Get Mystery Box with random crypto!

ሞዐ ተዋሕዶ

የቴሌግራም ቻናል አርማ moaatewahido — ሞዐ ተዋሕዶ
የቴሌግራም ቻናል አርማ moaatewahido — ሞዐ ተዋሕዶ
የሰርጥ አድራሻ: @moaatewahido
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 435
የሰርጥ መግለጫ

"አሐዱ እግዚአብሔር ወአሐቲ ሐይማኖት ወአሐቲ ጥምቀት " እግዚአብሔር አንድ ነው: ሐይማኖት አንዲት ናት :ጥምቀት አንዲት ናት ። ኤፌ 4:5
ተብሎ እንደተጻፈልን አንዲት ሐይማኖት አለች እሷም መሠረቷ ኢየሱስ ክርስቶስ የሆነችው ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ናት ።

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-04-23 21:26:22 ምድርስ የእግሩ ጫማ አልነበረችምን እንዴት መቃብር ሆነችው። ወይ ጊዜ ለካ ንጉሥ ሰሎሞን ለሁሉ ጊዜ አለው ያለው እውነት ነው።

መቃብርስ አሁን ስም ሆነባት እንጂ አሁን ምን ሆናት እንደ አልአዛር እንኳ ያራት ቀን እራት አልሆናት።

ማርያም መቅደላዊትም ለካ የዋህ ናት ፤ ሽቱ አዘጋጅታ ሬሳ ነው ብላ ልትቀባ የሄደች ።
ለእኅቷ ለማርታ እኔ ነኝ ትንሣኤ ሕይወት ሲል አልሰማችምን ። ወይም ተነስቼ ገሊላ እቀድማችኋለሁ ሲል አልሰማችምን ።

#ዘነብ_ኢትዮጵያዊ
285 views18:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-23 21:25:57 ዳዊት ፡ ይሁዳን ፡ አገሩን ፡ ምድረ ፡ በዳ ፡ ፡ ትሁን፡ እያለ ፡ ምን ፡ ያራግመዋል፤ እርሱ ፡ ካልበላሁት ፡ ብሎ ፡ ነውን ፣ እንደ ፡ ይሁዳ ፡ ያለ ፡ መልካም፡ ነጋዴ፡ የለም ፤ #የዘላለሙን_ምግብ ፡ በ30 ፡ ብር ፡ ሸጠልን።

#አለቃ_ዘነብ_ኢትዮጵያዊ
264 views18:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-22 20:47:01 " ስቅለት "

በክርስትና አስተምሮ ይህ ዕለት የአይሁድ ካህናት ያለ በደል ያለ ጥፋት ንጹሕ እና ጻድቅ የኾነውን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰቀሉበት ዕለት ነው።

ዕለቱ በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለም ዂሉ መድኀኒት ለአዳምና ለልጆቹ ሲል በመልዕልተ መስቀል በቀራንዮ አደባባይ ተሰቅሎ መዋሉን የሚታሰብበት ታላቅ ቀን ነው።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እና ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በስግደትና በጾም የሚታሰብ ሲሆን በወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረትም በተለያዩ ስነ-ስርዓቶች ታስቦ ይውላል፡፡

በተለይ ደግሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከንጋታው ጀምሮ እስከ ማምሻው በዕለቱ የተፈጸሙትን ክስተቶች በሰዓት ከፍላ በልዩ መንፈሳዊ ሥርዓትና በስግደት ታከብረዋለች ፦

ዓርብ ጠዋት

ዓርብ ጠዋት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በጲላጦስ ፊት በፍርድ አደባባይ መቆሙ ይታሰባል። የካህናት አለቆችና ሕዝቡ ሽማግሎች ሁሉ ሊገድሉት በኢየሱስ ላይ ተማከሩ፤ አስረውም ወሰዱት ፥ ለገዢው ለጰንጤናዊው ጲላጦስም አሳልፈው ሰጡት።

በ3 ሰዓት

ጲላጦስ በወቅቱ በነበረው ሕዝብ ግፊት መሠረት ወንጀለኛውን በርባንን ከእስር አስፈትቶ በምትኩ ኢየሱስን አሳልፎ የሰጠበት፤ አካሉ እስኪያልቅም 6,666 የገረፉት ከሊቶስጥራ - ቀራኒዮ እርጥብ መስቀል አሸክመው የወሰዱበት ነው።

