Get Mystery Box with random crypto!

አውደ Tibeb

የቴሌግራም ቻናል አርማ felege_tibeb — አውደ Tibeb
የቴሌግራም ቻናል አርማ felege_tibeb — አውደ Tibeb
የሰርጥ አድራሻ: @felege_tibeb
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 810
የሰርጥ መግለጫ

❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️♥♥♥♥♥♥♥♥♥
ከጥበብ ምንጭ
አብረን እንጎንጭ!!!
መንፈሳዊ፣ሀገራዊና፣ፍቅር ነክ ግጥሞች፤
ትረካ፣መነባንብ እና ለድራማ የሚሆኑ ጽሁፍች ከዚ ቻናል ያገኛሉ!!!
በሚመቾት መንገድ
የሚፈልጉትን ጽሁፍ እንጽፋለን ለትዕዛዞትና
ለአስተያትዎ @zemeden_bot
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️♥♥♥♥♥♥♥♥♥

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-07 21:12:02
https://t.me/felege_tibeb
1.5K viewsedited  18:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 21:12:59
እኛም እንድንድን ከኃጢአት በሽታ፤
መድኃኒት እንውሰድ እንጹም ፍልሰታ።
@Ortodox_Art
196 viewsedited  18:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 07:19:25
211 views04:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-27 21:34:46 #ፍቅርን_ያጣ_ፍቅር
#ክፍል_አልቦ
ያኔ በልጅነት ዕድሜያችን ሳይጠና፣
ከየኔታ እግር ሥር ፊደል ሥናጠና፣
ያለ ገደብ ስንጮህ ዕፍረታችን ሳይጸና፣
ነገን ስንስላት በሸራ አዕምሯችን ዳመና፣
"በዝናብ በረከት በበረዶ ቆሌ፣
በጣይ ብሩኅነት በከዋክብት ስንሳሌ፣
ጽልመትን በምትገፍ በጨረቃ ምሳሌ፣
ሣርን ባየንበት ባረንጓዴ ዝንባሌ፣
ስንጮህ ባስተጋባች በገደል ማሚቱ፣
በባሕር በጎርፉ በየ ሁነታቱ፣"
በጠቀስንበት ዓይን በተጥበረበረ፣
በጨቅላ መነጽር ትታየን ነበረ።
ስንስላት በምናብ፣
ስንሰማት በዜማ፣
ርስበርስ ተጣልተን፣
ወዲያው ስንስማማ፣
አ'ርቀን ስንኖር ርቀት ስንጓዝ፣
ወደ አዕምሯችን ጥበብን ስናግዝ፣
ከቃላቱ የከበረ፣
ከገበታው የነጠረ፣
ከቃል የቀጠለ፣
አንድ ቃል ነበረ
ቀጣይ ክፍል
ይቀላቀሉ
https://t.me/felege_tibeb
ከደበረህ ተወው
402 views18:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 21:37:11
https://t.me/felege_tibeb
558 viewsedited  18:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 18:24:44
#ደማችን_ተቀድቶ_ስንት_ሊትር_ይሙላ?
ቀይ መጠጥ የጠማው፣ችግኝህ እንዲፈላ፤
የተከልከው ጸድቆ፣ምድርን እንዲመላ፤
የስንት ሰው ደም ይፍሰስ? ስንቱ አንገቱ ይቀላ?
ግብህ እንዲሳካ........
ደማችን ተቀድቶ ስንት ሊትር ይሙላ?
ባቀላኃት ምድር.......
አረንጓዴ አሻራህ፣እንዲያስተጋባ፤
ስንት ሊትር እናልቅስ ምን ያህል ዕናንባ?
https://t.me/felege_tibeb
991 viewsedited  15:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 09:38:12
428 views06:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-02 11:22:17 Channel photo updated
08:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-02 11:15:27 #ዕርገቱን_ሳስብ
....ሀዘንና፣ደስታ ፍርኃትና፣ብርታት መለየትና፣ ሙላት ለምን ይደባለቁብኛል?....
ከደቀመዛሙርቱ  ጋ በመንፈስ ወደ ቢታንያ ይዞኝ እንዲወጣ እመኛለሁ፤ ሲባርከኝም ዝቅ ብዬ ቡራኬውን መቀበል እሻለሁ፤
ግን ደግሞ
እየባረከኝ ከቆምኩበት ስፍራ ከፍ ከፍ ሲል ጥሎኝ እንደሄደና እንደተለየኝ የሚያሳስብ ጭላንጭል ዕሳቤ ይመጣብኝና ጥቂት እተክዛለሁ ዕንባዬን መቆጣጠር ይሳነኛል፤
