ክፍል (45) #ነገረ ድኅነት #በነገረ ድኅነት የምስጢረ ተዋህዶ #ምሳሌዎች ሀ /የእሳትና #ብረት ውህደት (የጋለ ብረት) #ብረትና እሳት #ሲዋሐዱ ብረቱ ከእሳት በገባ ጊዜ #እሳቱ #የብረቱን ገነዘብ (ባሕርይ ) ገንዘብ ያደርጋል #ብረቱም የእሳቱን ገንዘብ ያደርጋል ልክ መለኮት የሥጋን ሥጋም የመለኮትን#ገንዘብ ገንዘብ እንዳደረጉት ማለት ነው። የቃል (መለኮት ) ገንዘብ #የሥጋ ሆነ ። #የሥጋ ገንዘብም ከኃጢአት በስተቀር የቃል ሆነ " ሃይ አበው ዘቄርሎስ #እሳት ረቂቅና ብሩህ ነው ነገር ግን #የብረትን ገንዘብ ገንዘብ በማድረግ በተዋሐዱ ጊዜ ግዙፍ(የሚያዝ የሚጨበጥ የሚዳሰስ ) ነው። #እንደዚሁም #ሥጋ በባሕርይው ግዙፍና ውሱን ነው #መለኮትን በተዋሐደ ጊዜ ግን #በመለኮት ገንዘብ ረቂቅ ምሉዕ ክቡር ባለጸጋ ነው ። #መለኮትም በሥጋ ገንዘብ (ሥጋን በተዋሐደ ጊዜ ) ግዙፍና ውሱን ነው። #ዳግመኛም የእሳትና የብረት ተዋህዶ የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ #የሕማሙ (የተቀበለው መከራ) አምሳል ነው። #እንደ እሳቱ የማይዳሰሰው የማይያዘውና የማይጨበጠው #ረቂቁ መለኮት እንደብረቱ የሚዳሰሰውን የሚያዘውና የሚጨበጠውን ሥጋን በመዋሐዱ ነው ። #እንግዲህ አምላክ ተያዘ ታሰረ ተገረፈ ተሰቀለ ሞተ ተቀበረ ተነሳ አረገ #የምንለው በሥጋ ሞተ #በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ ( 1ኛ ጴጥ 3 ÷ 18 ) ስብሐት ለሥላሴ ይቀጥላል ቀሲስ ጥሩውኃ ክፍሌ። 78 viewszemari tiruwuha, 03:30