Get Mystery Box with random crypto!

My letter 💌

የቴሌግራም ቻናል አርማ fekerachen — My letter 💌 M
የቴሌግራም ቻናል አርማ fekerachen — My letter 💌
የሰርጥ አድራሻ: @fekerachen
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 299
የሰርጥ መግለጫ

Well come to ma favored channel🤩
😎😎
Enaten feta enadregalne becha 😍😜
Stay home ok gays😷😷
Adiss music💃👯
Tik tok video 😆
Voice love message🔊
Pics😘
School life 👫

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-06-08 07:54:24 ያለህን ተመልከት !

ደስታህን ለማግኘት ሩቅ መሄድ አይጠበቅብህም ያሉህን ነገሮች በቂ ናቸው ፤ ሁል ግዜ ግን ችግሮችን የምታይ ከሆነ እና ፈተናዬ የበዛ ነው እያልክ የምታስብ ፣ ባለህ የማትደሰት ፣ በሆነው ሁሉ ቅሬታ ያለህ ከሆነ እመነኝ ዛሬ የምታማርራቸውን ቀናቶች የሚያስመሰግኑ ሌሎች ከባድ ቀናቶች ይመጣሉ ስለዚህ ሁሌም ባለህ ተደሰት አመስግን ያኔ በእጥፍ ይጨመርልሀል !

#meriti
97 viewsMíMã , 04:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 07:54:24 ከፈጣሪ ተጣበቅ!

ያስጨነቀህ ጉዳይ የማይፈታ ሊመስል ይችላል፤ መፍትሄውን ግን አንተ አላየኸውም ማለት የለም ማለት አይደለም፤ ሁሉን ማየት ወደሚችለው ልብህን ስታዞር የተሰወረብህ ሁሉ መገለጥ ይጀምራል።

ወዳጄ ከሰዎች አጠብቅ አያስተማምኑም፤ ሁኔታዎችም ተለዋዋጭ ናቸው፤ የጭንቀትህ መድሀኒት ያለው ፈጣሪህ ጋር ነው፤ ተስፋህ እሱ ብቻ ነው! ከፈጣሪህ ስትጣበቅ ሁሉም ምርጥ ይሆናል!
#meriti
95 viewsMíMã , 04:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 07:54:24 ቦታህ ላይ ጠንክር!

ጦጣ ዛፍ ይወጣል አዞ ውሀ ውስጥ ይሄዳል ይሄ የነሱ ተፈጥሮ ነው አዞ ዛፍ ላይ በመውጣት ከጦጣ ጋር ከተወዳደረ ከንቱ ድካም ነው ስለዚህ እኛም እንደዛው ነን ሁላችንም የየራሳችን የሆነ የተሰጠን ጥበብ አለን አንድ ካልሆንን ብለን በማይሆን ውድድር ውስጥ ብንገባ ግን ከኛ የሚባክነውን ጥበብ አስቡት ጎበዝ ሯጭ ሆነህ ተፈጥረህ በግድ ዶክተር ካልሆንኩ ካልክ ምን ሊፈጠር እንደሚችል? ስለዚህ የሆነ ቦታ ላይ ጀግና ሆነህ ሌላ ቦታ ላይ ግን ልታሸንፍ ባለመቻልህ በራስህ እንዳታዝን ያንተ ያልሆነ ቦታ ያንተ አይደለም ስለዚህ መታገልህን ተውና በቦታህ አሸንፍ!

#meriti
86 viewsMíMã , 04:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 07:54:23 የራስ መንገድ!

እውነት ነው የንፋሱን አቅጣጫ መቀየር አትችልም፤ መርከቡ ግን የነፋሱን አቅጣጫ ሳይሆን ያንተን መንገድ እንዲይዝ ማድረግ ትችላለህ።

አየህ በህይወት ውስጥም የሚገጥሙህን ሁኔታዎች፣ ፈተናዎች የማይጥሙ የሰው ፀባዮችን መቆጣጠር አትችልም፤ ግን ያንተን ህይወት እንዲወስኑት አለመፍቀድ ያንተ ምርጫ ነው ምክንያቱም
የመርከብህ ካፒቴን አንተ ብቻ ነህ!
#meriti
68 viewsMíMã , 04:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 07:54:22 አሪፉን ምረጥ!