በ6 ሰዓት

ኢየሱስ ክርስቶስን እጆቹን እና እግሮቹን ቸንክረው በቀራንዮ ጎልጎታ ተራራ በ2 ወንበዴዎች መካከል የተሰቀለበት ነው።

በ9 ሰዓት

በእምነቱ አስተምሮ ይህ ሰዓት ኢየሱስ ክርስቶስ ነፍሱን ከሥጋው በባሕርይ ሥልጣኑ የለየበት ወደ ሲዖል ወርዶም የታሠሩትን ሁሉ ያስፈታበት ነው።

11 ሰዓት

ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከታላቅ ክብር እና ሐዘን ጋር በአዲስ መቃብር የቀበሩበት ነው።
292 views17:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-21 20:33:01 ንጉሡ ለራሳቸው ዋጋ ማስተመን ፈለጉና ሊቃውንቱን ሰብስበው ዋጋዬን ገምቱልኝ ይላሉ። ተሰብሳቢው ሊቃውንትም በነገሩ ተቸግረው በጣም በጣም ትልቅ ያሉትን ቁጥር መጥራት ይጀምራሉ። የገንዘቡም ዓይነት የወርቅ ተደርጎ ይጠራ ቀጥሏል።

የቁጥሩ ስም እየጠፋ ሲሔድ ትልቅ የተባለውን ቁጥር የተናገሩትን ሊቅ እያነሡ እገሌ ያለውን እጥፍ ሲል አንዱ ሌላው ይቀበልና የእገሌን ኹለት ሦስት እጥፍ እያሉ እስኪደክማቸው ቀጠሉ።

ወደ መጨረሻ እኔ ልገምት እኔ ልገምት ከሚለው እሽቅድምድም ሳይገቡ የቆዩ አንድ ሊቅ እጅ አወጡ። እኔ ጃንሆይን ስገምትዎ ፳፱ ብር ነው ግምትዎ ይላሉ።

በዚህ ጊዜ ሁካታ ኾነ። አንዳንዱ እኒህ ሰው አለቀላቸው ይላሉ። ከፍ ብሎ አንገቱን ዝቅ ብሎ ባቱን ይቆረጥ የሚሉም ነበሩ። ወይ ድፍረት የሚልም አለ።

ንጉሡ ግን ጠየቁ። ይህ ሁሉ ሊቅ ቁጥር እስኪያጥረው ሲገምት ያውም በወርቅ አንተ ከቁጥርም ፳፱ መጥራትህ ሳያንስ በብር መዘንኸኝ። እንዴት ነው ነገሩ? አሉ።

ሊቁም መለሱ። ጃንሆይ ድፍረት አይደለም። ለማዋረድም አይደለም። ምን ንጉሥ ቢኾኑ ከጌታዬ ከጌታዎ ክርስቶስ አይበልጡ። እሱ እኮ የተሸጠው ለ፴ ብር ነው። ባይኾን በአንድ ይነሱ ብዬ ነው አሉ። ንጉሡም ሊቁን አመሰገኗቸው ሸለሟቸውም።

ይህ ሁሉ ጌታችን የከፈለልንን እንድናስብ ነው። እኛን ለማዳን ተሸጠልን።

እስኪ ዋጋችንን እንወቅ!

ዛሬ ምክረ አይሁድ ነውና ቤዛነቱን ለማስታወስ።
246 views17:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-18 11:28:35 እውነቱን ተቀበል !!
*****
የግንቦት ፩ ቀጠሮ !!
****
ጎጃም፣ ጎንደር፣ ወሎ፣ ሸዋ አራቱም ዞኖች የሚገናኙበት ብቸኛ ማዕከል Intersection ሲሆን ቦታው የዓለም አቀፍ የጥንተ ስልጣኔ መመዘኛ መስፈርቶች ተሟልተው የሚገኙበት መሆኑ በእጅጉ አነጋጋሪ ሆኗል… እንዴት እና በማን ተዳፍኖ ኖረ ?? እንጠይቅ የተዳፈነውን እንግለጥ !!

