Get Mystery Box with random crypto!

ፍቃዱ ሲሳይ የተለያዩ መጣጥፎች፣ግጥሞች ፣ የአመታዊ ክብረ በዓላት ወረቦች እና ታሪካዊ ቦታዎች በምስል

የቴሌግራም ቻናል አርማ fikadu_sisay — ፍቃዱ ሲሳይ የተለያዩ መጣጥፎች፣ግጥሞች ፣ የአመታዊ ክብረ በዓላት ወረቦች እና ታሪካዊ ቦታዎች በምስል
የቴሌግራም ቻናል አርማ fikadu_sisay — ፍቃዱ ሲሳይ የተለያዩ መጣጥፎች፣ግጥሞች ፣ የአመታዊ ክብረ በዓላት ወረቦች እና ታሪካዊ ቦታዎች በምስል
የሰርጥ አድራሻ: @fikadu_sisay
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 303
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ኦርቶዶክሳዊ የሆኑ ልዩ ልዩ መጣጥፎች ፣ የአመታዊ ክብረ በዓላት ወረቦች ፣ ግጥሞች እና ሀገራዊ አጀንደዎችን የምንዳስስበት እና እርሶሞ የሚጋሩበት በባለቤቱ የተከፈተ ቻነል ነው!!!
@fikadu_sisay

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-06 22:23:59
85 views19:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-06 22:23:53 ጾመ ፍልሰታ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
ፍልሰታ ማለት ምን ማለት ነው?

ጾመ ፍልሰታ <ፍልሰታ > የሚለው ቃል የሚገልጸው ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ለቆ መሔድን መሰደድን መፍለስን ያመለክታል። ይህም የእመቤታችንን ሥጋ ከጌቴሴማኒ ወደ ገነት መፍለሱን በኋላም በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር ከነበረበት መነሣቱን ለማመልከት ይነገራል። ጾመ ፍልሰታ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ፷፬ ዓመት በዚች ምድር ኖራ እንደ አንድ ልጇ መሞቷን መነሣቷንና ማረጓን ያዩ ዘንድ ሐዋርያት የጾሙት ጾም ነው::
ይህ በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ከተወሰኑት ሰባቱ አጸዋማት ውስጥ ለዓመቱ የመጨረሻው ጾም ነው።

ፍልሰታ ጾም ለምን እንፆማለን?

የፍልሰታ ጾም ከነሐሴ 1 እስከ 15 የሚጾም ሲሆን በቤተ ክርስቲያናችን አስተምሮ መሠረት እመቤታችን ያረፈችው በጥር 21 ቀን ነው። ሐዋርያትም አስከሬኗን ሊቀብሩ ወደ ጌቴሴማኒ ይዘዋት ሲሔዱ አይሁድ በምቀኝነት ልጇ ከሙታን ተለይቶ ተነሥቷል። አሁንም እርሷ ገቢረ ተአምር ልታደርግ አይደል? ብለው አስከሬኗን ተሸክመው የሚሔዱትን ሐዋርያትን በታተኗቸው። በዚህን ጊዜ መላእክት የእመቤታችንን አስከሬን ከአይሁድ ነጥቀው በገነት አኖሩት። በስምንተኛው ወር በነሐሴ ሐዋርያት ከነሐሴ 1 እስከ 14 ሁለት ሱባዔ ገብተው ከጌታችን ተቀብለው በጸሎትና በምህላ ቀበሯት። በዚህ የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ ከአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ ቶማስ የተባለው ለሐዋርያዊ አገልግሎት ወጥቶ ነበር እና መገኘት አልቻለም ነበር።
እመቤታችን በተቀበረች በሦስተኛው ቀን ከላይ እንደተጠቀሰው በነቢያት ትንቢት እንደተነገረላት እንደ ልጇ ተነሥታ ስታርግ ቶማስ ከሀገረ ስብከቱ በደመና ተጭኖ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመጣ አገኛት። በዚህን ጊዜ ትንሣኤዋን ሌሎች ሐዋርያት አይተው ለእርሱ የቀረበት መስሎት በረከት ቀረብኝ ሲል ተበሳጨ።ቀድሞ የልጅሽን ትንሣኤ ሳላይ ቀረሁ አሁን ደግሞ ያንችን ትንሣኤ ሳላይ ቀረሁ ብሎ እራሱን ከደመና ላይ ሊወረውር ቃጣው። በዚህን ጊዜ እመቤታችን ቶማስን አፅናናችው ከእርሱ በቀር ትንሣኤዋን ያየ አለመኖሩን ነገረችው።ለምስክርነት እንዲሆንም በቀብሯ ጊዜ የነበረውን ሰበኗን ሰጥታው አረገች።

