Get Mystery Box with random crypto!

all in one hawasa

የቴሌግራም ቻናል አርማ fetazonee — all in one hawasa A
የቴሌግራም ቻናል አርማ fetazonee — all in one hawasa
የሰርጥ አድራሻ: @fetazonee
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 130
የሰርጥ መግለጫ

@ https://t.me/fetazonee

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-10-02 19:49:22 " ኢትዮጵያ ከፍላዋለች ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ አክብሮታል " - ድምፃዊት ትዕግስት አፈወርቅ

በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው ድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ እህት የሆነችው ድምፃዊት ትዕግስት አፈወርቅ አሁን ላይ በስደት #በካናዳ_ሀገር የምትገኝ ሲሆን የወንድሟን ህልፈት በሰማችበት ወቅት እራሷን ስታ ሆስፒታል እንደነበረች ተናግራለች።

ድምፃዊት ትዕግስት ፤ የወንድሟን ህልፈት ተከትሎ የኢትዮጵያ ህዝብ ፣ የኢትዮጵያ መንግስት ላሳየው ልዩ ክብር ምስጋናዋን አቅርባለች።

ወንድሟን እስላም ፣ ክርስቲያኑ ፤ ኦሮሞው ፣ ትግራዩ ፣ አማራው አንድም ሳይለያይ አልቆሶ በክብር መቀበሩን የገለፀችው ትዕግስት ባየችው ነገር እንደተፅናናች ነገር ግን በኢትዮጵያ ውስጥ እየጠፋ ያለው የሰው ህይወት ይቆም ዘንድና ሁሉም ወደ ፍቅር እንዲመለስ እያለቀሰች ተማፅናለች።

ድምፃዊት ትዕግስት አፈወርቅ ፦

" ... ወንድሜን ኢትዮጵያ ከፍላዋለች። እግዚአብሔር ይመስገን የኢትዮጵያ ህዝብ አክብሮታል ፤ የኢትዮጵያ መንግስት አክብሮታል።

እንደ ንጉስ በክብር ተቀብሯል።

ፌንት አድርጌ ሆስፒታል ነበርኩኝ ፤ ወንድሜ ለኔ ልጄ ነው ፤ የስደት ጓዴ ነው፤ ሁሉ ነገሬ ነው። የጀግና ሞት ነው የሞተው፤ እንደ ንጉስ ነው የተቀበረው።

የማስተላልፈው መልዕክት ፤ ወንድሜ እንዲሁ እንደ ንጉስ እንደተቀበረ  ፤ #ኢትዮጵያን እንዳለ እንደዘፈነ ፤ ኢትዮጵያን እንደወደደ የክብር ሞት ነው የሞተው የኢትዮጵያ ህዝብም ብድሩን መልሶለታል።

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ ፤ ኢትዮጵያን ሰላም ያድርጋት።

ነገር ግን አንድ የሚያመኝ ነገር ወንድሜ እንዲህ እንደ ንጉስ ተከብሮ ተቀብሮ እንዲህ አንጀቴ ፣ ልቤ የተቆረጠ ፤ የሚያልቀው ህዝብ ፣ ምንም በማያውቀው ፣ ደጉ ባለሀገሩ ፣ ምስኪኑ የሚጨፈጨፈውስ ... ስለነሱ ነው መልዕክቴ።

የኢትዮጵያ ህዝብ እንደድሯችን #አንድ ልንሆን ይገባል፤ ሞት ሊቆም ይገባል። እኔ ወንድሜ በክብር ተቀብሮ እንደዚህ ያመመኝ ተዋግቶ በማያውቀው ተጋድሎ የሚሞተው ህዝብ ፤ ለእሱ ህዝብ ሞት ሊቆም ይገባል ነው መልዕክቴ።

ወንድሜማ እንደ ንጉስ ነው የተቀበረው ግን እንደዛም ሆኖ አንጀቴ ተቆርጧል። ማዲንጎ ኢትዮጵያን ነው ያሳየው እስላም፣ ክርስቲያኑ ፤ ኦሮሞው ፣ ትግራዩ ፣ አማራው ሁሉ አልቅሶ ነው የቀበረው። የኢትዮጵያ ህዝብ ደግ ህዝብ ነው።