#ሼር #ሼር #አዛምቱ #አዛምቱ

1. ሃይማኖት … የኦሪት መስዋዕት ይሰዋበት የነበረ በዘመነ
ክርስትና የሐዲስ ኪዳን ማዕከል ሆኖ የቀጠለ።

2. ቋንቋ…አማርኛ ቋንቋ የተፈጠረበት ምድር መሆኑ።

3. ዜማ … የዘመነ ብሉይ የአምልኮ መፈፀሚያ ዜማ
የነበረበት ፣ በዘመነ ሐዲስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
የሰዓታት ዜማ የደረሱበት።

4. ፍልስፍና … ዮሐንስ ገብላዊ ቅኔ ደርሶ ያመለከተበት፤

5. ትምህርት … በጽሑፍ ቋንቋ የአብነት ትምህርት ይሰጥበት
የነበረ።

6. የመንግሥት አስተዳደር … እንደ ክብረ ነገስት ያለ
የሥርዓተ መንግሥት መምሪያ ቦታና መዋቅር የነበረበት።

7 . የሐይማኖት እና የፍልስፍና ፣ የኪነ ጥበብና የስነ ጥበብ
ድርሰቶች ያሉበት።

8 . የግዕዝ፣ የአረማይክ፣ የአማርኛ ጽሑፎች በብራና እና
ደድጋይ ላይ ታትመው የሚገኙበት።

9. የጥንት ዘመን የጦር መሳሪያዎች እና የግብርና
መሳሪያዎች፣ የእንስሳት እርባታና የሰብል ማምረቻ
ጥንታዊ መገልገያዎች የሚገኙበት።

10. ስነ-ህንጻ … ከክርስቶስ ልደት በፊት የጥንት የስነ ህንፃ
አሻራዎች፣ የአምልኮ መሰዊያ ቦታዎች፣ ሌዋውያን
በእስራኤል ይሰሯቸው የነበሩ የሰቀላ ቤት አምሳያዎች…

ወ.ዘ.ተ … መሆኑ የጥንት ፐርሺያ፣ ቻይና፣ ግብፅ እና ግሪክ የመሳሰሉት በስልጣኔ የተለኩበት በአገራችን የአክሱም ስልጣኔ የተገለጠበት ሁሉ ሳይጓደል ተሟልቶ የሚገኝበት ግን እስከ ዛሬ ታሪኩ ተዳፍኖ የኖረ ስፍራ ነው።

አምሃራ ሳይንት (ቤተ አምሃራ)
----------------
በዚህ አስገራሚ ስፍራ በደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት በአምሐራ ሳይንት ወረዳ የምትገኘው ጥንታዊቷ ርእሰ አድባራት ወገዳማት ተደባበ ማርያም የተመሰረተችው በዘመነ
ብሉይ በቃዳማዊ ምኒልክ ዘመነ መንግስት
በ982 ዓመተ ዓለም ነው፡፡

በመፅሐፈ ሱባኤ ዘአማኑኤል ካልዕ ገጽ 2 ላይ እንደተጻፈው "ሌዋዊያን ካህናት ከእስራኤል በአዛሪያስ መሪነት የጁን አልፈው ከዛሪዋ አምሐራ ሳይንት ደረሱ"

ሌዋውያኑ አምሐራ ሳይንት እንደደረሱ 12 የተፈጥሮ በር ያለው ዙሪያው ገደል የሆነ የተለየ የተመረጠ ተራራ አግኝተው ለእግዚብሔር ቤተ መቅደስ ከሰሩ በኋላ ግማሾቹ ደብር ደባብ እንበላት ሲሉ አዛርያስ እና የዳዊት የወንድም
ልጆች ሳቤቅ ደግሞ "ይህቺማ የኢየሩሳሌም የዳዊት መታሰቢያ ከተማ ትሆን ዘንድ ተድባበ ጽዮን እንበላት" ብለው እንደሰየሟት ድርሳናት ያትታሉ፡፡

በብሉይ ዘመን መስዋዕተ ኦሪት ከተሰዋባቸው
መካከል አክሱም ጽዮን፣ ተድባበ ጽዮን (የዛሬዋ ተድባበ
ማርያም)፣ መርጡ ለማርያም፣ ጣና ቂርቆስ ቀዳሚዎቹ ናቸው፡፡

ቀዳማዊ ምኒሊክ ከአባቱ ከንጉሡ ከሰሎሞን መንግስት ተቀብሎ ከኢየሩሳሌም ወደ ኢትዮጵያ ሲመጣ 4 መናብርት ጽዮን ይዞ እንደመጣ ታሪክ ይናገራል። እንደ ኦሪቱ ስርዓት መናብርቱን ሲያፀናም፣