ሞት በጥር፣በነሐሴ መቃብር

ቶማስም ሰበኗን ደብቆ ይዞ ሐዋርያት ካሉበት ደረሰ። ሐዋርያትንም የእመቤታችን ነገር ምን ደረሰ? አላቸው። ሐዋርያትም እመቤታችን ሱባዔ ገብተን ጌታችን አስከሬኗን ከዕፀ ሕይወት አምጥቶ ሰጥቶን በክብር ቀበርናት አሉት። ቶማስም መልሶ ሞት በጥር፣በነሐሴመቃብር?አላቸው።ሐዋርያትም መለሱለት ቶማስ አትጠራጠር። ቀድሞ ጌታችን በተገለጠ ጊዜ ትንሣኤውን ጣቶቼን በተቸነከሩ እጆችህ ካላስገባሁ ብለህ የደረሰብህን ታውቃለህ አሁንም የእመቤታችንን መቀበር አላመንክምን? አሉት። ቶማስ ግን ሐዋርያትን ይዞ ወደ መቃብሯ ሔደ። መቃብሯን ከፍተው ሲመለከቱ ሐዋርያት ደነገጡ። በዚህን ጊዜ ቶማስ አታምኑኝም ብየ ነው እንጂ እመቤታችን አርጋለች። ስታርግም በደመና ከሀገረ ስብከቴ ስመጣ ተገናኘን ለምልክቱም ይኸው የቀበራችሁበት ሰበን አላቸው።ሐዋርያትም ለበረከት ሰበኗን ተከፋፍለው ወደየሀገረ ስብከታቸው ሔዱ።
በዓመቱ ግን ሐዋርያት ተሰበሰቡ እና ትንሣኤሽን ቶማስ አይቶ እኛም በረከት አይቅርብን ብለው ከነሐሴ አንድ ጀምረው ሱባዔ ገቡ።በነሐሴ 14 አስከሬኗን ትኩስ በድን አድርጎ አምጥቶ ሰጥቷቸው ከቀበሯት በኋላ በሦስተኛው ቀን ነሐሴ 16 እመቤታችን ተነሥታ ጌታችን ከመላእክት እና ቅዱሳን ጋር ሆኖ ሐዋርያትን አቁርቧቸዋል።(ውዳሴ ማርያም ትርጉም)።
ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሮ እናሐዋርያት መሠረት ላይ የታነፀችው ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን የሐዋርያትን ግብር ምሳሌ በማድረግ ልክ እንደ ሐዋርያት ለሐዋርያት የተገለጠ በረከት እና የእመቤታችን ረድኤት እንዲያድርብን እንጾመዋለን።በቤተ ክርስቲያናችን ከአምስቱ የአዋጅ አጽዋማት መካከልም በመሆኑም ሁሉም ምእመናን እንዲጾም ቤተ ክርስቲያን ታስተምራለች። ነቢዩ ዳንኤል በትንቢተ ዳንኤል ምዕ 10፣21 ላይ እንደተጠቀሰው ”በዚያም ወራት እኔ ዳንኤል ሦስት ሳምንት ሙሉ ሳዝን ነበርሁ።ማለፊያ እንጀራም አልበላሁም፥ ሥጋና ጠጅም በአፌ አልገባም፥ ሦስቱም ሳምንት እስኪፈጸም ድረስ ዘይት አልተቀባሁም።” እንዳለ
የእመቤታችን በረከቷ አማላጅነቷ ከሁላችንም ጋር ይሁን እናትነቷ ይብዛልን ::
መልካም የፍልሰታ ፆም ይሁንልን ሀገራችንን ሰላም ታድርግልን አሜን።
ወስብሀት ለ እግዚአብሔር
165 views19:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-02 23:30:59
የታወጀበት
ፍቅር በተግባር የተገለጠበት
እውነት ከሁሉ ከፍ ብሎ የታየበት

ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለምን ለማዳን በዓለም ተሰደበ፣ በዓለም ተሰቀለ። ልታድኑት የምትፈልጉት ሕዝብ ሊሰድባችሁ ሊሰቅላችሁ ይችላል። በጨለማ ላለ ሕዝብ ብርሃንን ይዘህ ስትቀርብ በጨለማ ያለው ሕዝብ ወደ ግብጽ ሊያሳድድህ ይችላል።

ሕዝብህ ምንም ቢጠላህና ቢሰድብህ ግን ለሕዝብህ መልካም ማድረግን አትተወው። እስኪሰቅሉህ ድረስ መልካም ማድረግህን ቀጥልበት።

ሁልጊዜም ዕለተ ስቅለትን እናስባት

ምንጭ:- መ/ር በትረማርያም
126 viewsedited  20:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-02 22:55:57

ስነ ፍጥረት
ክፍል (፯) ስድስት

#የዕለተ_አርብ_ፍጥረታት

#አርብ፦የሚለው የሚለው የዕለቱ ስም አረበ ከሚለው የግእዝ ቃል የተገኘ ነው #መጨረሻ ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔር ፍጥረታትን መፍጠር በዕለተ እሑድ ጀምሮ በዕለተ አርብ አጠናቋል።

#የአርብ ፍጥረታት 4 ናቸው።
1.ዘመደ እንስሳት
2.ዘመደ አራዊት
3.ዘመደ አእዋፋት
4.የሰው ልጅ (መዝ 139፥18)
መዝ 48፥12
ኦ.ዘፍ 1፥26
የሀሙሱ እና የአርቡ ፍጥረታት ልዩነት
#.የሀሙሱን ፍጥረታት ያስገኘው ውሃ ነው። ኦ.ዘፍ 1፥20
#.የአርቡ ፍጥረታት ግን ያስገኘችው ምድር ናት። ኦ.ዘፍ 1፥24

#የሰውን ልጅ ለምን መጨረሻ ፈጠረው?

መጀመሪያ የሚያስፈልገውን ሁሉ አስቀድሞ አዘጋጅቶ ሊፈጥረው ስለፈለገ

1.የሚመገበው፦እንስሳት እና አትክልት
2.ብርሐን የሚሰጡት፦ፀሐይ እና ጨረቃ
3.የሚጠብቁት፦ቅዱሳን መላዕክት
4. የሚኖርባት:- ምድር
5. የሚወርሰው:- ሰማያዊ ርስት

እነዚህ ሁሉ የግድ ያስፈልጉታል እና አዘገየው።
ከጎኑ ለምን ሄዋንን ፈጠራት?
1.ጎን የፈለገ እርቃን ቢኮን በልብስ ይሸፈናል። የባል እና የሚስት ገበናም በሰው ፊት አይወራም እና
2.እሷን ከጭንቅላቱ ከፍ አድርጎ ቢፈጥራት ኖሮ ትሰለጥንበት ነበር
ዝቅ አድርጎ ከቁርጭምጭሚቱ ቢፈጥራት ኖሮ አዳም ይነግስባት ነበር

ለዛ ነው መካከለኛውን ቦታ መርጦ ከዛ የፈጠራት። ሁለቱም እኩል መሆናቸውን ሲያሳይ ነው።

የጋብቻ አላማ ምንድን ነው?
1.ዘር ለመተካት
2.ከዝሙት ጠንቅ ለመራቅ
3.ለመረዳዳት

1ኛ ቆሮ 7 : 1 - 10

የመጨረሻው ክፍል

ክፍል 8 ይቀጥላል....

