Get Mystery Box with random crypto!

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

የቴሌግራም ቻናል አርማ juwanagibigg — ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ
የቴሌግራም ቻናል አርማ juwanagibigg — ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ
የሰርጥ አድራሻ: @juwanagibigg
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.43K
የሰርጥ መግለጫ

"ይህ ቻናል የጅ/ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉ ሲሆን በጅማ ዋና ግቢ ለሚማሩ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ተማሪዎች በግ/ጉ ሚትላለፉትን መልዕክት፣ት/ቶች፣ስነ ጽሁፎች እና ሌሎችም ለማድረስ የተከፈተ ቻናል ነው።"
ለማንኛውም አስተያየት
👉 @natidula
👉 @MeronW_BAHIRAN
👉 @Mek_J

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-12-24 19:54:57
ታላቅ የምስራች

በአምላካችን መልካም ፈቃድ እነሆ የግቢ ጉባኤያችን የቴሌግራም ቻናል ስራውን በአዲስ መልክ ለመጀመር ዝግጅቱን አጠናቋል!!

ከእናንተ የሚጠበቀው ግብዣውን ለራሳችሁ ተቀብላችሁ ለሌሎችም መጋበዝ ብቻ ነው #Share

ተቀላቅላችሁ በቅርብ ቀን በሚጀመሩት መርሃግብራት ላይ ለመሳተፍ ራሳችሁን እያዘጋጃችሁ በጉጉት ጠብቁን



@JuWanaGibiGG

316 viewsNati Dula, edited  16:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-24 12:23:36 በጎ ፈቃደኛ

ሰላም የእግዚአብሔር ቤተሰቦች።
አምላካችን ቢፈቅድ በግቢ ጉባኤ ተማሪዎች ፤ በሐመረ ኖኅ ቅድስት ኪዳነምህረት ቤተክርስትያን ያሉትን የ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች የሆኑትን የሰንበት ትምህርት ቤቱ ልጆች በቀለም ትምህርት (academically) ለመደገፍ ታቅዷልና ታናናሽ ወንድም እኅቶቻችንን ለማስጠናት ፈቃደኛ የሆናችሁ  ወንድሞች እና እኅቶች በ @Youknowma አናግሩን።


ቀን- በየሳምንቱ ቅዳሜና እሑድ
ሰዓት - ጠዋት 4:00-6:00


ከሙያና በጎ አድራጎት ክፍል

@JuWanaGibiGG
256 viewsትንሣኤ, edited  09:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-23 10:00:49 ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ pinned a photo
07:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-23 10:00:33 "ጋብቻ ለመመስረት ያሰበ አንድ ወጣት ከቤተሰብና ከጓደኞቹ ጋር ተማክሮ ከጨረሰ በኋላ የመንፈስ አባቱ ዘንድ በመሔድ ይህንን ውሳኔውን አስረዳቸው፡፡ ጥበበኛውም አባት ለማግባት ያለውን ጉጉት በልጁ ፊት ላይ እያስተዋሉ አሳቡ መልካም እንደሆነ ገልጸው ማስታወሻና ብዕራቸውን በማውጣት “ስለ ልጅቷ ትንሽ ነገር ንገረኝ” በማለት ጥያቄ አቀረቡለት፡፡ እርሱም እንዲህ አለ “ትውልዷ ከነገስታት ዘር እድገቷም በምቾት መሐል ነው” አለ፡፡ እኚህም አባት በሙሉ ልብ ሆነው በያዙት ማስታወሻ ላይ ዜሮ ጻፉ፡፡
ወጣቱም ስለ ልጅቷ ማብራራቱን ቀጠለ፡- “በጣም ውብ ናት” አለ፡፡ እርሳቸውም ሌላ ዜሮ ጻፉ፡፡ “በጣም ዝነኛ ናት” አለ፡፡ ደግመው ሌላ ዜሮ ጻፉ፡፡ “በጣም ሀብታም ናት” አለ፡፡ ጥበበኛውም ሌላ ዜሮ ጻፉ፡፡
“በጣም ምሁር ናት” አለ፡፡ አሁንም ሌላ ዜሮ ጻፉ፡፡
“በጣም ዘመናዊ ናት” አለ፡፡ ተጨማሪ ሌላ ዜሮ ጻፉ፡፡ በመጨረሻ ግን የረሳውን አንድ ነገር ነገራቸው “ልባም እንዲሁም ሕይወቷ ለእግዚአብሔር ክብርና ምስጋና የተሰጠ ነው” አላቸው፡፡ ጥበበኛውም አባት ፊታቸው ላይ ፈገግታ እየተነበበባቸው አስቀድሞ ከጻፉአቸው ስድስት ዜሮዎች ፊት አንድ ቁጥርን ጽፈው “በል ሂድና አግባት” አሉት፡፡ ወጣቱም በደስታ ከፊታቸው ሄደ፡፡