1. የአክሱም ጽዮን (ንቡረ እድ)
2. የተድባበ ማርያም (ፓትርያርክ)
3. የመርጡለ ማርያም (ርዕሰ ርኡሳን)
4. የጣና ቂርቆስ (ሊቀ ካህናት) ተብለው ተሰየሙ።

ከቀዳማዊ ምኒልክ ጀምሮ እስከ ጃንሆይ ዘመነ መንግስት ከሦስት ሺህ ዓመታት በላይ ንጉስ ቀብተው የሚያነግሱ እነዚህ አራቱ መናብርተ ጽዮን ነበሩ።

የአክሱሙ ንቡረ እድ … ዘውድ ይጭናል
የተድባበ ማርያሙ ፓትርያርክ … ቅንአተ ሰይፍ አስታጥቆ
በትረ መንግሥቱን ያስጨብጠዋል
የመርጡ ለማርያሙ ርዕሰ ርኡሳን… ልብሰ ንግሥናውን
ያለብሳል
የጣና ቂርቆሱ ሊቀ ካህን… ቅብአ ንግሥናውን ይቀባል


የመናብርተ ጽዮኑ ስያሜም 3ስቱ በእመቤታችን ምሳሌ በጽዮን ስም አራተኛው የሊቀ ካህናቱ ታቦት ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡ ከእነዚህ ጋር ቀዳማዊ ምኒልክን ተከትለው ወደ ኢትዮጵያ የመጡ 12.000 መሣፍንትና መኳንንት ወይዛዝርት 1.500 በተግባረ ዕድ የሰለጠኑ የወርቅና የብር፣ የብረትና የመዳብ፣ እንዲሁም የነሐስ አንጥረኞች አዋቂዎች ጠቢባን ፀበርተ ዕፀውና ወቀርተ አዕባን ናቸው፡፡ እነዚህ ኢትዮጵያ ገብተው በየክፍለ ሀገሩ ሥራቸውን ሲጀምሩ አክሱም ጽዮን ትግራይ ላይ ስትቀር የዳዊት የወንድም ልጅ ሳቤቅ የሰሎሞን አጎት ከመጀመሪያው ፓትርያርክ አዛሪያስ ጋር ተከዜን ተሻግሮ
አምሐራ ሳይንት ደረሰ፡፡

የአሁኗ ተድባበ ማርያም ካለችበት አምባ
ላይ ሲደርስ ቤተ እግዚአብሔር መሥራት ጀመረ፡፡ ቦታዋንም
በሀገሩ ስም ገሊላ ብሎ ጠራት፡፡ ፓትርያርክ አዛሪያስ ደስ አለውና ስሙን በቡራኬ አፀደቀለት፡፡ ለዚህችውም ተድባበ ጽዮን ቤተ መቅደሱን ሰርቶ ሲጨርስ ከሌዋውያኑም ከካህናቱም ከፍሎ መስዋተ ኦሪት የሚሰው ካህናትና ሌዋውያንንም ሾመ፡፡

መስፍኑ ሳቤቅ ቤተልሄማዊም በገፀ ንጉስ በወርቅ ወንበር የሚቀመጥ ነበር፡፡ ከዚህ ላይ ገሊላ ብሎ ከሰየመ በኋላ አገሮቹን አሻግሮ እያየ በሀገሩ ምሳሌ ይሰማቸው ጀመር፡፡ ደብረ ዘይት፣ ኬብሮን አሁን ከቀን ብዛት የተነሳ ህዝቡ ኬብሮንን ከሚኖር ይለዋል ይኽውም ከተድባበ ማርያም አምባ በር ወደ ምስራቅ ያለውን መግቢያ ነው፡፡

ወደ ቀኝ በኩል ተመልከተና እያሪኮ ትባል አለ ከቀን ብዛት ግን ሕዝቡ እያሪኮን አራሆ ይሏታል ቀጥሎ ኢየሩሳሌም ቀጥሎ ሎዛ ከዚህ ከሎዛ በላይ ታቦር አለው ይኸውም በአፄ በዕደ ማርያም ዘመን መግስት የተነሱት የቅኔ ፈጣሪዎች እነ ዮሐንስ ገብላአዊ፣ እነ ሠምራ አብ፣ እነ ወልደ ገብርኤል እነ ደቅ እስጢፋ የነበሩበት ነው፡፡