የእስካሁኖቹን የተለቀቁትን ክፍላት በደንብ አንብቡ በ 24 ሰዓት ውስጥ የሚመለስ ጥያቄ ይኖረዋል።
98 viewsedited  19:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 16:44:22

ስነ ፍጥረት
ክፍል (፮) ስድስት

#የዕለተ_ሐሙስ_ፍጥረታት

#ሐሙስ፡- የሚለው የዕለቱ ስም ሀምሰ ከሚለው የግእዝ ቃል የተገኘ ነው #አምስተኛ ማለት ነው፡፡ አምስተኛነቱም እግዚአብሔር ፍጥረታትን መፍጠር ከጀመረበት ከዕለተ እሑድ ጀምሮ ያለው ቀን ማለት ነው፡፡

#የሐሙስ_ፍጥረታት
እግዚአብሔር ሐሙስ በቀዳማይ ሰዓት ለሊት “#ውሃ_ሕያው_ነፍስ_ያላቸው_ተንቀሳቃሾች_ታስገኝ” ብሎ በማዘዝ ሦስት አይነት ፍጥረታትን ፈጠረ፡፡ ዘፍ 1፡20 በዕለተ ሐሙስ የተፈጠሩት ሦስት ፍጥረታት ዘመደ እንስሳት የሚባሉት አሣዎች፣ ዘመደ አራዊት የተባሉት ኣዞ፣ጉማሬ፣ አሳነባሪ፣ ዘመደ አዕዋፍ የሚባሉት ደግሞ ዳክዬዎች ናቸው፡፡
#በዕለተ_ሐሙስ_የተፈጠሩት_ፍጥረታት_ተፈጥሮአቸው_ከአራቱ_ባሕሪያተ_ስጋ /መሬት፣ ውሃ ፣ነፋስና፣ እሳት/ ነው፡፡ አካላቸው ሥጋና ደም፣ አፅምና ጅማት ሲሆን በደም ነፍስ ይንቀሳቀሳሉ የደመ ነፍስ እውቀት አላቸው ደመነፍስ ማለትም በደም ነፍስነት፣ ኃይልነት የሚንቀሳቀሱ፣ የደም ነፍስ ያላቸው፣ ደማቸው ሲቆም እንቅስቃሴያቸውም የሚቆም ማለት ነው፡፡
#የሐሙስ_ፍጥረታት_በአካሄዳቸው_በአኗኗራቸው_አንፃር_በሦስት_ይከፈላሉ በአካሄዳቸው በልብ የሚሳቡ፣ በእግር የሚሽከረከሩ፣ /የሚሄዱ/፣ በክንፍ የሚበሩ ይባላሉ፡፡ በአኗኗራቸውም አንጻር በባህር ውስጥ ተፈጥረው በረው ወደ የብስ፣ ወደ ደረቁ መሬት የወጡ፣ በዚያው በተፈጠሩበት በባህር ውስጥ የቀሩ፣ ወጣ ገባ እያሉ ማለት ከባህር ወደ የብስ፣ ከየብስ ወደ ባሕር ወጣ ገባ እያሉ የሚኖሩ ይባላሉ፡፡ ከእነዚህም ፍጥረታት የሚበሉና የማይበሉ ለሰው የሚገዙና፣ የማይገዙም አሉ፡፡

#የሐሙስ_ፍጥረታት_ምሳሌነት

#በባሕር_ውስጥ_የሚኖሩት_ምሌሳነታቸው፡-
በእግዚአብሔር አምነው በስሙ ተጠምቀው በዚያው ፀንተው የሚኖሩ ሰዎች፤
በሕገ እግዚአብሔር ፀንተው በትዳር ተወስነው በሀብት በንብረታቸው መልካም ስራ እየሠሩ ዓሥራት አውጥተው፣ በዓላትን አክብረው የሚኖሩ የሕጋውያ ሰዎች፤
ግብራችንን አንተውም ብለው ሲሰርቁ ሲቀሙ፤ ሲምሉና ሲገዘቱ የሚኖሩ የኃጥአን ምሳሌ ናቸው፡፡

#ወጣ_ገባ_እያሉ_የሚኖሩት_ምሳሌነታቸው
አንድ ጊዜ ወደ ዓለም አንድ ጊዜ ወደ ገዳም ሲመላለሱ የሚኖሩ መነኮሳት፣
አንድ ጊዜ ወደ ሀይማኖት አንድ ጊዜ ወደ ክህደት የሚወላውሉ ሰዎች፤
#በባሕር_ተፈጥረው_በረው_ወደ_የብስ_የሄዱት፡
ከዘመድ አዝማድ ተለይተው ርቀው ከበረሃ ወድቀው ደምፀ አራዊቱን ፀብአ አጋንንቱን ግርማ ለሊቱን ታግሰው የሚኖሩ የመናንያን ምሳሌ ናቸው፡፡
አንድም በባህር ተፈጥረው በረው ወደ የብስ የሚኖሩት የከሀዲዎች ምሳሌ ነው በሀይማኖት ኖረው በኋላ ይክዳሉና

#አካሄዳቸውም
#በልብ_የሚሳቡ፡- የመንግስት ምሳሌ ናቸው እነዚህ በልብ (በደረት) ተስበው ስራቸውን ፈቃዳቸውን እንዲፈፅሙ መንግስትም በልቡ ያሰበውን ይሠራል ይፈፅማል፡፡
#በእግር_የሚሽከረከሩ
“ያላችሁን ትታችሁ ተከተሉኝ” ባለው አምላካዊ ቃል መሠረት ሁሉን ትተው ከሴት ከወንድ እርቀው ድንግልናቸውን ጠብቀው ከትሩፋት ወደ ትሩፋት እየተሸጋገሩ የሚኖሩ የመናንያን ምሳሌ፡፡