ጋብቻ ብዙ ጊዜም በሌላው ሰው አካላዊ ገጽታና ውጫዊ አቋም ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ምንም እንኳን በአካላዊ ውበት መማረክ ወደ ፍቅር የሚመራ አንደኛው መንገድ ቢሆን እውነተኛ ፍቅር ግን በአካላዊ ውበት፣ በአፋዊ መስፈርት ከመሸነፍ ያለፈ ነው፡፡ አካላዊ ውበት የጊዜያዊ ጉጉት መገለጫ ሲሆን ፍቅር ግን በሌላው ውስጥ ያለውን መልካሙን ነገር በመሻት ትዕግስትን መሰረት የሚያደረግ ነው፡፡ይህም የትኛውንም ልብ የመንካት፣ በላቀና በጠለቀ መንገድ የመግዛት ጉልበት ነው፡፡ ማንኛውም ሰው በዘመኑ የሚያሳልፋቸው ትልልቅም ይሁን ትንን ውሳኔዎች አሉ፡፡ ሕይወትም በዚህ የዕለት ተዕለት ቋሚ የመምረጥና የመወሰን ተግባር ላይ የተመሰረተች ናት፡፡ ጋብቻ የእኛን ትልልቅ ውሳኔ ከሚፈልጉ ነገሮች አንዱ ነው፡፡ የምናመልከውን እንመርጣለን፣ የምንኖርበትን አካባቢ እንመርጣለን፣ የልባችንን የምናካፍለው ባልንጀራ እንመርጣለን፣ በትዳር አጋር የሚሆነንን እንመርጣለን፣ በአጠቃላይ መሆን የምንፈልገውን እንመርጣለን፡፡ በእርግጥ ምርጫችንን ከምንኖረው በላይ ተጽእኖ ወደ ኑሮአችን የሚያመጣውን መኖራችን ግልጽ ነው፡፡ ነገር ግን በዚህም ውስጥ ከእውነት ጋር ያለን ትስስር ሊደበዝዝ አይገባም፡፡ ምርጫችን ውስጥ ሞትም ሕይወትም፣ ደስታም ሀዘንም፣ ክብርም ውርደትም አለ፡፡ መርጠን ዘመናችንን የእንባ ልናደርገው መብቱ የእኛ ነው፡፡
321 views07:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-22 16:42:06
ሰላመ እግዚአብሔር ይብዛላችሁ።

እንደሚታወቀው ለነዳያን ጾም ማስፈቻና የገና በዓል ማክበሪያ የሚውል መዋጮ (ከ50 ብር ጀምሮ የቻላችሁትን) እየተሰበሰበ ስለሆነ ተቀሳቅሰን በጊዜ ለባች አስተባባሪዎቻችን እንድንከፍል በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።

@JuWanaGibiGG
511 views13:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-21 20:25:56 "በእንተ እግዝእትነ ማርያም ተገብረ ኵሉ ዓለም፤ ፍጥረት ሁሉ ስለ እመቤታችን ማርያም ተፈጠረ፤"
(በዲ/ን በረከት አዝመራው)