ከታቦር ቀጥሎ ሊባኖስ፣ ደማስቆ፣ አርሞንኤም፣ ደብር ፋራን፣ ደብረሲና አሁን ቦረና በመባል የሚጠራው::
በስተ ሰሜን በኩል ኮሬብ፣ ቃዴስ ደብረ ፍጌህ፣ ቂሣርያ፣ ቢታኒያ& ጋዛ ፣ ጎልጎታ፣ ፌልስጥኤም ወዘተ ተብለው ተሰይመዋል፡፡ ይኸውም መታሰቢያነቱ ለ12 ነገደ እስራኤል እንደሆነ ይነገራል፡፡

# ሥርዓተ በዓላት በተድባበ ማርያም
****
በዘመነ አራት የቂጣ በዓል የአይሁድ ፋሲካ ይከበር ነበር፡፡ ወደ ኢትዮጵያ ታቦተ ጽዮንን ተከትለው ከመጡት አስራ ሁለት ሺህ ነገደ እስራል ሁለት ሺህ አመስት መቶዎቹ ተድባበ ማርያም እንደገቡ ይነገራል፡፡

በዘመነ ክርስትና አብረሃ ወአጽብሃ ተድባበ ማርያምን
አንጽው ካበቁ በኋላ ጥር 21 ቀን በአሏን ለማክበር ደንግገው
ነበር፡፡ ይህም የበአል አከባበር እስከ ዐፄ ገላውዴዎስ ከቆየ በኋላ ዐፄ ገላውዴዎስ ግራኝ አህመድን ድል አድርጎ ሲመለስ ግንቦት ፩ ቀን ተድባበ ማርያም በመግባቱ የገባሁት በልደቷ (እለቱ የእመቤታችን ልደቷ ነው) በማለት የልደታን ጽላት አሰገብቶ የተድባበ ማርያምን በአል ግንቦት ፩ ቀን እንዲሆን አዋጅ አስነገረ፡፡ ከዚያን ዘመን ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ግንቦት አንድ ቀን በደማቆ ሁኔታ ይከበራል፡፡

@MoaaTewahido
@MoaaTewahido
1.3K views08:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-04 22:37:23
327 views19:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-04 22:37:19
252 views19:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-04 15:26:38 በደቡብ ኢትዮጵያ…!!

• ኦርቶዶክሳውያን እየታረዱ ነው።
• አብያተ ክርስቲያናት እየወደሙ ነው።
• የዘር ማጥፋት እየተፈጸመ ነው።

"…በደቡብ ኢትዮጵያ በፅንፈኛ ፕሮዎች የሚመራ "ኮንሲታ" የተባለ ገዳይ ቡድን በኦርቶዶክሳውያን የጉማይዴ ነገድ አባላት ላይ መዓት በማዝነብ ላይ እንደሚገኝ እየተነገረ ነው።

"…ከታች ከላይ በምስሉ ላይ የሚታየው ጥፋትም የተፈጸመው በዚሁ የጥፋት ቡድን ሲሆን በ1903 ዓም የተቆረቆረችውና ከመቶ ዓመት በላይ መንፈሳዊ አገልግሎት ስትሰጥ የኖረችውን የዱጋያ ማርያም ቤተ ክርስቲያንን ነው በዚህ መልክ ያወደሟትም ተብሏል። "ኢየሱስ ጌታ ነው" እያሉ በመፎከር በተዋህዶ ላይ እንደ ኦነግ የዘመቱት ኮንሲታዎች ያለፈው መጋቢት 21/2014 ዓም በእመቤታችን በዕለተ ቀኗ የጣሪያ ቆርቆሮዋ ሳይቀር ነቅለው ዘርፈው የቀረውን በዚህ መልክ ሰባብረው፣ በታትነው፣ መሄዳቸው ነው የተነገረው።

