2022-11-30 14:34:23
ተግዳሮቶች ጠንክረን ከሰራንባቸዉ እድሎች ናቸዉ"፡፡
ክብርት ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚንስትር
ዓለም አቀፍ የኢንርፕሪነርሺፕ ሳምንት ፕሮግራም ሚሊዮን ፈተናዎች፤ ሚሊዮን እድሎች በሚል መሪ ቃል በይፋ ተጀመረ፡፡
በፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ኢንስቲትዩት በተጀመረዉ እና በቴክኒክና ሙያ ተቋማት የተሰሩ የተለያዩ የፈጠራ ዉጤቶች ለጉብኝትና ልምድ ልዉዉጥ በቀረቡበት በዚህ መድረክ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችን ጨምሮ በርካታ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡
በመድረኩ መዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚንስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ተግዳሮቶችና ችግሮች ጠንክረን ከሰራንባቸዉ እድሎች ናቸዉ ሲሉ ገልጸዋል፡፡
የአለም አቀፍ የኢንተርፕረነርሺፕ ሳምንት በአንድ ሳምንት ተከብሮ የሚያልቅ አለመሆኑ ጠቁመዉ ይልቁንም አመቱ ሙሉ ለምንሰራቸዉ ስራዎች ሃሳብ የምንለዋወጥበት እና ባለድርሻ አካላትን የምናገኝበት መድረክ ነዉ ብለዋል፡፡
የኢንተርፕሪነር አስተሳሰብ ባህል አድርጎ ለመገንባት ሰፋፊ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን የገለጹት ሚንስትሯ እንደ ሀገር ለተጀመረዉ ለዉጥ እንዲሁም ለቴክኖሎጂ ሽግግር ትልቅ አስተዋጽዎ እንደሚኖረዉም አብራርተዋል፡፡
የቴክኒክና ሙያ ተቋማት በየጊዜ የሚያፈልቋቸዉ ሀሳቦች ሼልፍ ላይ የሚቀመጡ ሳይ ወደ ተግባር ተቀይረዉ ችግር የሚፈቱ፣ ስራ እና ሀብት የሚፈጥሩ ለማድረግ ከሚመለከታቸዉ ሚኒስትር መስሪያ ቤቶች በጋራ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ንጉሱ ጥላሁን በበኩላቸዉ በዚህ የኢንርፐሪነርሺፕ ሳምንት የቴክኖሎጂ ዉድድር፣ የጀማሪ ኢንርፕራይዞች ዉድድር፣ ኤግዚቢሽንና ልምድ ልዉዉጥ ፣ የቴክኒክና ሙያ እና ዩኒቨርስቲዎች የትምህርት አሰጣጥ እና ኢንተርፕረነረሺፕ እና የፐብሊክ አንተርፐሪነርሺ ላይ የሚመክር አወደ ጥናት እና ሌሎችም በርካታ ስራዎች ማስጀመሪያ ፕሮግራም ነዉ ብለዋል፡፡
በዕለቱ የተለያዩ የፈጠራ ስራ ዉጤቶች ተጎብኝተዋል፡፡
3.8K views11:34