እባካችሁ ወገኖቼ ፣ ወንድሜ እንዲህ በክብር ተቀብሮ እንኳን አዝኛለሁ አንጀቴ ተቆርጧል፤ እያየች ልጇ የሚገደልባት እናት አባት ፣ እህት ወንድም የሚያልቅው እባካችሁ ... እባካችሁ ሞት ይቁም ኢትዮጵያ ላይ ፤ እግዚአብሔርን አምላክን ፍሩ ፤ ሁላችንም እንፍራ ወደ ፍቅር እንምጣ።

ማዲንጎ ይጠበቃል ዱብእዳ ነው የሆነብኝ፤ ቀኝ እጄ ነው የተቆረጠው ... በሰው ሀገር ፌንት ነው ያደረኩት ግን የኢትዮጵያ ህዝብ አፅናናኝ ፣ የኢትዮጵያ መንግስት እንደዛ ሲሆንለት ሳይ ፣ ህዝቡ እንደዛ ሲወጣ አንድ አደረጋት ፣ #አንድ_ናት_ኢትዮጵያ እያለ ዘፍኖ ቀብሩ ላይ እስላም ፤ ክርስቲያን ሳይል ሁሉም አንድ ሆኖ ኦሮሞው ፣ ትግራዩ አንድ ሆኖ ነው አልቅሶ የቀበረው እናም ይሄ ህዝብ ፍቅር ነው የሚያስፈልገው ፤ ለእሱ ስንል መታሰቢያነቱ ለወንድሜ ይሁን አንድ ያድርገን እባካችሁ ፤ #ሞት_ይብቃን !! "

(ድምፃዊት ትዕግስት አፈወርቅ ፤ በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሬድዮ ላይ ለሚሰራጨው " ታዲያስ አዲስ " ለተሰኘው የሬድዮ ዝግጅት ከሰጠችው ቃል የተወሰደ)

https://t.me/fetazonee
9 views16:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-02 19:48:10 የተመድ ፀጥታ ም/ቤት በኢትዮጵያ ገዳይ መክሯል ?

ትላንት ለሊት የተመድ ፀጥታው ምክር ቤት በኢትዮጵያ ጉዳይ #ኢመደበኛ_ዝግ ስብሰብ ያደርጋል ተብሎ ነበር። ስብሳባው ስለመደረግ አለማደረጉ እስካሁን በይፋ የሚታወቅ ነገር የለም።

ስለዚህ ስብሰባ የሚታወቀው ነገር የሚከተለው ነው ፦

- ግጭት ዳግም ካገረሸ በኃላ መስከረም 2 (እኤአ) አይርላንድ ከአልባኒያ ፣ ፈረንሳይ፣ አሜሪካ፣ ዩናይትድ ኪንግደም (UK) ጋር በመሆን ምክር ቤቱ በኢትዮጵያ ጉዳይ በክፍት እንዲሰብሰብ ጠይቃ ነበር። አይርላንድ " በኢትዮጵያ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በግጭት ምክንያት በረሃብ እየተሰቃዩ በመሆናቸው ለሰብአዊ ዕርዳታ እንቅፋት የሚሆኑ ነገሮች በጣም ያሳስበናል " በሚል ነው ክፍት የሆነ ስብሰባ እንዲካሄድ ጥያቄ አቅርባ የነበረው፤ ሀገሪቱ ሁሉም ወገኖች ግጭት እንዲያቆሙና በአፍሪካ ህብረት (AU) ወደሚመራው የሰላም ንግግር እንዲመለሱ እንደምትፈልግ ነው የገለፀችው።