"…የጉማይዴ ሕዝብ የጠየቀው የመዋቅር አደረጃጀት ጥያቄ ሲሆን የደቡብ ባለሥልጣናት የሚሰጡት ምላሽ ግን የሃይማኖት ሆኖ የበቀል ዱላቸውን የሚያሳርፉትም በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ ነው። ይህን ጥፋት ያየው የጉማይዴ ህዝብም በቁጣ ግልብጥ ብሎ ወጥቶ አውዳሚዎቹ ላይ እርምጃ ወስዶ የቅድስት ቤተ ክርስቲያኒቱን ቅፀር በድጋሚ ተቆጣጥሯል። በወራሪዎቹ የተሰደዱ ካህናትም ተመልሰዋል። እግዚአብሔር ይመስገንና ከተዋሕዶ ልጆች ወገን የእሷ ጥበቃ ታክሎበት አንድም ሰው ምንም ሳይሆን ደብራቸውን መልሰው ተቆጣጥረው አሁን ተራበተራ እየጠበቁ መሆናቸው ነውረ የመረጃ ምንጮቼ የነገሩኝ።

"…በጉማይዴ ችግር መፈጠሩን የኢሠመጉ በሪፖርቱ በስሱ የጠቀሰ ሲሆን በትናንትናው ዕለት ደግሞ ይሄው የኮንሲታ ፅንፈኛ ቡድን በገጠር እየዞሩ የምስኪን ገበሬዎች ላይ እሳት በመልቀቅ ዐመድ ሲያደርግ ውሏል።

ይህም የብልጽግና ፍሬ ነው!

ዘመድኩን በቀለ
242 viewsedited  12:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-04 15:26:26
220 views12:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-02 11:03:29 ደቡብ ክልል ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ ዞኖች በይፋ ፕሬቴስታንታዊ መንግስት የማወጅ ዝንባሌ እያሳዩ ነው
~~~~~~~
ይድረስ ለዳውሮ ዞን እና ለደቡብ ክልል ፓሊስ ኮምሽን
~~~~~~~

ይህ በዳውሮ ዞን ዋና ከተማ በሆነችው ተርጫ ከተማ ላይ በእስራኤል ዳንሳ አማካኝነት የተካሄደው ኮንፍራንስ ላይ የታየው የሕዝባዊ ፓሊስ አሳፋሪ ድርጊት ነው።

የትኛውም ወታደር ከሥራ ሰዓት ውጪ የግል እምነት ልምምዱን ማድረግ ህጋዊ ቢሆንም የህዝብ እና የመንግስት አደራ ያለበትን ወታደራዊ ዩኒፎርም የለበሱ የፓሊስ አባላት ሁሉንም የማገልገል የፓሊስነት ኃላፊነታቸውን ወደ ጎን በመተው እንዲህ በግል የእምነት ስካር ውስጥ ወድቆ ማዬት ያሳፍራል።

የፓሊስ ሠራዊትን እራሳቸውን ነብያት ፓስተር ብለው የሚጠሩ ሰዎች የግል ጋርድ እና የአምልኮ ስርዓት መፈጸሚያ ማድረግ ደቡብ ክልል ላይ ባሉ አንዳንድ ዞኖች የተለመደ መጥቷል።

በተለይ በወላይታ፣ዳውሮ፣ሀዲያ፣ከንባታ ዞኖች ላይ ይህ ትዕይንት በድፍረት እና ያለዕፍረት በተደጋጋሚ በገሃድ ይፈጸማል።

እንግዲህ በመርህ ደረጃ ሃይማኖት እና መንግስታዊ ምልክቶች አይደባለቁም በሚባልበት ሀገራችን ይህን አይነት ተግባር በሚፈጽሙት የህግ አስከባሪዎች ላይ ቁጥጥር ታደርጉ ዘንድ እየጠየቅን ወይም ኦርቶዶክሳዊ ሙስሊም የፓሊስ ሰራዊቶችም ከእነ ዩኒፎርማቸው ስርዓተ አምልኮ ይፈጽሙ ዘንድ ፍቃድ እንዲሰጣቸው እናሳስባለን።

ሳብስክራይብ በማድረግ የyoutube ቻናላችንን ቤተሰብ በመሆን አገልግሎቱን ይደግፉ።

https://youtube.com/user/0468811209
**

// ከሁሉም በላይ በምትሆን ሐዋርያት በሰሯት በአንት ቅድስት ቤተክርስቲያን እናምናለን //

የቴሌግራም ቻናላችን ከታች ያለውን ሊንክን በመስፈንጠር ቤተሰብ ይሁኑን፤ አብረው እናገልግል።

t.me/southethiopiaorthodoxy

የቴሌግራም የመወያያ ግሩፓችን ለመቀላቀል ከታች ያለውን መስፈንጠርያ በመንካት አባል ይሁኑን

https://t.me/southethiopiaorthodoxtewahidoun

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
262 views08:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