Get Mystery Box with random crypto!

የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት

የቴሌግራም ቻናል አርማ aasundayschool — የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት
የቴሌግራም ቻናል አርማ aasundayschool — የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት
የሰርጥ አድራሻ: @aasundayschool
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5.84K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ልሳን ነው።

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-30 10:32:30

706 viewsBereket kebede, 07:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 13:15:02
1.0K viewsBereket kebede, 10:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 13:14:45 ✥••••✥••••✥••••●✞ ● ✞ ●✞ ●••••✥••••✥••••✥✞ ●••••✥••••✥••••✥
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ሰ/ት/ቤት 60ኛ ዓመት የምሥረታ በዓሉን ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የአዲስ አበባ እና ጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀጳጳስ እንዲሁም የአዲስ አበባ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤና የቅድስት ሥላሴ ዩንቨርስቲ የቦርድ ሰብሳቢ ፤ ብጹዕ አቡነ እንጦንስ የምዕራብ ሐረርጌ እና የአፋር አህጉረ ስብከት ሊቀጳጳስ ፤ የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ገነት ክብሩ እንዲሁም የደብሩ ሰ/ት/ቤት አባላትና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት በድምቀት ተከበረ።

በምሥረታ በዓሉ ዕለቱን የተመለከተ ያሬዳዊ ወረብ በሰ/ት/ቤቱ አባላት ፤ ቅኔ በደብሩ የቅኔ ሊቅ የቀረበ ሲሆን እንዲሁም ሰፊ ትምህርተ ወንጌልም ተሰጥቷል።

ሰ/ት/ቤቱ ሲመሠረት ጀምሮ ላለፉት 60 ዓመታት ያለመታከት በድካምና በብዙ ውጣ ውረድ ያገለገሉትን  አቶ አሰፋ ተስፋዬን ጨምሮ በልዩ ልዩ ዘርፍ አገልግሎቱን ለደገፉ ድርጅቶችና በርካታ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ለሚኖሩ ግለሰቦች እንዲሁም ለደብሩ ሰ/ጉ/ጽ/ቤት ፣ ደብሩን ከአሁን በፊት ሲያስተዳድሩ ለነበሩ የቀድሞ አስተዳዳሪዎችና በአሁኑ ስዓት በማስተዳደር ላይ ለሚገኙት መልአከ ገነት ክብሩ የምሥጋና የምሥክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።

በተቋም ደረጃ ኢትዮ ኤፍ ፣ ፋና ትሬዲንግ ፣ አርኪ እና አኳ አዲስ ውሃ ፣ ማኅበረ ቅዱሳን ፣ ኢ/ር ደረጄና ድርጅቱ እንዲሁም ሚልንየም ማተሚያ ቤት ፣ በመርሐ ግብሩ ላይ ምሥጋና ከተቸራቸው መካከል ተጠቃሾች ናቸው።

ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ ባደረጉት ንግግር "የዛሬ 60 ዓመት ህፃን ዛሬ ደግሞ ለሽምግልና ዕድሜ ለደረሰው የመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ/ክ ሰ/ት/ቤት 60ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል። በሰ/ት/ቤት ደረጃ 60 ዓመታትን በፅናት መቀጠል ቀላል አለመሆኑን ገልጸው ይህንን ዕድሜ ያስቆጠረው ሰ/ት/ቤት አንጋፋዎችን ያፈራ አንጋፋ ፣ በተምሮ ማስተማር ረገድም ከአዲስ አበባ ውጭ ላሉ ወጣቶች ተከታታይ የሆኑ የተልእኮ ትምህርት እየሰጠ የሚገኝ እና ለሌሎች ሰ/ት/ቤቶች ጥሩ ምሳሌና ሞዴል የሆነ አምሳለ ኮሌጅ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

ብፁዕነታቸው አክለውም  ሰ/ት/ቤት ለቤተክርስቲያን የችግኝ ጣቢያ ነው፣ ቤተክርስቲያን ልጆቿን ነገ  ለምትሰጣቸው ልዩ ልዩ ኃላፊነቶች እየተንከባከበች የምታቆይበት ሥፍራ በመሆኑ ትልቅ ትኩረት ሰጥተን ልንጠብቀውና ልንከባከበው እንዲሁም አስፈላጊውን ሁሉ ልናደርግ ይገባል ሲሉም አሳስበዋል።

የምዕራብ ሀረርጌ እና የአፋር አህጉረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብጹዕ አቡነ እንጦንስም "እኔ ሰ/ት/ቤቱን የማውቀው  ከረጅም ዓመት በፊት ነው ፣ ብዙ ሊቃውንትን ያፈራ ሰ/ት/ቤት ነው ሲሉ ምሥክርነታቸውን ሰጥተዋል።