***

ሁለት ራእያዊ (apocalyptic) ይዘት ያላቸው ጥንታውያን ድርሳናትን እንጥቀስ። ዕዝራ ሱቱኤል (4 Ezra) እና እረኛው ሔርማስ (The Shepherd of Hermas)።
የመጀመሪያው ፍጥረት ሁሉ ለተመረጠው የእግዚአብሔር ሕዝብ ለቤተ እስራኤል ሲባል ተፈጠረ፤ አሕዛብ ግን ምንም ናቸው ይላል። (6÷54-56) ሁለተኛው ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን በከበረች ሴት አምሳል በራእይ ያያታል፤ ፍጥረት ሁሉ ስለ እርሷ እንደተፈጠረ ይናገራል። በዚህ ላይ የጥንት ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት (ዮስጢኖስ ሰማዕት፣ ኦሪገን፣ አውግስጢኖስ፣ ጠርጡለስ ...) ብዙ ብለዋል።
ጠለቅ ብለን ስንመረምረው ዓለም የተፈጠረው ስለሚጠፉት ሳይሆን ስለሚድኑት ነው። ቤተ ክርስቲያን (መላእክትንም ቤተ እስራኤልንም ባጠቃለለ ሰፊ ትርጉሟ - አቅሌስያ ማለት ጉባኤ እግዚአብሔር ማለት ነውና) የዚህ ማዕከል ነች። እግዚአብሔር ፍጥረትን የፈጠረው ፍቅሩን እና ክብሩን ሊገልጥበት ነው፤ ይህ ደግሞ በፍጽምና ያገኘነው እግዚአብሔር ሰው ሆኖ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ባካፈላት በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ነው። ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ ሙሽራ ነች፤ ክርስቶስ የፈጠረው ዓለም ክብሩን እና ዓላማውን የሚያገኘው ከሚወዳት ከሙሽራው ከቤተ ክርስቲያን የተነሳ ነው።

* *

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ፍጥረት ሁሉ ስለእኛ ተፈጠረ ያሉት ቤተ እስራኤል እና ቤተ ክርስቲያን የሚጋጠሙባት (ሁለቱንም በፍጽምና የምትወክል) ነች። ቤተ እስራኤልን ፍጥረት ስለ እነርሱ እንደተፈጠረ እስኪነገርላቸው ድረስ ከፍ ያደረጋቸው የእሥራኤል ተስፋቸውና ክብራቸው ክርስቶስ ከእነርሱ በሥጋ መወለዱ ነው፤ ይህ ደግሞ እውነተኛዋ 'የእስራኤል ሴት ልጅ - ወለተ እስራኤል በሆነች በቅድስት ድንግል ማርያም የተፈጸመ ነው። የቤተ ክርስቲያን ክብሯ የመለኮት ማደሪያ እና የክርስቶስ አካል መሆኗ ነው፤ ይህ ደግሞ ቀድሞ በፍጽምና የተደረገው በቅድስት ድንግል ማርያም ነው። እንደ እግዚአብሔር ዓላማ ፍጹም እስራኤላዊ እና ፍጹም ክርስቲያን ከድንግል ማርያም በላይ ማን አለ? ከፍጡራን ወገን ቤተ ክርስቲያንን በፍጽምና ሊወክል የሚችል ከድንግል ማርያም በቀር ማን ነው? ማንም!

* *

"ፍጥረት ሁሉ ስለ እመቤታችን ማርያም ተፈጠረ" የሚለውን ከዚህ ጥልቅ መንፈሳዊ (mystical) እይታ አንጻር ማየት ያስፈልጋል። እመቤታችን በብቻዋ አካል ሳይሆን ቤተ ክርስቲያንን ወክላ የተነገረላት ነው ፤ በብዙ የቅዱሳት መጻሕፍት ትርጓሜዎች (ለምሳሌ ሙሴ ያያት እፅ፣ ሰሎሞን የሚዘምርላት ሙሽራ ፣ በራእይ ዮሐንስ ያለችው አውሬው የሚያሳድዳት ሴት) እና በቤተ ክርስቲያን ጸሎቶች ድንግል ማርያምና ቤተ ክርስትያን አንድ ሆነው እናገኛለን። እናታችን ጽዮን አንድም ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አንድም ድንግል ማርያም ናት።
ፍጥረት ስለ እመቤታችን ተፈጠረ ማለት እርሷን ለማምለክ ተፈጠረ ማለት አይደለም፤ ይህን የምትል ቤተ ክርስቲያን እንዴት ልትኖር ትችላለች? (ይህን የምትሉ ሰዎች ኸረ ተው አባቶቻችንን እንዲህ አትናቁ! ጅሎች ይመስሏችኋል እንዴ? ጅሎች ሳይሆኑ በጣም ምጡቆች (mystical) ናቸው!)