- የክፍት ስብሰባ ጥያቄው በ #A3 ሀገራት ማለትም #በኬንያ፣ #በጋቦን እና #በጋና ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል። ሀገራቱ ይህን የስብሰባ ይዘት የተቃወሙ ሲሆን የተስማማቱ መደበኛ ያልሆነ ስብሰባ (IID) እንዲካሄድ ነው። ይህም ኢትዮጵያ የምትመርጠው አይነት የስብሰባ ይዘት እንደነበር ተነግሯል።

መደበኛ ያልሆነ ስብሰባ (IID) ማለት ምንድነው ? IID መደበኛ ያልሆነ ዝግ ስብሰባ ሲሆን የምክር ቤት አባላት ያልሆኑትን እንዲሳተፉ የሚያስችልም ነው። የዚህ  የስብሰባ ይዘት የስብሰባ መዝገቦች የሌሉት ሲሆን በም/ቤቱ ወርሃዊ የስራ መርሃ ግብር ውስጥም አይካተትም።

- አይርላንድ ሁሉም ወገኖች በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን ጦርነት እንዲያቆሙ እና ለተቸገሩ ሰዎች ሁሉ ሰብአዊ አገልግሎት እንዲያገኙ የሚጠይቅ ረቂቅ ጋዜጣዊ መግለጫ አሰራጭታ ነበር ሆኖም ግን #A3 ፣ #ቻይና እና #ሩሲያ በረቂቅ ጽሑፉ ላይ ለመሳተፍ ፈቃደኛ አልነበሩም። ሀገራቱ መግለጫውን ከስብሰባው በኃላ ከግምት ውስጥ ማስገባትን ነው የመረጡት ተብሏል። በዚህም በመግለጫው ላይ የነበረ ውይይት ባለበት እንዲያዝ ተደርጓል።

- ትላንትና ይካሄዳል የተባለው እና እስካሁን ተካሂዶ ስለመሆን አለመሆኑ በይፋ ያልታወቀው የተ.መ.ድ. ፀጥታ ምክር ቤት የIID ስብሰባ ላይ የመንግስታቱ ድርጅት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሃና ተቴህ ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሎ ነበር። የአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ ኦሉሴጉን ኦባሳንጆም አጭር መግለጫ እንዲሰጡ ተጋብዘው እንደነበር ታውቋል ፤ በስብሰባው ላይ ኢትዮጵያ እንድትሳተፍም ተጋብዛ ነበር።

- ትላንት ለሊት በተያዘው እቅድም መሰረት ኢመደበኛ ስብሰባው (IID) መካሄዱ ከተረጋገጠ የሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ዳግም ካገረሸ በኃላ የፀጥታው ም/ቤት በኢትዮጵያ ጉዳይ ለመጀመሪያ ጊዜ የተነጋገረበት ነው የሚሆነው።

መረጃው ከSCR ፣ ከተመድ የአይርላንድ እና ኖርዌይ ተልዕኮ ፅ/ቤት የተሰባሰበ ነው።

https://t.me/fetazonee
9 views16:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-02 05:57:17 ከታሪፍ ውጪ አትክፈሉ !

" የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች ላይ ምንም አይነት የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ አልተደረገም " - የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር

ከቀናት በፊት የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ ተግባራዊ ማድረጉ ይታወቃል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ ፤ የታለመለት የነዳጅ ድጎማ ተጠቃሚ የሆኑ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎች በሚጠቀሙት ነዳጅ ላይ ምንም ዓይነት የዋጋ ጭማሪ አልተደረገም።

አነስተኛ ገቢ ያላቸው ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ በተዘረጋው ብሔራዊ የታለመ የነዳጅ ድጎማ አሠራር ታቅፈው ህዝቡን እንዲያገለግሉ የተመረጡት የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎች በሚጠቀሙት ነዳጅ ላይ በ2ኛው ምዕራፍ ምንም ዓይነት የዋጋ ጭማሪ አልተደረገም።

ይህም ማለት ቀደም ሲል ይቀርብ በነበረበት የነጭ ናፍጣና ኬሮሲን ዋጋ ብር 40.86 ፣ የቢንዚን ብር 41.25 ነው እየቀረበ የሚገኘው።

