። ያን ጊዜ ልዑል እግዚአብሔር ልቧን ወደ ሰማይ አሳርጎ ለቅዱሳን ሰማዕታት የተዘጋጁ የብርሃን ማደሪያዎችን አሳያት። ቅድስት እየሉጣም እንደገና በሃይማኖቷ ጸናች። እግዚአብሔር አምላኳንም አመሰገነችው። ልጇን ሕፃኑን ቅዱስ ቂርቆስንም ልጄ ሆይ አንተ ከእንግዲህ አባቴ ነህ እኔም ልጅህ ነኝ አለችው። ቅድስት እየሉጣም ለልጇ ያች የተወለድክባት እለት ቀኗ የተባረከችና የተቀደሰች ናት አለችው። የመኳንንቱ ጭፍሮችም እሳት ወደ አለበት ጋኖች ውስጥ ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱን ቅድስት እየሉጣን በጨመሯቸው ጊዜ የውሃው ፍላት ወደያውኑንቀዘቀዘ። ከእግዚአብሔር የታዘዘ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወርዶ የእሳቱን ኃይል አቀዝቅዞታልና። ይህን ያየ መኮንን ሥጋቸው ተቆራርጦ እስከሚወድቅ ድረስ በመቃጥን ውስጥ አድርገው አንዲጎትቷቸው አዘዘ። ከእግዚአብሔርም የታዘዘ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል አዳናቸው። መኮንኑም በታላቅ ስቃይ ያሰቃያቸው ዘንድ አስቦ እስኪመክር ድረስ በወህኒ ቤት ዘጋባቸው። በዚህን ጊዜ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሕጻኑ ቅዱስ ቂርቆስን አረጋጋው አጽናናው። ስሙን ጠርተው መታሰቢያ ለሚያደርጉለትም በረከትን እንደሚያገኝ ቃል ኪዳን ሰጠው ። እግዚአብሔር አምላካችን የሕጻኑ ቅዱስ ቂርቆስና የእናቱ የቅድስት ኢየሉጣን በረከታቸውንና ረድኤታቸውን ያድለን አሜን።

ቅዱስ ቂርቆስና ቅድስት ኢየሉጣ በእግዚአብሔር ቸርነት በቅዱስ ገብርኤል ተራዳኢነት በእሳት ከመጣል በንፍር ውሃ ከመለብለብ ከዳኑ በኋላ እለስክንድሮስ መከራውን ፈርተው ይመለሳሉ ብሎ በሀብለ ሰናስል እያሰረ በችንካር እየቸነከረ ሲያሰቃያቸው ቆየ፡፡ የማይሆንለት ሲሆን እጅ እግራቸውን አስሮ ከዝግ ቤት አስቀመጣቸው፡፡ ጌታም የመከራቸውን ጽናት የትዕግስታቸውን ብዛት አይቶ ከመከራ ሊያሳርፋቸው ሽቶ በመንፈቀ ሌሊት ተገልጾ፤ በመጣ ጊዜ “ሰላም ለከ ኦ ፍቁርየ ቂርቆስ” ወዳጄ ቂርቆስ ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን፤ ብሎ ሠላምታ ከሰጠው በኋላ የመከራህን ጽናት፣ የትዕግስትህን ብዛት አይቼ ቃል ኪዳን ልገባልህ ነው።” “ዘመጠነዝ ገድለ ተጋዲልየ ምንተኑ ትዔስየኒ” በሕፃንነቴ ይህን ያህል ተጋድዬ የምትሰጠኝ ምንድነው?” አለው። “አዐሥየከ ዘሀሎ ውስተ መልብከ” በልብህ ያለውን ሁሉ እሰጥሃለሁ አለው። እንኪያስ በስሜ ቤተ ክርስቲያን ከታነጸበት ረሃብ፣ ቸነፈር፣ የሰው በሽታ፣ የከብት እልቂት፣ የእኅል የውሃ ጥፋት፣ አይሁን አለ። ጌታም ይሁንልህ በማለት ቃል ኪዳን ገብቶላታል፡፡ ደግሞም “ኢትቅብር ሥጋየ በዲበ ምድር” ሥጋዬ በምድር አይቀበር አለው። “አልቦ ዘይፈደፍደከ ዘእንበለ መንበረ መንግሥትየ ወማርያም ወላዲትየ ወዮሐንስ መጥምቅየ” (ከመንበረ መንግስቴ፣ ከማርያም እናቴ ከዮሐንስ መጥምቅም በቀር በመንግሥተ ሰማያት የሚበልጥህ የለም።)
“ወዓዲ ከመ ኢይስማን ሥጋከ ዲበ ሠረገላ ኤልያስ አነብረከ”
(ሥጋህን እንዳይፈርስ በኤልያስ ሠረገላ አኖርልሃለሁ) ብሎ ተስፋውን ነግሮታል። እናቱ ቅድስት ኢየሉጣ በመኮንኑ በሰይፍ ጥር ፲፮ በሰማዕትነት ያረፈች ሲሆን ቅዱስ ቂርቆስን ግን ተመለስ ቢለው አልመለስም እምነቴንም አልክድም ባለው ጊዜ ሰይፍ ጃግሬውን ጠርቶ በጥር ፲፭ አስገድሎት ሰማዕትነትን ተቀብሏል፡፡ የእናቱ የቅድስት ኢየሉጣ መታሰቢያዋ ዕለት በየወሩ በ፲፮ እመቤታችን ቃል ኪዳን በተቀበለችበት ቀን በሚታሰብበት የቅድስት ኪዳነ ምህረት ቀን ይታሰባል።
የመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ምልጃና ጸሎት፤ የቅዱስ ቂርቆስና የቅድስት ኢየሉጣ በረከታቸው ቃል ኪዳናቸው ይድረሰን በእውነት ይጠብቀን ለዘለዓለሙ አሜን፨

ምንጭ:- በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት
92 views10:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