ኢየሱስ ክርስቶስ ተለይቶኝ ከፍ ከፍ እንዳለ እስከ ዓለም ፍጻሜ ካንተጋር ነኝ ያለኝ ዛሬ ግን እንደተወኝ በልቡናዬ ይመላለሳል እንደ ደቀመዛሙርቱ ፍርኃት፣ብቸኝነት፣የሁኔታዎች ጣዕም አልባነት በውስጠቴ ይራወጣል  "ኢይደንግጽክሙ ልብክሙ(
ልባችሁ አይታወክ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፥ በእኔም ደግሞ እመኑ።)
ዮሐንስ 14፥1
"ያለውን ሳሰላስል የወረረኝ ፍርኃት ወደ ኃያል ፍቅር፣ ድንጋጤዬ ወደ መደነቅ፣ ብቸኝነቴ ከሰማያውያን ጋር ወዳጅ ወደ መሆን ይለወጣል።
ቢሆንም ጌታዬ ሲለየኝ እያየሁት ከፍ ከፍ ሲል
ልቦናዬ በመለየት ጦር ይወጋል ኢየሱስን ደመና ሲቀበለው፤
የኔ ፊት ላይ የዕንባ ደመና ያንዣብባል፤
ጥቂት ቆየት ብሎም
“ወላጆች እንደ ሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም፤ ወደ እናንተ እመጣለሁ።”ዮሐንስ 14፥18 የሚለው ልቦናን የሚያረጋጋ ኃይለ ቃል ወደ ቀልቤ ይመለሳል በትካዜና በመለየት ሰበብ ያንዣበበው የዕንባዬ ደመና የ አምላኬን ፍቅር እና ርኅራኅኄን
በማሰብ በትኩሱ ዱብ ዱብ ይላል። ፍቅር፣ደስታ፣ሀሴት፣ዕልልታ በነገሰበት ዕለት የኔ ሀዘን፣ፍርኃትና፣
የጥሞና ልቅሶን ሳስብ በራሴ እሳቀቃለሁ እንዴት ነው እንደሌላው ደስ የማይለኝ ብዬ ውሳጤ ህሊናዬን ሳጤነው
እጅግ ከልብ የመነጨ ደስታ እየተደሰትኩ እንደሆነ ይነግረኛል
ጌታዬ ሞትን አሸንፎ፣ ጠላቴን አንበርክኮ፣ የተዋረደውን የኔን ሥጋ ይዞ፣ አዳምና ትውልዱን ሁሉ በመስቀሉ በከፈለው ዋጋ
አድኖ በክብር ወደ ሰማይ እንዳረገ እየተመለከትኩኝ ደስታም በውስጤ እንደመላ ይመልስልኛል እና ታዲያ ዕርገቱን ሳስብ ሀዘንና፣ደስታ ፍርኃትና፣ብርታት መለየትና፣ ሙላት ለምን ይደባለቁብኛል?
“እነሆም፥ አባቴ የሰጠውን ተስፋ እኔ እልክላችኋለሁ፤ እናንተ ግን ከላይ ኃይል እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ።” ሉቃስ 24፥49
የሚለውን ምክሩንና ትዕዛዙን ሳስብ ወደራሴ ተመልሼ በተስፋ
እሞላለሁ እንጂ
አንዳንዴ እኮ ጌታዬ በቢታንያ ወደ ሰማይ ከፍ ከፍ ሲል ሳይ
ከእንግዲ ምን ቀረኝ
ብዬ በሀዘን ተኮራምቼ ወደ ነበርኩበት ዓለም መመለስም እኮ ያምረኛል።
በቃ ከፍ ከፍ ሲል አጠገቤ እንደሌለ አስባለሁ ምሉዕ ነውና በምልአቱ እንዲጎበኘኝም አምናለሁ ደመና እንደተቀበለችው
እኔም ወደ ልቦናዬ ሳተኩር መድኃኔዓለምን በልቤ ውስጥ ተቀምጦ አገኘዋለሁ።
ሀዘኔ ወደ ሀሴት መከፋቴ ወደ መጽናናትና ፍጹም መረጋጋት ሲመለስ ይታወቀኛል።
ዳግም በድዬ ጌታዬን ከልቤ እንዳላጣው ለራሴ ቃል እገባለሁ
ጥቂት ቆይቼ ግን ያው ወደ ከረፋ በደሌ እመለሳለሁ፤
ከበደሌ እንዲያጥበኝ ስለማምን ከኢየሩሳሌም ሳልወጣ
ከፍ ከፍ ካለበት ተራራ ወጥቼ ዳግም ወደ ልቦናዬ እንዲመለስ
ዮሐንስ 16
"⁵ አሁን ግን ወደ ላከኝ እሄዳለሁ ከእናንተም፦ ወዴት ትሄዳለህ? ብሎ የሚጠይቀኝ የለም።
⁶ ነገር ግን ይህን ስለ ተናገርኋችሁ ኀዘን በልባችሁ ሞልቶአል።
⁷ እኔ ግን እውነት እነግራችኋለሁ፤ እኔ እንድሄድ ይሻላችኋል። እኔ ባልሄድ አጽናኙ ወደ እናንተ አይመጣምና፤ እኔ ብሄድ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ።"
ባለው መሠረት አጽናኙን እንዲልክልኝ እማጸነዋለሁ።
ዐረገ በስብሐት ስል ድምጸ ልቦናዬን ከፍ አድርጌ እዘምራለሁ።
ግንቦት 25 2014 አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
ዐሳቤ ዐሳባችሁ ከሆነ ተጋሩት አጋሩት
እንኳን ለብርሃነ ዕርገቱ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን
Henok kibebew
https://t.me/felege_tibeb
2.4K viewsedited  08:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-04 23:03:15 https://t.me/Happy_Brand_Market
549 views20:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