#በታለመለት_የነዳጅ_ድጎማ_የታቀፉ_ተሽከርካሪ አሽከርካሪዎች ቀደም ሲል በወጣላቸው ታሪፍ ሀብረተሰቡን እንዲያገለግሉ ማሳሰቢያ የተሰጠ ሲሆን ህብረተሰቡ ይህን አውቆ መንግስት ካስቀመጠው ታሪፍ ውጪ ባለመክፈል ተባባሪ እንዲሆን ተጠይቋል።

በተጨማሪም ኃላፊነታቸውን በተገቢው መንገድ የማይወጡ አሽከርካሪዎች ሲያጋጥሙ በየደረጃው ላሉ የፀጥታ አካላት #ጥቆማ በመስጠት ህብረተሰቡ መብቱን እንዲያስከብር በትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር መልዕክት ተላልፏል።
https://t.me/fetazonee
16 views02:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-01 21:14:12 #ይቺ_ናት_ኢትዮጵያ !!

የዘር ፓለቲካ ዘልቆ የሚታይባት ወንድማማችነታችን ተረስቶ ከአንድ እናት ሀገር ኢትዮጵያ መፈጠራችንን እረስተን ፣ፈርሀ እግዚአብሔርን ዘንግተን መገዳደላችንን ቀጥለናል አሁንም አለን ።በዚሁ ከቀጠልን ግን ኢትዮጵያስ የምትባል ሀገር ትኖር ይሆን ?

መቼ ይሆን ግን ማብቂያው ?
መፅሐፍ አገብጬ ፣አባቶቼን ጠይቄ፣ ጎግል ጎልጉዬ ...መልስ ያጣሁለት ጥያቄ ነው ።
መቼ ነው ፖለቲከኞች ህዝባቸውን ለእኩይ ተግባር መጠቀማቸውን የሚያቆሙት ? መቼ ነው የነሱን ልጅ በሞቀ ቤት በአውሮፓ እና አሜሪካ አስቀምጦ እዚህ ያለውን ባዶ ሆዱን የሚያድረውን ወጣት መጠቀሙን የሚያቆመው ? መቼ ነው አንድነታችን የሚመለሰው ? መቼ ነው ወጣቱ የእናትን ጓዳ ሊጥ መድፋት ትቶ ለእናቱ ንፁህ እንጀራ የሚያመጣው ? መቼ ነው ...? መቼ ነው ....? መልስ ያላገኘሁላቸው ጥያቄዎች ።

አስታውሳለሁ በአንድ ወቅት የአማርኛ ቋንቋ መምህራችን እንዲህ ብላን ነበር ''አንድ አዛውንት ሲሞት አንድ ቤተመፃህፍት እንደተቃጠለ ይቆጠራል'' ... እና እስካሁን ስንት ቤተመፃህፍት ፣ስንት የእውቀት አባቶችን አተን ይሆን ?

ከሀገራችን ሰንደቅዓላማ ይልቅ ሰባራ ሰንደቅ ከልካይ ሳይኖራቸው ሲውለበለቡ አያለሁ ያሳዝናል ኢትዮጵያን መርሳታችን ያሳዝነኛል።
''እዛ ጋር ጤፍ ቆጠራ
እዚህ ጋር ቃል ምንዘራ
ሀገር ምድሩ ባንቺ እየተጠራ''

ስኬት ያለ ውድቀት ማግኘት እንደማይቻለው ይህም ግዜ አልፎ የኢትዮጵያን ትንሳኤ እንደምናይ እርግጠኛ ነኝ ምክንያቱም የንፁሀን ነፍስ ወደ ፈጣሪዋ አብዝታ ስለምትጮህ ሁሉም የዘራውን ያጭዳልና ።

''የአሜሪካው ከመጣ አለን መመለሻ
የሱዳኑ ቢመጣ አለን መመለሻ
እኛን ያስቸገረን ሀበሻ ላበሻ''

