Get Mystery Box with random crypto!

ሄሪ በጭንቀት ጣቶቹን የወምበሩ መደገፊያ ላይ ይጠበጥባል፡፡ እግሩ ስር ያለው ምንጣፍ፣ የተቀመጠበት | 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜

ሄሪ በጭንቀት ጣቶቹን የወምበሩ መደገፊያ ላይ ይጠበጥባል፡፡ እግሩ
ስር ያለው ምንጣፍ፣ የተቀመጠበት ሶፋና የግድግዳው ቀለም ማማር
የድሎት ስሜት ስሜት ቢፈጥሩለትም አንድ ቦታ መቀመጡ ወጥመድ ውስጥ የገባ እንዲመስለው ማድረጉ አልቀረም፡ ጥቂት ጊዜ ቆይቶ የመቀመጫ ቀበቶውን ፈታና ብድግ አለ፡፡ ከዚያም ኒኪ በሄደበት አቅጣጫ አቀናና አስተናጋጁ ምግብ የሚያዘጋጅበት ክፍል ውስጥ ዘው አለ፡፡ በቀኝ በኩል የወንዶች መፀዳጃ ክፍል የሚል የተጻፈበት ክፍል አየ፡፡ ከእሱ ቀጥሎ ወደ ላይ የሚያስወጣ ደረጃ አገኘ፡፡ ወደ አይሮፕላን ነጂዎቹ ክፍል ይወስዳል፡፡ ከፊት ለፊት ደግሞ የአየር መንገዱን ዩኒፎርም የለበሱ የአይሮፕላኑ ሰራተኞች
የተገጠገጡበት ክፍል ይገኛል፡፡ ሄሪ እነሱን ሲያይ ምን ይሰሩ ይሆን?› ሲል
አሰበ፡፡ ጉዞው ሰላሳ ሰዓት የሚወስድ መሆኑ ትዝ ሲለው ሰራተኞቹ እየተለዋወጡ ማረፍ እንዳለባቸው ገባው፡፡ ከዚያም አይሮፕላኑ የኋላ ክፍልጋ ሲሄድ ሶስት ክፍሎች ውስጥ ተሳፋሪዎች ተቀምጠው ስላገኘ ባለጸጋና በራሱ
የሚተማመን አሜሪካዊ እንደሚያደርገው ኮራ ብሎ በግምባር ጥቅሻ ሰላምታ
እየሰጠ አለፈ።

አራተኛው ክፍል ትይዩ የተቀመጡ ሁለት ሶፋዎች የያዘ ሲሆን ከጎኑም
የሴቶች መዋቢያ ክፍል ወይም መጸዳጃ ቤት አለ፡፡ ከዚያም ቀጥሎ በብዙ
ሰዎች አፍ የተወራለት የሙሽሮች ክፍል ይገኛል፡፡ ሄሪ በሩን ለመክፈት
ሞከር አደረገ ነገር ግን ተዘግቷል፡፡ ተመልሶ ሲሄድም ተሳፋሪዎቹን
በፈገግታ መልከት ከማድረግ አልተቆጠበም፧ በአሜሪካውያን ስታይል።

አንድ ዝንጥ ያለ የፈረንሳይ ልብስ የለበሱ ሰው አየና ባሮን ጋቦን ሳይሆኑ አይቀርም› ሲል አሰበ፡ አንድ ያለ ካልሲ ጫማ ያደረጉ ጭንቅ ያላቸው ሰው አጠገቡ ተቀምጠዋል፡ ሁኔታቸው ሁሉ ለየት ያለ ነው ምናልባትም ፕሮፌሰር ሃርትማን ሳይሆኑ አይቀርም፡፡ የለበሱት ሱፍ ልብስ ጭምድድ ያለ ከመሆኑም በላይ ምግብ ካገኙ የሰነበቱ ይመስላል።

ሄሪ ሉሉ ቤልን ገና እንዳያት አወቃት፡፡ ነገር ግን በፊልም
እንደሚያያት ሳትሆን ጎልማሳ መሆኗን ሲያይ ቀልቡ ግፍፍ አለ፡፡
የምትሰራባቸው ፊልሞች ላይ የአስራ ዘጠኝ ዓመት ኮረዳ ነው የምትመስለው፡፡ ከዳይመንድ የተሰሩ ውድ የጆሮ ጌጦች፣ የአንገት ጌጥና የእጅ አምባሮች አጥልቃለች፡

አይሮፕላኑ ውስጥ ከመግባቱ በፊት የቆየበት ሆቴል ውስጥ የነበረችውን ጸጉረ ነጭ ውብ ሴትም ሲያይ አወቃት: አሁን የሰሌን
ባርኔጣዋን አውልቃለች፡፡ ዓይኖቿ ሰማያዊ ሲሆኑ ቆዳዋ ምንም ምልክት
የሌለበት ንፁህ ነው፡፡ አጠገቧ የተቀመጠው ጓደኛዋ የሆነ ነገር እየነገራት
ትስቃለች፡፡ ከሰውየው ጋር ፍቅር የያዛት መሆኑ በግልጽ ይታወቃል፡ ሄሪ ሴቶች ኮሚክ ወንድ ይወዳሉ ሲል ገመተ፡፡

በዳይመንድ የተለበጠ የሉል ጌጥ የያዘችው አሮጊት ልዕልት ላቪኒያ
ሳትሆን አትቀርም፡፡ ያለችበትን ቦታ በጥላቻ ታማትራለች፡፡ ቀጥሎ ባለው
ክፍል ውስጥ አምስት ሰዎች ተቀምጠዋል፡፡ ሰዎቹ ካርታ እየተጫወቱ ሲሆን እንደዚህ ባለ ረጅም ጉዞ ወቅት ጎበዝ ቁማርተኛ ብዙ ገንዘብ ሊበላ እንደሚችል ተገነዘበ፡፡

ወደ መቀመጫው ተመለሰና አስተናጋጁ ውስኪውን ሲያመጣለት
‹‹አይሮፕላኑ አልሞላም›› አለው አስተናጋጁን፡፡

ኒክም ‹‹ሞልቷል›› አለው፡፡

ሄሪ ዙሪያ ገባውን ተመለከተና ‹‹እዚህ ክፍል ውስጥ አራቱ ወንበሮች
ክፍት ናቸው፣ ሌሎቹ ክፍሎች ውስጥም እንዲሁ ነው፡፡››

‹‹አልተሳሳትክም፧ ይህ ክፍል ቀን ቀን አስር ሰው፣ በመኝታ ጊዜ ግን ስድስት ሰው ብቻ ነው የሚይዘው፡፡ ከራት በኋላ መኝታ ስናመቻች ታያለህ፡ እስከዚያው ዘና ብለህ ቁጭ በል›› አለው፡.....

ይቀጥላል