ህይወትህ የሚወሰነው በምርጫህ ነው፤ ከአመታት በፊት አብረሀቸው የዋልካቸው ሰዎች፣ ያነበብካቸው መፅሀፎች፣ ያየሀቸው ቪዲዮዎች፣ የሰማሀቸው ነገሮች ሁሉ ተጠራቅመው
ዛሬ የደረስክበትን ወስነዋል።

ከ 5 አመት በኋላ የምትደርስበትንም የሚወስኑት አሁን የምታደርጋቸው ነገሮች ናቸው፤ ካንተ የተሻሉ ሰዎች ጋር ለመዋል መምረጥ አለብህ፤ የሚጠቅምህን ቪዲዮ ማየት አለብህ፤ መፅሀፍ ማንበብ አለብህ።
ምርጫህ ህይወትህን ይቆጣጠረዋል፤ አሪፉን ምረጥ
#meriti
59 viewsMíMã , 04:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 07:54:22 አምላክ አለ!

የትኛውም የዚህ አለም ችግር በአምላክህ ፊት እንደ ቁጫጭ ነው፤
ለምን ብቻህን ትታገላለህ? ያንተ ስራ እኮ ፈጣሪህን አጥብቀህ መጠየቅ እና የጠየከውን ለማግኘት በሙሉ አቅም መጣር ነው እንጂ መጨነቅ አይደለም እኮ። ወዳጄ ካንተ በላይ የሚያስብልህ አምላክ አለ! ሁሉንም ለርሱ አደራ ስጥ!

#meriti
55 viewsMíMã , 04:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 07:54:22 መጠየቅ አትፍራ!

ህልመኛ መሆን አለብህ ያለበለዚያ ህልም ያለው አገልጋይ ነው የምትሆነው። ፈጣሪህ ውዱን ስጦታ በነፃ ሰጥቶሀል፤ ጤናህን ቤተሰቦችህን የምትወዳቸውን ሰዎች ሁሉ በነፃ ነው የሰጠህ፤ ሀብት ስኬት ደስታ ብትጠይቀው ለሱ ርካሽ ነው። ወዳጄ መጠየቅ መመኘት አትፍራ፤ ምንም የማይሳነው አምላክ ከጎንህ ነው!


#meriti
51 viewsMíMã , 04:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 07:54:21 በፈጣሪህ ተደገፍ!

ህይወትህን የሚቀይረው ከሰው ጠብቀህ በምታገኘው ነገር አይደለም፤ ፀጋው፣ ስጦታው፣ ቸርነቱ ከማያልቀው
ከፈጣሪህ ከምታገኘው በረከት ነው ህይወትህ የሚቀየረው።

ወዳጄ በጭራሽ ከሰው እንዳጠብቅ፤ ሰው ማለት ሸንበቆ ነው የሆነ ቀን መቀንጠሱ አይቀርም!
ከፈጣሪ ቀጥሎ ግን ራስህን እመነው!

#meriti
49 viewsMíMã , 04:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 07:54:05 ቆራጥ ሁን!

የትም አያደርስህም እንጂ የስሜትህ ባሪያ መሆን ቀላል ነው፤ ጊዜያዊ ደስታ የሚሰጡህን ነገሮች በጥበብ እለፋቸው፤
ለእውነተኛ ደስታህ ስትል አሁን የማይጠቅሙህን ሰዎች፣ ነገሮች፣ ሁኔታዎች፣ ቦታዎች ሁሉ ከህይወትህ አውጣቸው!

የተመረዘ እጅ ወይም እግር የሚቆረጠው ባለቤቱ ስለማያስፈልገው አይደለም ግን ሌሎቹን የሰውነት ክፍሎች ስለሚመርዝ ነው፤
ስኬትና ደስታ መስዋዕትነት ይጠይቃል! ወዳጄ የሚጠቅምህን አሳምረህ ታውቃለህ ቆራጥ ሁን!

#meriti
48 viewsMíMã , 04:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 07:54:05 " ጀግና ማለት ፍርሃት የማይሰማው አይደለም ፤ ፍርሃቱን ፊት ለፊት የሚጋፈጥ ነው። "

#meriti
43 viewsMíMã , 04:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