ከፊት ነበርን አሁን ግን ከሁሉም ኃላ ቀርተናል ወደ ቀድሞ አንድነታችን እና ስልጣኔአችን የሚመልሰን የኢትዮጵያ ሙሴን ፈጣሪ እንደሚልከልን አምናለሁ ።

''ሰላም ፣አንድነት እና ፍቅር ፈጣሪ አብዝቶ እንዲያድለን ከልብ እመኛለሁ ።''
https://t.me/fetazonee
18 views18:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-01 21:14:11 በዓመት አንድ ቀን የሚውለው እድሜ ጠገቡ ገበያ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ መስለማርያም ቀበሌ በዓመት አንድ ቀን ብቻ የሚውል ገበያ አለ፡፡

የአካባቢው ህብረተሰብ በአመት አንድ ጊዜ የሚገበያይበት ይህ ገበያ እድሜ ጠገብ መሆኑም ይነገርለታል።

“የሩፋኤል ገበያ” በመባል የሚታወቀው ይህ አመታዊ ገበያ በየአመቱ ጳጉሜን 3 ቀን ይውላል።

ዓመትን ጠብቆ የሚውለው ይህ ገበያ ታዲያ ከግብይት ባለፈ ማህበራዊ እና ሐይማኖታዊ ገጽታዎችን የተላበሰ ነው።

ከ700 ዓመታት በላይ ዕድሜ እንዳስቆጠረ የሚነገርለት “የሩፋኤል ገበያ”÷ በዘመኑ የነበሩት ነገሥታት እንዳስጀመሩት ይታመናል፡፡

በአካባቢው ነዋሪዎች ዘንድ የሚናፈቀውና የሚወደደው ይህ ገበያ፥ ነዋሪዎች ለመንግሥት ግብር እንዲከፍሉ ለማመቻቸት በማሰብ ሳይጀመር እንዳልቀረም በአፈ ታሪክ ይነገራል፡፡

የዕለቱ የገበያ ውሎ ከገበያነት ባለፈም የአመቱን ገበያ እና የሸቀጦች ዋጋ ያመላክታል የሚል ዕምነት በህብረተሰቡ ዘንድ መኖሩም ነው የሚነገረው።

በዕለቱ በገበያው ላይ ለሽያጭ የቀረበ ቁሳቁስ፣ ዕቃ፣ የቁም እንስሳት ወይም ሸቀጥ ከተወደደ÷ ዓመቱን ሙሉ ገበያው ውድ ይሆናል ይባላል።

በአንጻሩ በዕለቱ ግብይት የዋጋ ቅናሽ ከታየ፥ ቅናሹ ዓመቱን ሙሉ ይዘልቃል የሚል ዕምነት በህብረተሰቡ ዘንድ አለ።

በስፍራው በዕለቱ ከሚውለው ገበያ ባለፈ የቅዱስ ሩፋኤልን ዓመታዊና ሐይማኖታዊ በዓል ለማክበር በርካታ ምዕመናን በስፍራው በመሰባሰብ ሐይማኖታዊ ስርአት ይከውናሉ፡፡

የሩፋኤል ገበያ ሻጭና ሸማችን እያገናኘ የሰውን ዕለታዊ ፍጆታ ብሎም ፍላጎት ከመሸፈን አልፎ ሌላም ሲሳይ አለው ነው የሚባለው፡፡

መረጃዎች እንደሚያመላክቱት ለአቅመ አዳምና ሔዋን የደረሱ ወጣቶች በትዳር ተጣምረው ለመኖር የሩፋኤል ገበያን እንደ መልካም አጋጣሚ ይጠቀማሉ፡፡

እናም በእይታ የተፈላለጉ ወጣቶች ከገበያው ዕቃ ሸምተው፥ ቀልባቸው ያረፈበትን አጭተው፤ ውሃ አጣጫቸውንም ይዘው ይመለሳሉ።

የወረዳው ባህልና ቱሪዝም ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ቅመም አሽኔ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ “አካባቢውን የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ ከደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ጋር በጋራ እየተሠራ ነው”፡፡