#በክንፋቸው_የሚበሩት፡- ሥጋችሁን እንጂ ነፍሳችሁን ለመግደል የማይችሉትን አትፍሩ ባለው አምላካዊ ቃል ተመርተው ሳይፈሩ ዓላውያን ነገስታት ካሉበት ገብተው ሃይማኖታቸውን በመመስከር ሰማዕታትነታቸውን የሚፈፅሙ ሰማዕታት ምሳሌ ናቸው፡፡
#ሰው_የሚባላቸውና_ለሰው_የሚገዙት፡- ለእግዚአብሔርና ለሰው በፍቅር በትሕትና የሚገዙ፣ የእግዚአብሔርን ፍቃድ የሚፈፅሙ የፃድቃን ምሳሌ ናቸው፡፡
#ሰው_የማይበላቸው_ለሰው_የማይገዙት ለእግዚአብሔርም ለሰውም የማይገዙ፣ አንገዛም አንታዘዝም ብለው በትዕቢት በዓመፅ የሚኖሩ የሃጣን ምሳሌ ናቸው፡፡
እግዚአብሔር ከአንድ ባሕር ሦስት ወገን የሆኑ ፍጥረታትን ፈጠረ፡፡ ከአንድ ማየገቦ ሦስት ትውልድ፡- ትውለደ ሴም፣ ትውልደ ያፌት፣ ትውልደ ካም ይጠመቁ ዘንድ መሰጠቱን ያሳያል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ልጅነት በአብ‹ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ተጠምቀው ለመሰጠቷም ምሳሌ ነው፡፡
በዕለተ ሐሙስና በዕለተ ዓርብ የተፈጠሩት ፍጥረታት “እንስሳት” በመባል አንድ ቢሆኑም በአኗኗራቸውና በግብራቸው ይለያያሉ፡፡ የሐሙስ ፍጥረታት ከባሕር ተለይው በየብስ /በምድር/ መኖር አይችሉም የፀሐይ ሙቀት ሲነካቸው ይሞታሉ፡፡
የግብር ፍጥረታትም ከምድር ተለይተው በባህር ውስጥ መኖር አይችሉም የባህር ውርጭ ቅዝቃዜ ይገድላቸዋልና፡፡


ወስብሐት ለእግዚአብሔር


ክፍል 7 ይቀጥላል ……
106 views13:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-30 08:23:30

ስነ ፍጥረት
ክፍል (፭) አምስት

#በዕለተ_ረቡዕ_የተፈጠሩ

ረቡዕ ረብዕ ከሚል የግእዝ ቃል የተገኘ ሲሆን አራተኛ ማለት ነው በዚህ ዕለትም ልክ እንደማክሰኞ ሶሰት ፍጥረታት ተፈጥረዋል እነርሱም፡
1. ፀሐይ
2. ጨረቃ
3. ከዋክብት ናቸው

ተፈጥሮአቸውስ ከምን ነው ቢሉ የፀሐይ ተፈጥሮ ከእሳት እና ከነፋስ ነው ጥቂት እሳት ከኮሬብ ጥቂት ነፋስ ከአዜብ ከፍሎ ፀሐይም ከእሳትና ከነፋስ እንደተፈጠረች በእሳትነቷ ትተኩሳለች በነፋስነቷ ደግሞ ከቦታ ወደ ቦታ ትንቀሳቅሳለች
ጨርቃ እና ከዋክብትን ከነፋስ እና ከውሃ ፈጠራችው ጥቂት ውሃ ከናጌብ ጥቂት ነፋስ ከአዜብ ከፍሎ ጨረቃንና ከዋክብትን ፈጠረ ሁለቱም ከውሃ እንደመፈጠራቸው ይቀዘቅዛሉ ከነፋስ እንደመፈጠራቸው ደግሞ ልክ እንደ ፀሐይ ከቦታ ወደ ቦታ ይንቀሳቀሳሉ፡፡
ከመቶ ነገድ ለአስሩ አለቃ መላእክት ከሃሊነቱን ሊያሳያቸው ከታችኛው ከተማ አውጥቶ በላይኛው ከተማ አቆማቸው ከዚያም ለይኩን ካለው ብርሃን የስንዴ ፍሬ ታህል ከፍሎ ለፀሐይ ቀብቶ ለመላእክት ቢያሳያቸው አስፈራቻቸው፡፡ ጌታም ለመላዕክት ያልተቻለ ለሰው አትቻልም ብሎ ብርሃኗን ከሰባት እጅ ከፍሎ ሁለት እጅ ለጨረቃ ቀባት አምስት እጅ ለፀሀይ ቀረ ዳግመኛም ከአምስት እጅ ብርሃን አንድ እጅ ነስቶ ለከዋክብት ሰጠ ክብራቸውን አበላልጦ ቀባቸው፡፡
“1 ቆሮ 15፡41 “በክብር አንዱ ኮከብ ከሌላው ኮከብ ይለያል” አራት እጅ ለፀሐይ ቀረ ዳግመኛም እግዚአብሔር አንድ እጅ ብርሃን ነስቶ ለሰማያት ለደመናት ቀባቸው ሶስት እጅ ደግሞ ለፀሐይ ተሰጣት ፀሀይም ዛሬ እንደምናያት ሆና ቀረች፡፡
ፀሐይ ቀንና ሌሊቱን ብታበራ ከዋዕዩ ፅናት የተነሳ ፍጥረት ሁሉ በተቃጠለ ነበር ጨረቃና ከዋክብትም ቀንና ሌሊቱን ቢያበሩ ከቁር /ከቀዝቃዛ/ ብዛት ከውርጭ ጽናት የተነሳ ፍጥረት ሁሉ በተኮማተረ ነበር ስለዚህ ፀሐይ ቀን ያቃጠለቻትን ምድር ጨረቃና ከዋክብት በለሊት ያበርዳታል ጨረቃና ከዋክብት ለሊቱን ምድርን ያቀዘቅዛታል ፀሐይም በቀን በመውጣት ምድርን ታሞቃታለች፡፡
ፀሐይን፣ ጨረቃን፣ ከዋክብትን መፍጠሩስ እጠቀምባቸው ብሎ ነውን ቢሉ አይደለም ለሰው ልጆችና በዚህ አለም ለሚገኙ ፍጡሮች እንዲያበሩላቸው ብሎ እንጂ እግዚአብሔር አንድ ጊዜ ብርሃን ፈጥሮ አለም በዚያ ብርሃን ብቻ እንድትገለግል ማድረግ ይቻለው ነበር ነገር ግን ለዘመን መታወቂያና መለያ ይሆን ዘንድ ፀሐይን፣ ጨረቃን፣ ከዋክብትን በቀን እና በለሊት አስለጠናቸው ዘፍ 1፡ 14
#እነዚህ_ፍጥታት_እያንዳንዳቸው_ምሳሌነት_አላቸው_ይህም
#ፀሐይ፡- ሁል ጊዜ ሙሉ ሆና እንደምትኖር ጻድቃንም በምግባር በሃይማኖት ምሉአን ናቸውና ሃጥአንን በፀሐይ ይመሰላሉ፡፡ እንዴት ቢሉ ፀሐይ ብርሃኗ ሳይለወጥ በምላት እንደምትኖር ሃጥአንም በክህደት ምሉአን ናቸውና፡፡ “ሀጥእ ልቡ እንደ ጨረቃ ይጎድላል”
#ጨረቃ፡- ደግሞ አንድ ጊዜ ሙሉ አንዴ ግማሽ ስለምትሆን ባለፀኑ ሰዎች በሃጥአን ትመሰላለች አንድም በጻድቃን ጨረቃ ትመሰላለች ጨረቃ አንድ ጊዜ ስትሞላ አንድ ጊዜ ስትጎድል እንደምትኖር ጻድቃንም ፍጹማን ከሆኑ በኋላ በሃጥያት ቢሰናከሉ በንስሐ ይታደሳሉ “ምሳሌ 24፡16 “ጻድቅ ሰባት ጊዜ ይወድቃልና ይነሳማል” ተብሎ እንደተፃፈ
እነዚህን ፍጥረታት በማዕከል ሰማይ ወምድር ማድረጉ ምዕመናን ፃድቃን ምድራዊያ ሲሆኑ ሰማያውያን ለመሆን ምሳሌ ነው፡፡