በተያያዘ ዜናም ሰ/ት/ቤቱ የምሥረታ በዓሉን አስመልክቶ ለሕጻናትና አብነት ተማሪዎች መማሪያ የሚሆን እና 60 ሚሊየን ብር ወጪ የሚጠይቅ #G+4 ሕንጻ ለመገንባት ባቀደው ዕቅድ መሠረት በብፁዓን አባቶች የመሠት ድንጋይ ተቀምጧል።

✥••••✥••••✥••••●✞ ● ✞ ●✞ ●••••✥••••✥••••✥✞ ●••••✥••••✥••••✥
975 viewsBereket kebede, 10:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 12:04:08
908 viewsBereket kebede, 09:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 19:14:33
2.9K viewsBereket kebede, 16:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 09:09:35 #የ2014 ዓ.ም ጾመ ፍልሰታ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት መልዕክት ከዋሽንግተን ዲሲ ሰሜን አሜሪካ።

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
በሀገር ውስጥም ሆነ በመላው ዓለም ዙርያ የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናንና ምእመናት፣ እንዲሁም ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት በሙሉ #እንኳን_ለጾመ_ፍልሰታ_ለማርያም_በ ሰላም_አደረሳችሁ !!!
“ወተዘከረ ሣህሎ ዘይቤሎሙ ለአበዊነ ለአብርሃም ወለዘርዑ እስከ ለዓለም፤ ለአባቶቻችን ለአብርሃምና ለዘሩ የነገራቸውን ይቅርታውን ለዘላለሙ አሰበ” (ሉቃ.፩፥፶፭ )
ማኅደረ መለኮት፣ ማኅደረ መንፈስ ቅዱስ የሆነች እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፣ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልታ እግዚአብሔርን ባመሰገነችበት ምስጋናዋ፣ ከላይ የተጠቀሰውን ይህንን ዐረፍተ ነገር መናገሯን በቅዱስ ወንጌል ተጽፎልናል፡፡

ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ምስጋናዋ የገለፀችው ዓቢይ መልእክት የክብር አምላክ እግዚአብሔር የተናገረውን የማያስቀር አምላክ መሆኑን ነው፤ ኤልሻዳይ እግዚአብሔር የተስፋ አምላክ ነውና በየጊዜው ለፍጡራኑ የተስፋ ቃል ይሰጣል፣ ቃል ኪዳንም ይገባል፣ እግዚአብሔር በክዋኔው ዘላለማዊ እንደሆነ ሁሉ ቃል ኪዳኑም ዘላለማዊ እንደሆነ “ወተዘከረ ኪዳኖ ዘለዓለም፣ ማለትም ዘላለማዊ ቃል ኪዳኑን አሰበ” በማለት ቅዱስ መጽሐፍ ያስተምረናል፡፡ እግዚአብሔር መፍቀሬ ሰብእ ከሆነ አምላካዊ ጠባዩ በመነጨ ፍቅሩ ከመጀመሪያው ሰው ከአዳም ጀምሮ ለአበው ቃል ኪዳን እንደገባላቸው ተጽፎልናል፣ ይልቁኑም ለአብርሃም “በዘርእከ ይትባረኩ ኲሎሙ አሕዛበ ምድር ማለትም የምድር አሕዛብ ሁላቸው በዘርህ ይባረካሉ” ብሎ ለዓለም ሁሉ የሚሆን በረከትና ድኅነት ከእርሱ እንደሚገኝ ቃል ኪዳን ገብቶለታል፤ ቅድስት ድንግል ማርያም “ለአብርሃምና ለዘሩ የተናገረውን ቃል አሰበ” ብላ የገለፀችውም ይህንን ቃል ኪዳን ነው፤ ምክንያቱም የምድር አሕዛብ ሁሉ የሚባረኩበት ዘር ኢየሱስ ክርስቶስ በወቅቱ በማኅፀኗ እንዳለ ታውቃለችና ነው፡፡

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት
ከቅድስት ድንግል ማርያም ምስጋና የምንማረው ዓቢይ ትምህርት ሁሌም የእግዚአብሔርን ድንቅ ፍቅር በማስታወስ፣ በመናገርና በመመስከር ማመስገን፣ ማሰብና ማስታወስ እንደሚገባን ነው፡፡ እግዚአብሔርም ይህንን እንደሚወድ “ወተዘከሩ መንክሮ ዘገብረ፤ ያደረገውን ድንቅ ሥራ አስቡ” ብሎ ነግሮናል፡፡

