Get Mystery Box with random crypto!

ከኃጢያት ጋር አትጫወት/አትጫወቺ!! | ፍኖተ ~ ጽድቅ

ከኃጢያት ጋር አትጫወት/አትጫወቺ!! <<>>

አሁን አሁን ከኃጢአት ጋር በጥቂቱ ከመጫወት አልፎ ኃጢአትን እንደውሃ የሚጠጣበት ደረጃ ላይ ተደርሷል ብንል ማጋነን አይመስለኝም። ብዙ ሰው ኃጢአትን መፍራት አቁሟል። ከዚህም የተነሣ በስውር የሚደረጉ የኃጢአት ልምምዶች በምዕመኑ ዘንድ ብቻ ሳይሆን በአገልጋዩም ዘንድ እንደ አሽን ፈልተዋል።

በነገራችን ላይ እግዚአብሔርን የሚፈራና መንፈሳዊ የሆነ ሰው የአደባባይ ህይወቱና የጓዳ ህይወቱ አይለያይም። ፈሪሃ እግዚአብሔር በልቡ ላይ ስላለ በዙሪያው የሚያዩት ሰዎች ኖሩም አልኖሩም እሱ የሚያውቀው አይኖቹ እንደ እሣት ነበልባል የሆኑለት ጌታ ሁልግዜ እንደሚያይ ነው። ከኃጢያት ጋር ምን አለበትና ምን ችግር አለው በሚል የሰነፎች ብሂል ተጠምደን አንድና ሁለት እያልን ጨዋታዎች ከጀመርን አደጋ ላይ መሆናችንን መረዳት አለብን።

የኃጢያት ደሞዝ ሞት ነውና። የኃጢያት ልምምድ እንደ ዘር ሲሆን እንደቀልድ የገባንበትና የጀመርነው ጉዳይ መዘዙ ምናልባት ከአመት በኃላ ይሆናል የሚገለጠው። ዛሬ ዛሬ ማንም አያቅውም ብለን እንደ ጨዋታ የምንለማመደው ኃጢያት ነገ ላይ ኃፍረትንና ውርደትን በአደባባይ ሊያከናንበን ይችላል።

ወዳጆቼ ሆይ ስውር የኃጢያት ልምምዶች በጨለማው አለም ተፅዕኖ ሥር የመሆናችን ምልክት ስለሆነ በኢየሱስ ክርስቶስ ደም ታጥበን ከዚህ ክፉ ባርነት በፍጥነት ልንፈታ ይገባናል። ከሁሉ የባሰው ደግሞ በኃጢያት ልምምድ ውስጥ ያለ የትኛውም ሰው በጥልቁ አለም ላይ የሚሠሩትን ርኩሳን መናፍስቶች ወደ ህይወቱ በቀላሉ መጋበዙ ነው። ምክንያቱም እነዚህ ክፉና ጨካኝ መናፍስቶች ንብረታቸው ባለበት ቦታ ሁሉ የመገኘት ህጋዊ መብት አላቸው።

ንፅህና በጎደለው ቤት ውስጥ ዝንቦች፣ ትኋኖች፣ አይጦች፣ ቅማሎች፣ በረሮዎች፣ ሽረሪቶች ወዘተ እንደሚንፈላሰሱበት እንዲሁ በኃጢያት ወደ ተበከለና ወደ ቆሽሽ የሰው ህይወትም ርኩሳን መናፍስቶችና አጋንንቶች ሳይጠሩ(ተስበው ብቻ) ይመጣሉ። እንደዚህ አይነት ሰዎች በጨለማው አለም ቁጥጥር ሥር ስለወደቁ ከፍተኛ አደጋ ተጋርጦባቸዋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ደግሞ በስውር ኃጢያትን የሚለማመድ ሰው ክፉ መናፍስቶችን የሚቃወምበት ኃይል የለውም። በምሳሌ ለማስረዳት ያህል:-'ሣንባን በእጅ ይዞ ድመትን ለማባረር እንደመሞከር ብላችሁ አስቡት' ሰይጣን ወደሰዎች ህይወት ውስጥ ገብቶ ለመበጥበጥ እና ለማጥፋት ሲፈልግ ቅድሚያ የኃጢያት ግብዣውን በማቅረብ ሲሆን ግብዣውን የተቀበሉለት ሰዎች ደግሞ የፈለገውን እንዲያደርግ ህጋዊ መብትን/ፈቃድን የሰጡት ሰዎች ናቸው።
/ካነበብኩት/

ይቀላቀሉ ➟ @fenote_tsedek
በቅንነት ያጋሩ ➟ @fenote_tsedek