ወስብሐት ለእግዚአብሔር

ክፍል 6 ይቀጥላል ……
100 views05:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-29 12:55:09 #ተዘርተው_በሚያፈሩበት_ጊዜ_ስናያቸው
• በጥቂት ጊዜ ተዘርተው የሚያፈሩት ግንቦት ተዘርተው በሰኔ የሚበቅሉ በትንሽ ዝናብ ፍሬ የሚሰጡ ሲሆን ይህ ባጭር ጊዜ መከራ የጌታን መንግስት የሚወርሱ ሰማዕታትን ያመለክታል በላይሰብን እና ፈያታዊ ዘየማንን አብነት እናደርጋለን፡፡
በግንቦት ተዘርተው በሌላኛው ዓመት ሐምሌ የሚያፈሩ ደግሞ የጌታችንን መንግስት ለመውረስ ብዙ ፈተናን መከራን የሚያዩ ቅዱሳን ምሳሌ ናቸው እንደ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ እንደ ኢዮብ ብዙ ደዌ ብዙ ስቃይ ያዩ የቅዱሳን ሰማዕታት ምሳሌ ናቸው፡፡
ምነው ጌታችን ሰውን በክብር አበላለጠው ቢሉ ይኸስ እንደልቡናው ፅናት እንደ አእምሮው ስፋት ነው ጌታ የሚችሉትን መከራ ይስጣል እንጂ የማይችሉትን አይሰጥምና ነው፡
• እነዚህን ሁሉ ያስገኘች ምድር ሰውን ትመሰላለች ሰው በሦስት ነገር ፀንቶ ይኖራል 1) በአጥንት 2) በጅማት 3) በደም እንዲሁም ምድር እንደ አጥንታችን ድንጋይ እንደጅማታችን ስር እንደ ደማችን ውሀ ይመሰላሉ የማክሰኞ ዕለት ፍጥረታት በእመቤታችንም ይመሰላል አምላካችን ደግሞ በዘር የማክሰኞ ፍጥረትን ምድር ምግብ የሚሆኑ አዝርዕት፣ አትክልት፣ ዕፅዋትን እንዳስገኘች እመቤታችንም ለሰው ልጅ ሥጋውን ደሙን ምግበ ነፍሰ አድርጎ የሰጠንን ክርስቶስን “እንበለ ዘር” (ያለ ወንድ ዘር) አስገኝታለች “ዘር ያልዘሩበት እርሻ አንቺ ነሽ የሕይወት ፍሬ ካንቺ ወጣ /ውዳሴ ማ ዘማክሰኞ/
• ምድር የእመቤታችን ምሳሌናት በሶስት ነገሮች እንደፀናች ሁሉ በድንጋይ፣ በስር፣ በውሃ እመቤታችንም በሦስቱ በአብ- በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ለመፅናቷ ምሳሌ ነው፡፡
አብ በየማኑ ከደነኪ
ወልድ አደረብሽ
መንፈስ ቅዱስ ፀለለብሽ አነፃሽ (አንቀጽ ብርሃን


ይኽ ከክፍል 4 የቀጠለ ነው ክፍል 5 የረቡዕ ሥነ ፍጠረት ነው ይቀጥላል......
96 viewsedited  09:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-28 16:53:43 • ቅጠል ኖሯቸው ፍሬ የማያፈሩ ደግሞ ሀይማኖት እያላቸው ምግባር ያልያዙ ናቸው “ወንድሞቼ ሆይ እምነት አለኝ የሚል ሥራ ግን የሌለው ቢኖር ምን ይጠቅመዋል እምነቱስ ሊያድነው ይችላል” እንዳለ ያዕ 2፡14
• እንዲሁም ቅጠል ኖሯቸው ፍሬ ያፈሩ ሀይማኖት ከምግባር አጣምረው የያዙ ቅዱሳንን ሲመስሉ ቅጠል ያላፈሩ ደግሞ ምግባር በሌላቸው አህዛብ ይመሰላሉ።

ክፍል 5 ይቀጥላል.....
100 views13:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-28 16:53:43

ስነ ፍጥረት
ክፍል ፬ ( አራት)