እግዚአብሔር የተናገረውን የማያስቀር ታማኝ አምላክ ነውና ለአብርሃምና ለዘሩ የገባውን ቃል ኪዳን እነሆ ከዛሬ ሁለት ሺሕ ዐሥራ አምስት ዓመታት በፊት ቃል ኪዳኑን እንደተስፋ ቃሉ በተግባር ፈጽሞአል፤የምድር አሕዛብ ሁሉ የሚባረኩበት ወይም የሚድኑበት ዘር እርሱም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የአብርሃም ዘር ከሆነች ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ የምድር አሕዛብ የሆነውን በሙሉ በደመ መስቀሉ ባርኮ አንጽቶና ቀድሶ አድኖአል፡፡ እግዚአብሔር የምድር አሕዛብ ሁሉ በምሕረትና በይቅርታ እንድንባረክበት የሰጠን ዘር አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ ሁላችንም መገንዘብና ማመን ይገባናል፣ ይህንን ማወቅ፣ ማስተዋልና ማመን ብፅዕና ማግኘትን ያስከትላል፡፡ ቅድስት ድንግል ማርያም “ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ነሽ ይሉኛል” ስትል የተናገረችው ቃለ ትንቢት የእግዚአብሔር ማደሪያ ቤተ መቅደስ መሆኗን ስለተረዳች ነው፡፡
እኛም እንደእሷ “አንትሙ ውእቱ ታቦቱ ለመንፈስ ቅዱስ ማለትም እናንተ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ናችሁ” ተብለናል፤ ቅድስት ድንግል ማርያም ማኅደረ መለኮት የሆነችው በሃይማኖት በትሕትና ነው፤ ከዚህ አንጻር እኛም በሃይማኖት ጥላ ሥር ሆነን በትሕትና በፍቅር በአንድነት የምንኖር ከሆነ የእግዚአብሔር ማደሪያ ለመሆናችን ሌላ ምስክር አያስፈልገንም፡፡ ምክንያቱም ጌታችን “ተፋቀሩ በበይናቲክሙ ወእምከመ ተፋቀርክሙ በበይናቲክሙ የአምረክሙ ዓለም በዝንቱ ከመ አርዳእየ አንትሙ፤ እርስ በርሳችሁ አብዝታችሁ ተፋቀሩ፤ እርስ በርሳችሁ ከተዋደዳችሁ ደቀመዛሙርቴ እንደሆናችሁ ዓለም በዚህ ያውቃል” ብሎ እንዳስተማረን ምስክሮቻችን ፍቅር አንድነትና ትሕትና ይሆናሉና ነው፡፡

የተወደዳችሁ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት ከነገው ዕለት ጀምሮ የምንጾመው የጾመ ማርያም ዋና ዓላማ ጠብንና ጥላቻን ማሸነፍ የሚያስችል የይቅርታን የፍቅርንና የአንድነትን ኃይል በመለኮት ፈቃድ ለማጐልበት ነው፤ የተለየ የጾም፣ የጸሎት፣ የንሥሐ ጊዜ ወስኖ እግዚአብሔርን መለመንና ከእርሱ ጋር መገናኘት ከጥንት ጀምሮ የሃይማኖት መርሕ ነው፡፡ በዚህ መርሕ ተመርተው ሕዝባቸውንና ሀገራቸውን ከመከራና ከፈተና የታደጉ ቅዱሳን ብዙ ናቸው፡፡ የልቡናቸውን መልካም ምኞት ያገኙም እንደዚሁ ብዙ ናቸው፡፡

እኛም ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን በደነገገችው የቀኖና ድንጋጌ መሠረት የምንጾመው ጾመ ማርያም፣ ቅዱሳን ሐዋርያት ጌታችን የልቡናቸውን መሻት እንዲፈጽምላቸው የጾሙትና የለመኑትን ያገኙበት ኩነት መነሻ አድርገን እግዚአብሔር እንደነሱ የልቡናችንን መሻት እንዲፈጽምልን በማመንና ተስፋ በማድረግ ነው፤ ከዚህ አንጻር የቅድስት ድንግል ማርያም ነገረ ትንሣኤ ወፍልሰት በማሰብ ከእግዚአብሔር ጋር ለመገናኘት በብርቱ እንጥራለን፣ እንጾማለን፣ እንጸልያለን፣ በንሥሐም ወደ እርሱ እንቀርባለን፣ ቅዱስ ምሥጢረ ቊርባንንም እንቀበላለን፤ በዚህም ከእግዚአብሔር ጋር እንገናኛለን፡፡ ይህ ሲሆን እግዚአብሔር የልባችንን መሻት በብሩህ ገጽ ተቀብሎ ይፈጽምልናል፡፡ ሁላችንም እንደምንገነዘበው በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ ሕዝብ ፍላጎት ፍጹም ሰላም ያላት ሀገር እንድትኖረው ነው፤ ይህ ትክክለኛ ፍላጎት ነው፡፡ ይሁንና ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ ሁሉም ነገር ስለማይሆን ፍጹም ሰላም በሀገር ሰፍኖ ሕዝባችን እግዚአብሔር በሰጠው ምድር በፍቅር፣ በአንድነት በነጻነትና በእኩልነት እንዲኖር ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት ሁሉ በዚህ ወቅት የቅድስት ድንግል ማርያምን ጸሎትና ስእለት ተማኅፅኖና አስተበቊዖት አጋዥ አድርገን በልዩ ሱባዔ ወደ እግዚአብሔር በመቅረብ በንሥሐ፣ በጾም፣ በጸሎት፣ ነዳያንን በመርዳትና ቅዱስ ቊርባንን በመቀበል እሱን መማፀን ይኖርብናል፡፡