የአካባቢውን ታሪካዊነት የሚያሳዩ የቤተ መንግሥት ፍርስራሾች እና ጥንታዊ ቅርሶች መኖራቸው አካባቢውን ለማልማት መልካም ዕድል ነው ያሉት ኃላፊዋ÷ የሰሜንሸዋ ዞንም አስፈላጊውን ሁሉ እገዛ እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡

በገበያው ዕለት የአካባቢው ነዋሪዎችን ጨምሮ ከአጎራባች ወረዳዎች የሚሰባሰቡ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አንድም ለመጎብኘት አንድም ደግሞ ለመገበያየት በቦታው እንደሚገኙ ወይዘሮ ቅመም ይናገራሉ፡፡

በገበያው÷ የቁም እንስሳት፣ የእርሻ መሣሪያዎች፣ የፋብሪካ እና የግብርና ምርት ውጤቶች እንዲሁም የእንስሳት ተዋጽኦ ይቀርባሉ፡፡
https://t.me/fetazonee
21 views18:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-01 15:03:34
#ATTENTION

ወልድያ !

ከወልድያ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ም/ቤት ነባራዊ ሁኔታን ታሳቢ በማድረግ ተጨማሪ ክልክለዎችን አስተላለፈ።

የፀጥታ ምክር ቤቱ ከዚህ ቀደም የከተማውን ወቅታዊ ሁኔታ መነሻ በማድረግ  ክልከላዎችን ማስቀመጡ ይታወሳል።

ሆኖም ነባራዊ ሁኔታ በማየት ተጨማሪ ክልከላዎች በማስፈለጉ ከነገ መስከረም 22 2015 ዓ.ም ጀምሮ  የሚተገበሩ ተጨማሪ ዉሳኔዎችን ማሳለፉን ገልጿል።

በዚህ መሰረት :-

1. ከ ነገ መስከረም 22  ቀን ጀምሮ ጫት ወደ ከተማዋ ማስገባት በጥብቅ ተከልክሏል።

2. ከነገ ጀምሮ ጫት መቃም ሆነ ማስቃም በጥብቅ ተከልክሏል።

3. ከነገ ጀምሮ የጎዳና ላይ ቁማር (ቢንጎ የመሳሰሉትን) መጫወት ተከልክሏል።

ከላይ የተዘረዘሩትን ውሳኔዎች ጨምሮ ከዚህ በፊት የተላለፉ ዉሳኔዎችን ማንኛውም አካል የማክበርና ኃላፊነቱን የመወጣት ግዴታ አለበት የተባለ ሲሆን ውሳኔዎቹን የማያከበር ግለሰብም ሆነ ድርጅት ላይ የፀጥታ መዋቅሩ አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል።

መረጃው ከከተማው ኮሚኒኬሽን የተገኘ ነው
@fetazonee
26 viewsedited  12:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-01 13:56:08 Selam beteseboc endet nachulign ena alehulacu lenate yitekimal yalikutin endhu yasitemiral yalikutin mereja tef tef biye bemakireb lay egegnalewu enate demo group lay memeber add be mareg ina linkun share bemareg endititebaberugn be akibirot eteyikalewu melikam ken yihunilachu selamacu yibiza
https://t.me/fetazonee
https://t.me/Tik454 group
https://youtube.com/channel/UCrtjN7XAj_-j6Eao3iAfT3Q you tube
29 viewsedited  10:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-01 13:54:46 #ብሔራዊ_ፈተና

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከቀናት በኃላ መሰጠት ይጀምራል።

ፈተናው በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚሰጥ ይታወቃል። ተማሪዎች መብታቸው ፣ ግዴታቸው፣ ወደ ዩኒቨርሲቲ ይዘው መሄድ የሚችሉት እና የተከለከሏቸው ነገሮችን ከላይ በምስሉ በዝርዝር ተቀምጧል።

በተጨማሪም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የጊዜ ሰሌዳ እንደሚከተለው ቀርቧል።

➤ የመጀመሪያ ዙር (የሶሻል ሳይንስ) ፦

ከመስከረም 26 - 28 (ተፈታኞች ወደ ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ)