#የዕለተ_ሰኞ ፍ_ጥራታት
ሰኞ በግዕዝ “ሰኑይ” ሲባል ይህም ሁለተኛው ዕለት ነው በእለተ ሰኞ አዲስ ፍጥረት አልተፈጠረም፡፡ በዕለተ እሁድ የፈጠረውን ከሰማይ እስከ ምድር የነበረውን ውሃ ለሶስት ከፈለው ዘፍ 1፡6-8 በሁለተኛው ቀን ውሀን ወደታችና ወደላይ ለየ በመካከሉም ጠፈርን አደረገ በዚህ ቀን ጠፈርን ብቻ ፈጠረ ኩፋሌ 2፡9 ከጠፈር በላይ የቀረው ውሃ ሀኖስ ሲባል ከጠፈር በታች የቀረውን ደግሞ ውቅያኖስ ይባላል፡፡ ጠፈር ከመፈጠሩ በፊት ከምድር እስከ ኤረር ድረስ ውሀ ሞልቶ ነበር ሰኞ በአንደኛው ሠዓት ሌሊት በውሃና በውሀ መካከል ይለይ ዘንድ ጠፈር ይሁን ብሎ ቢያዝ በዓለም ሞልቶ የነበረው ውሀ ለሦስት ከፈለው፡-
1 ሀኖስ
2 ጠፈር
3 ውቅያኖስ ናቸው፡፡
እግዚአብሄር ከጠፈር በላይ ያወጣው ውሀ ሐኖስ የተባለውን ጠፈርን እንደይጫነው ባቢል የሚባል ነፋስ ወደ ላይ አውጥቶ ሐኖስን አሸከመው ባቢልም የረጋ ነፋስ ነው ጠፈርን ከታች ባቢልን (የረጋ ንፈስ) ከላይ አድርጎ ሁሉን በየቦታው አፀናቸው፡፡ ሐኖስ የተባለው ውሀ ከላይ ጠፈርን ባያቀዘቅዘው ኖሮ የፀሐይ ትኩሳት ይሰብረው (ይበሳው) ነበር፡፡
ሐኖስ፣ ጠፈር፣ ውቅያኖስ እያዳንዳቸው በቤተክርስቲያን ምሳሌ አላቸው
#ሀኖስ፡- በአብ ይመሰላል ምክንያቱም እግዚአብሔር አብን አላየነውም አልዳሰስነውም እንዲሁ ሀኖስም አይታይም አይዳሰስምና ነው፡፡
#ጠፈር፡- በመንፈስ ቅዱስ ይመስላል ይህ በተለምዶ ሠማይ የምንለው ነው፡፡ በመንፈስ ቅዱስ መመሠሉም መንፈስ ቅዱስ በሠው አድሮ ይታያል ነገር ግን አይዳሰስም ጠፈርንም እናየዋለን እንጂ መዳሰስ አይቻልም እግዚአብሔር ጠፈርን ማለትም በተለምዶ ሰማይ የምንለውን ፈፅሞ ነጭ ወይም ቀይ አላደርገውም ይህም ነጭ ቢሆን የሰውን ዓይን ይበዘብዛል ቀይ ደግሞ ቢሆን ዓይንን ያሳውር ስለነበር የሚሰማማ ቀለም አድርጎታል፡፡
#ውቅያኖስ፡- ሲሆን መሬት ላይ እንደመገኘቱ ምሳሌነቱ የወልድ ነው፡፡ ወልድ ስጋ ለብሶ በምድር አይተነዋልና በዚህ ይመሰላል ሶስቱም አንድ ውሃ መሆናቸው ደግሞ “ሥላሴ” ምንም እንኳን በአካል ሶስት ቢሆኑም በመለኮት አንድ መሆናቸውን ያሳየናል እንዲሁም ውሀ በሁሉም ቦታ እንደሚገኝ ሥላሴም በሁሉ ስፍራ የመገኘታቸው ምሳሌ ነው፡፡

#ዕለተ_ሰኞ_የተፈጠረው_የጠፈር_ጥቅም
እግዚአብሔር አምላክ በዕለተ ረቡዕ “ዘይኩኑ ብርሃናት ውስጠ ጠፈር ሰማይ ወያብርሁ ዲበ ምድር” ብርሃን ይሁን ባለ ጊዜ ፀሐይ፣ ጨረቃ፣ ከዋክብት የሚፈጠሩ ናቸውና ለነዚያ ማመላለሻ ሊሆን አስቀድሞ ፈጠረው
ቅርፁ ጎበብ ያለ በመሆኑ ከመጠን ያለፈ የፀሐይ ሙቀት መፋጀት እንዲያቀዘቅዝ
የሠው ልጅ ሰማይን እያየ ሰማያዊ ርስቱን ተስፋ እንዲያደርግ ነው፡፡


#የዕለተ_ማክሰኞ_ፍጥረታት
ማክሰኞ በግዕዝ ሰሉስ ማለት ሲሆን ሰሉስ ማለት 3ኛ ቀን ማለት ነው በዚህች ዕለት 3 ፍጥረታት ተፈጥረዋል፡፡ እነርሡም

1) #አትክልት - በእጅ የሚነቀሉ (የሚለቀሙ)

2) #አዝርእት - በማጭድ የሚታጨዱ

3) #ዕፅዋት - የሚቆረጡና የሚላጡ
እዚህ ጋር ሳናነሳው ማለፍ የሌለብን የዕለተ ሠሉስ ፍጥረታት አራት ናቸው ይላል መፅሐፈ ኩፋሌ፡፡ በዕለተ ሰሉስ ሦስት ፍጥረታት ተፈጠሩ የሚሉ ሊቃውንት በዕለተ እሁድ 8 ፍጥረታት ተፈጠሩ ይላሉና ጨለማን በመደመር መፅሐፈ ኩፋሌ ግን በዕለተ እሁድ 7 ፍጥረታት ተፈጠሩ ስለሚል ጨለማን በመቀነስ የዕለተ ሠሉስ ፍጥረታት ደግሞ 4 ፍጥረታት ስለሚል በጠቅላላው ፍጥረታት 22 ናቸው በማለት ይስማማሉ የዕለተ ሠሉስ ፍጥረታት 4 የሚሆኑት እንዴት ነው ቢባል 1) አዝርእት 2) አትክልት 3) እፅዋት 4) በገነት ያሉ አትክልት ናቸው በማለት የዕለተ ማክሰኞ ፍጥረታትን አራት ያደርገዋል፡፡ እነዚህ የማክሰኞ ፍጥረቶች ለሰው ልጆች መገልገያ ይሆኑ ዘንድ ተፈጥረዋል፡፡
መጠለያ ሠርተን ከቀን ሐሩር ከሌሊት ቁር እንከለልባቸዋለን
ታንኳ/ መርከብ/ በመስራት ባሕር ከመስጠም እንድንባቸዋለን
ቢበርደን አቃጥለን እንሞቃቸዋለን፣ ዕቃ ቢጠፋብን አብርተን እንፈልግባቸዋለን
ምግበ ስጋ እንዳርጋቸዋለን
ልብስ ሰርተን እንጠቀምባቸዋለን