በርግጥ "በእንተ እግዝእትነ ማርያም ተገብረ ኵሉ ዓለም፤" የሚለው በቀጥታ ሲተረጎም "ፍጥረት ሁሉ ስለ እመቤታችን ማርያም ተፈጠረ፤" እንጂ "ፍጥረት ሁሉ እመቤታችንን ለማመስገን ተፈጠረ" አይልም። (እኛ ቤት ውስጥ ውርስ ትርጉም ሀገር እያጠፋ ነው ፤ ቀደምት ኢትዮጵያውያን አባቶች ግን እንደዚህ አልነበሩም)
ቢሆንም እንኳ ማመስገን አምልኮ የሚሆነው ለፕሮቴስታንት እና እስላሞች (ሁሉም አይመስሉኝም) እንጂ ለቤተ እስራኤል እና ትውፊታውያን አብያተ ክርስቲያናት አይደለም። ማመስገን ማለትም ግዴታ በቃል መናገር አይደለም፤ ፍጥረት ሁሉ የሚናገር (ነባቢ) አይደለምና። "ፍጥረት ስለ እመቤታችን ማርያም ተፈጠረ" ማለት ድንግል ማርያም በወከለቻቸው ቤተ እስራኤል እና የአዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያን አማካኝነት እግዚአብሔር ሰው ሆኖ ከፍጥረቱ ጋር ለዘላለም ሲዋሐድ ፍጥረታት የተፈጠሩበት ክቡር ዓላማ ተፈጸመ፤ በዚህም የፍጥረታት ደስታ ሆነ ማለት ነው።

አንድ ሰው ኦርቶዶክስ ክርስቲያንም ሆኖ እነዚህ በጣም ረቂቅ አገላለጾች ካልገቡት ብዙ መጨነቅ አይገባውም፤ እስኪገቡት ድረስ በመሠረታዊው አስተምህሮ አምኖ መኖር ይችላል። ያልገባኝ ሁሉ ስህተት ነው ማለት ግን ትዕቢት ነው!

በሌላ በኩል ፤ ቤተ ክርስቲያን መናፍቃን ምእመናንን ለማወናበድ እና ለማጠራጠር የሚጠቀሙባቸውና ብዙ ማብራሪያ ከመፈለጋቸው የተነሳ በየጊዜው ሥራ የሚፈጥሩባትን እንዲህ ያሉ ጠጣር ንባባትን ከዘወትር አገልግሎት አውጥታ በተቻለ መጠን ግልጽ የሆኑ እና ለአብዛኛው ምዕመን የሚሆኑ ንባቦችን የያዙ የመጻሕፍት ቅጅዎች (abridged versions) ማውጣት ይኖርባታል ፤ አጥንት መቆርጥም የሚችሉ ግን በሁሉም ይራቀቁ። የግብጽ ቤተ ክርስቲያን እና ሌሎች ጥንታውያን አብያተ ክርስቲያናት እንዳደረጉት። ይህ እንደ ልጅነታችን በትህትና የምናቀርበው ሐሳብ ነው!
333 views17:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-18 20:02:23 ሰላም የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እንደምን አላችሁ?
ከነገ ሰኞ 10/04/2015 ጀምሮ የሚካሄድ የተተኪ መምህራን ስልጠና ስላለ ተቀሳቅሰን እንገኝ። ወንድሞች ብቻ ሳይሆን እኅቶችም ተገኝታችሁ እንድትሰለጥኑ እናሳስባለን።

ሰዓት ጠዋት 12:00 - 1:00

በሐመረ ኖኅ ቅድስት ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን
447 views17:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-16 15:59:11
ባች የሆነ ሁሉ ሊያመልጠው የማይገባ ስልጠና!!!!

ያልሰማ እንዳይኖር በአካልም በsocial mediaም ተቀሳቅሰን እንሳተፍ። ስለ አገልግሎታችን በቂ እውቀት አግኝተን ፤ ተግተን ለመስራትም አላማ ሰንቀን እንመለሳለን።

የሚቀርም የሚያረፍድም እንዳይኖር።

ቅዳሜ ከ3:30 - 5:00

በሐመረ ኖኅ ቅድስት ኪዳነምህረት ቁጥር 1 አዳራሽ
492 views12:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-16 10:34:15
"ዕቅበተ እምነት"

በጉጉት ስንጠብቀው የነበረ መርሐግብር!!
ለብዙ ጥያቄዎቻችን መልስ የምናገኝበት ነውና ወንድም እኅቶቻችንን ይዘን ሳናረፍድ እንገኝ።

በሐመረ ኖኅ ቅድስት ኪዳነምህረት ቤተክርስትያን

ቅዳሜ 08/04/2015 ከ8:30 - 10:30

በቋንቋ እና ልዩ ፍላጎት ክፍል የተዘጋጀ።
653 views07:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-16 08:50:37
ላልሰሙት ወንድሞች እና እኅቶች እያሰማን ተቀሳቅሰን እናጥና።
397 views05:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