መስከረም 29 (ኦረንቴሽን ይሰጣል)

ከመስከረም 30 - ጥቅምት 2 (ፈተና ይሰጣል)

ከጥቅምት 3 - ጥቅምት 4 (ተፈታኞች ወደየአካባቢያቸው ይመለሳሉ)

➤ ሁለተኛ ዙር (የተፈጥሮ ሳይንስ) ፦

ከጥቅምት 5 - ጥቅምት 6 (ተፈታኞች ወደ ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ)

ጥቅምት 7 (ኦረንቴሽን ይሰጣል)

ከጥቅምት 8 - ጥቅምት 11 (ፈተና ይሰጣል)

ከጥቅምት 12 - ጥቅምት 13 (ተፈታኞች ወደየአከባቢያቸው ይመለሳሉ)

(ትምህርት ሚኒስቴር / የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት)
https://t.me/fetazonee
27 views10:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-01 13:52:53
28 views10:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-01 10:27:27 መፈንቅለ መንግስት - በቡርኪናፋሶ !

" መፈንቅለ መንግሥት " በማደረግ ስልጣን የያዙት የቡርኪናፋሶ መሪ መፈንቅለ መንግሥት ተደረገባቸው።

የቡርኪናፋሶ የጦር መኮንኖች ትላንት በብሔራዊ ቴሌቪዥን ላይ ቀርበው የአገሪቱ ወታደራዊ መሪ ሌተናል ኮሎኔል ፖል ሄንሪ ዳምቢባ ከሥልጣን መወገዳቸውን አስታውቀዋል።

የቡድኑ መሪ ሻምበል ኢብራሂም ትራኦሬ የሚባሉ ሲሆን ባሰሙት ንግግር የወታደራዊ መሪ ሌትናል ኮሎኔል ዳምቢባ ከመሪነት የተወገዱት፣ በአገሪቱ የሚንቀሳቀሱትን አማጺያንን በአግባቡ መቆጣጠር አልቻሉም በሚል ነው። ላልተወሰነ ጊዜ ሁሉም ድንበሮች ዝግ እንደሚሆኑና የትኛውም አይነት ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ መከልከሉን አሳውቀዋል።

አሁን ከሥልጣን መወገዳቸው የተገለጸው ዳምቢባ የሚመሩት ቡድን ባለፈው ዓመት ጥር ላይ ነበር በሕዝብ የተመረጠውን አስተዳደር በመፈንቅለ መንግሥት ገልብጦ ወደ ሥልጣን የመጣው። በወቅቱ ወታደራዊ ቡድኑ መንግሥት የአማፂያንን ጥቃት ማስቆም አልቻለም በሚል ነበር መፈንቅለ መንግሥት ያደረገው።

ትናንት ምሽት ላይ ከ20 በላይ የሚሆኑ አብዛኞቹ ፊታቸው የተሸፈነ የታጠቁ ወታደሮች በብሔራዊው ቴሌቪዥን ላይ ቀርበው የቡድኑ መሪ ናቸው በተባሉት ትራኦሬ የተፈረመ መግለጫ አቅርበዋል።  
መግለጫው ፤ " እየተባባሰ የሚሄድ ችግር በገጠመን ጊዜ ዳምቢባ በደኅንነት ጉዳዮች ላይ እንዲያተኩሩ ለማድረግ በተደጋጋሚ ሞክረናል፤ ነገር ግን የዳምቢባ ተግባር ለማድረግ ካቀድነው ውጪ በመሆኑ አሁን ከሥልጣን እንዲወገድ ወስነናል " ብሏል።

ከዚህ በኋላም በመላዋ አገሪቱ ከምሽት 3 ሰዓት እስከ ንጋት 11 የሚቆይ የሰዓት እላፊ ገደብ የተጣለ ሲሆን፣ ሌተናል ኮሎኔል ዳምቢባ የት እንዳሉ የታወቀ ነገር የለም ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
https://t.me/fetazonee
34 views07:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