በመጨረሻም በሀገራችን የተከሠቱት ያላስፈላጊ ግጭቶችን በድርድር ለመፍታት እየተሞከሩ ያሉ አንዳንድ የሰላምና የውይይት ድምፆች ተስፋ ሰጪ ስለሆኑ ሥር ሰደው፣ በተግባር ተተርጉመው፣ ለተጐዳው ሕዝባችን መጠገኛ ይሆኑ ዘንድ፣ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት ሁሉ በዚህ ዙርያ በሱባዔው ወቅት ወደ እግዚአብሔር አቤት በማለትና ሂደቱን በመደገፍ የበኩላቸውን ጥረት እንዲያደርጉ፣ መንግሥትም ሆነ የዓለም አቀፉ ማኅበረ ሰብ በዚህ በጎ ሐሳብ እንዲገፉበትና ሕዝባችንንና ሀገራችንን ከጥፋት እንዲታደጉ አባታዊ መልእክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፡፡

እግዚአብሔር አምላክ ጾሙን የሰላም የሥርየት የፍቅር የአንድነት ጾም ያድርግልን፡፡
ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን
አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ዋሽንግተን ዲሲ አሜሪካ ፡፡
4.6K viewsBereket kebede, 06:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 09:06:56
2.4K viewsBereket kebede, 06:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 19:55:09
የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ተመራቂ ተማሪዎች እንኳን ለዚህ አበቃችሁ። በእውነት ትልቅ ተስፋ ሰጭ ተግባር ነው። የቸርነት አምላክ ያበርታልን።
YouTube
https://www.youtube.com/channel/UC83LE1vp0FBsV2TEfcpSmUg
Facebook
http://facebook.com/EOTC.GSSU
Telegram
https://t.me/EOTCNSSU
Website
https://eotc-gssu.org/a/
2.7K viewsBereket kebede, 16:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-30 11:44:48 https://www.facebook.com/112246503449787/posts/pfbid0WnaoxHPzBEZ2jn5VDzTM83J6gYM9S4prnbxwq7F3xdwQQ93i45vvnzSoM35VvCWbl/?sfnsn=mo
2.1K viewsBereket kebede, 08:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-29 14:50:53
✥••••✥••••✥••••●✞ ● ✞ ●✞ ●••••✥••••✥••••✥✞
✥••••✥••••✥••••●✞ ● ✞ ●✞ ●

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ከሀገረ ስብከቱ የሰንበት ት/ቤት ማደራጃ ክፍል ጋር በጋራ በመሆን በአዲስ አበባ ውስጥ ካሉ የደብራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች ፣ የሰበካ ጉባኤ ምክትል ሊቃነ መናብርት እንዲሁም የስብከተ ወንጌል ኃላፊዎች ጋር በቀጣዩ ዓመት የሰንበት ት/ቤቶች ሥርዓተ ትምህርት ትግበራ ዙሪያ ዛሬ ሐምሌ 22/2014 ዓ.ም የጋራ ምክክር አደረገ ።

የምክክር መድረኩ የሀገረ ስብከቱ ሰንበት ት/ቤት ማደራጃ ዋና ክፍል ኃላፊ መምህር ደምስ አየለ የተመራ ሲሆን :: ስለ ስርዓተ ትምህርቱ ገለጻ እና ውይይት በመምህር በላይነህ መኮንን እና ዲ/ን ስንታየሁ ምስጋናው ቀርቧል ::

በምክክር ጉባዔው ማጠናቀቂያ ላይም ከየአጥቢያው የመጡ ባለድርሻ አካላት በየአጥቢያችን ላይ ሥርዓተ ትምህርቱን ለማስተግበር ኃላፊነት እንወስዳለን በማለት አጋርነታቸውን ገልጸዋል ።

#የአዲስ_አበባ_ሰንበት_ትምህርት_ቤቶች_አንድነት
✥••••✥••••✥••••●✞ ● ✞ ●✞ ●••••✥••••✥••••✥✞
✥••••✥••••✥••••●✞ ● ✞ ●✞ ●
5.0K viewsBereket kebede, 11:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