#ከአራቱ_ባሕርያት_ተፈጥረዋል_መፈጠራቸው_በምን_ይታወቃል_ቢሉ_በግብራቸው
#ከእሳት፡- እንደ ተፈጠሩ እንጨት ለእንጨት ባሳበቁዋቸው ጊዜ እሳት ይወጣቸዋል
#ከውሀ፡- እንደ ሆኑ ደግሞ ሲቆርጡዋቸው ደም የሚመስል ይፈሳቸዋል ሌላ እንደ ወተት እንደ ውሃ ያለ ነገር ይወጣቸዋልና
#ከነፋስ፡- አየር የተስተካከለ ይሆን ዘንድ አስፈላጊ ናቸው
#ከመሬት፡- ቆርጠው በጣሏቸው ጊዜ ፈርሰው በስብሰው አፈር ሆነው ይቀራሉ

#ከነዚህ_ከአፈጣጠራቸው_አንፃር_ምሳሌነታቸው_ስንመለከት
1) በሥራቸው 2) በጎድናቸው 3) በጫፋቸው የሚያፈሩ

1. #በሥራቸው_የማያፈሩ፡- ሥር የጌታ ምሳሌ ሲሆን ፍሬው ልደቱን፣ ጥምቀቱን አምነው ክብር የሚያገኙ የምእመናን ምሳሌ ነው “አነ ውእቱ ጉንደ ወይን” ዮሐ 15፡5 እ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናቸው እንዲል፡፡
አንድም በሥራቸው አፍርተው ፍሬያቸውን ከወፍ ከጠላት ሸሽገው የሚያስቀሩ በዚህ ዓለም ሲኖሩ ብዙ ትሩፋት ብዙ ምግባር ሰርተው አብልተው አላበላንም አጠጥተው አላጠጣንም፣ አልብሰው አላለበስንም እያሉ ክብራቸውን ሰውረው በወዲያኛው ዓለም የሚጠቀሙት የባለመቶ ክብር አምሳል ናቸው፡፡ ማቴ 25፡34-40
1. #በጎድናቸው_የሚያፈሩ፡- የሐዋርያት ምሳሌ ናቸው፡፡ ፍሬው ሐዋርያት ያስተማሩትን ትምህርት፣ ያደረጉትን ተአምራት አምነው ክብር የሚያገኙ በውሀ ተጠምቀው በመስቀሉ የፀኑ ፍሬአቸውን ከአዕዋፍ ሰውረው የሚኖሩ ናቸው ማቴ 7፡16
1. #በጫፋቸው_የሚያፈሩ፡- የጌታ ምሳሌ ናቸው ፍሬው ጌታ ያስተማረውን ትምህርት ያደረገውን ተዐምራት አምነው ክብር የሚያገኙ የምዕመናን ምሳሌ ናቸው፡፡ አንድም በጫፋቸው አፍርተው ፍሬያቸውን ወፍ ጠርጥሮት ጠላት ለቅሞት የሚቀሩ በዚህ ዓለም ብዙ ትሩፋት ብዙ ምግባር ሠርው ይታይልኝ፣ ይሰማልኝ፣ ይታወቅልኝ ብለው በከንቱ ውዳሴ ተነድተው በወዲያኛው ዓለም ሳይጠቀሙ የሚቀሩ አምሳል ናቸው ከአንድ መሬት ወይንና ሙዝ ሬትና መርዝ ይበቅላሉና እንዲሁም ከአንድ አዳም ሀጥህ እና ፃድቅ ተገኝተዋል፡፡ እነዚህም ታላላቅ ፍሬን፣ መካከለኛ ፍሬን፣ ጥቃቅን ፍሬን ያፈራሉ ጌታችንም በጎልማሳነቱ፣ በወጣትነቱ፣ በህፃንነቱ ዘመን ለሰራቸው ትሩፋቶች ምሳሌ ናቸው፡፡

#በሚያፈሩበት_ወቅት_አንፃር_ምሳሌነታቸው
• ክረምት ለምልመው በጋ የሚደርቁ በዚህ ዓለም በልተው ጠጥተው በወዲያኛው አለም የማይጠቀሙ የእነ ነዌ አምሳል ናቸው ሉቃ 16፡ 19
• ክረምት ደርቀው በጋ የሚለመልሙ በዚህ አለም ተርበው፡፡ ታርዘው መከራውን ተቀብለው በወዲያኛው አለም የሚጠቀሙ ሰዎች አምሳል ናቸው፡፤ የእነ አልዓዘር አይነቱ ሉቃ 16
96 views13:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-26 21:51:21

ስነ ፍጥረት
ክፍል ፫ (ሶስት)

7. #የመላዕክት_አፈጣጥር
መላእክት “እምሀበ አልቦ ሀበቦ” (ካለመኖር ወደ መኖር) ከአምላካዊ ብርሃን ተፈጥረዋል መፅሀፈ “አክሲማሮስ” መላዕክት ከእሳትና ከነፋስ ተፈጥረዋል ይለናል፡፡ ነገር ግን ከእሳትና ከነፋስ ተፈጥረዋል የሚለን ባህሪያቸውን ለመግለፅ እንደሆነ ብዙ ሊቃውንት ይተረጉሙታል ከእሳትና ከነፋስ ተፈጥረው ቢሆንማ እንደ እኛ በበሰበሡና በፈረሱ ነበር ከንፋስ ተፈጠሩ ለምን አለ ቢሉ መላዕክት እንደ ነፋስ ረቂቃን ናቸው አይታዩም እንደንፋስ አይዳሰሱም ከእሳት ተፈጠሩ ለምን አለ ቢሉ እሳት ብርሃናዊ ነው መላዕክትም እንዲሁ ብርሀናውያን ናቸው ስለዚህ ግብራቸውን በማየት ተናግሮዋል አንድም እሳት የማይጨበጥ እንደሆነ መላዕክትም ረቂቅ መሆናቸውን እሳት እንደሚያቃጥል መላዕክትም የእግዚአብሔርን ክብር በሚጋፉ ሰዎች ላይ ቅጣት እንደሚያደርሱ ሲያመለክት ነፋስ ደግሞ ፈጣን ነው መላዕክትም ለተልዕኮ ፈጣን መሆናቸውን ሲያሳይ ነው፡፡ (ዕብ 1፡14) መላዕክት ለምን ተፈጠሩ ቢባል እግዚአብሔርን ለማወደስ /ለማመስገን/ ክብሩንም ለመውረስ ነው ይህ ማለት ግን ጌታ ከዛ በፊት አይመሰገንም ማለት አይደለም፡፡ እርሱ ፍጥረታትን ከመፍጠሩ በፊት በባህሪው ምስጉን ነበር፡፡ ከተፈጠሩ መላዕክት ውስጥ ሳጥናኤል አንዱ ነበር ሳጥናኤል የስሙ ትርጓሜ “አኃዜ መንጦላዕት” (የሥላሴን መጋረጃ) የሚከፍት የሚዘጋ ማለት ነው፡፡ አለቃም ነበር አምላካችንም ከፈጠራቸው በኋላ ተሰውሮባቸዋል አዋቂ አድርጌ ፈጥሬአቸዋለሁና ይሹ ይመርምሩ ሲል ነው፡፡ በዚህ ጊዜ ሳጥናኤል የሀጥያት መሠረት የሆነውን ሀሰት እኔ አምላካችሁ ነኝ በማለት ተናገረ ይህንም ከሱ በላይ መላዕክት እንደሌለ ካረጋገጠ በኋላ ነበር፡፡ አምላካችንን እስክናውቅ እነጠብቅ ሲሉ እነቅዱስ ገብርኤል አንዳንዶቹ ደግሞ አዎ እውነት አማልካችን አንተ ነህ ያሉት አብረው ከሡ ጋር ተጥለዋል፡፡ መፅሐፈ ሔኖክ 11፡4 መላዕክት በመጀመሪያ ያልተፈጠሩበት ምክንያት እንደ ሳጥናኤል ያሉ መላዕክት እንደሚኖሩ ሁሉን የሚያውቅ እግዚአብሔር አስቀድሞ ቢፈጥራቸው ኖሮ ሌሎች ከነርሱ በኋላ የተፈጠሩትን እኛ ፈጠርን ብለው እንዳያስቱ ከእነርሱ ትምክህትን ለማራቅ ሲል ነው፡፡ ወይም አብረን ፈጠርን በማለት እንዳይሰናከሉ ነው፡፡ መላዕክትን በ10 ከተማ በ100 ነገድ አድርጎ ፈጥሮአቸዋል፡፡ ነገድ ስንል ቁጥር ኖሮአቸው አይደለም ለመላዕክት ስፍር ቁጥር የላቸውም በመጀመሪያ በኢዮር በ4 ከፍሎ 40 ነገድ አደረገ

በኢዮር የሚኖሩ
1ኛው አጋዕዝት
2ኛው ከሩቤል
3ኛው ሴራፌል
4ኛው ሀይላት

በመቀጠል ራማን በ3 ከተማ ከፍሎ 30 ነገድ
1ኛው አርባብ
2ኛው መናብርት
3ኛው ስልጣናት

በመቀጠልም ኤረርን በ3 ከተማ ክፍሎ በ30 ነገድ
1ኛው መኳንንት
2ኛው ሊቃናት
3ኛው መላዕክት
በድምሩ በኢዮር 40 ነገድ + በራማ 30 ነገድ + በኤረር 30 ነገድ = በድምሩ 100 ነገድ (መዝ 105፡4 ዕብ 1፡7


#የመላዕክትን_ባህሪይ_በአጭሩ_ስንመለከት
መላዕክት ጾታ የላቸውም አያገቡም፣ አይጋቡም ማቴ 22፡30 መላዕክት ረቂቃን ስለሆኑ አጥንት የላቸውም አይበሉም አይጠጡም አይወልዱም አይወለዱም ሉቃ 24፡30

8. #ብርሃን፡- የዕለተ እሁድ የመጨረሻው ስምንተኛው ፍጥረት ነው ብርሃን የተፈጠረው ከመላዕክት ውድቀት በኋላ ነው የተፈጠረውም በነቢብ /በመናገር/ ነው “ለይኩን ብርሃን” (ብርሃን ይሁን) በማለት አምላካችን ብርሃንን ከጨለማ በኋላ ፈጥሮታል ለምን ቢሉ ብትሹኝ ብትመረምሩኝ እገኛሁ ሲል አንድም ጨለማ የኦሪት ብርሃን የወንጌል ምሳሌ ነውና ኦሪት ከወንጌል እንደምትቀድም ጨለማን ከብርሃን አስቀደመ ምንም እንኳን ጨለማ ቀድሞ ቢፈጠርም ብርሃንን ግን አያክልም ኦሪትም አስቀድማ ብትሰጥም ብርሃን ወንጌል ግን በልጣለች፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም ኦሪትን በሌሊት ወንጌልን በመዓልት መስሎ አስተምሮዋል ሮሜ 13፡12 “በጨለማ ለሚኖር ሕዝብ ታላቅ ብርሃን ወጣለት” እንዲል መፅሐፍ ጌታ 12ቱን ሰዓት ሌሊት 12ቱን ሰዓት መዓልት ሥራ ሰርቶበታል ስለምን ነው ቢሉ በጊዜው ፈቃዱ ቢሆን ፍፃሜውን ግን በኋላ የሚነሱ ቅዱሳን በ24 ሰዓት ውስጥ ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ እያሉ እግዚአብሔርን የማመስገናቸው ምሳሌ ነው፡፡ መዝ 33፡ 1 በተጨማሪም በዕለቱ ብርሃን ቀድሞ ለምን አልተፈጠረም ቢሉ በኋላ ዘመን “ግኖስቲኮች” ከሐዲዎች ስለነበሩ ቀኑን በመጀመሪያ የፈጠረው ደጉ አምላክ ነው ከዛ በኋላ በብርሃን ላይ ክፉ አምላክ ጨለማን ከለሰበት ይሉ ነበርና ነው አስቀድሞ ጨለማን የፈጠረው፡፡
በእለተ እሁድ የተፈጠሩት ከላይ የተመለከትናቸው ስምንት ፍጥረታት ሆኑ ማለት ነው።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

ክፍል 4 ይቀጥላል ……
106 views18:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