Get Mystery Box with random crypto!

መንግሥት የሰጠውን የ72 ሰዓት ጊዜ በመጠቀም እጅግ በርካታ የትግራይ ሚሊሻና ልዩ ኃይል አባላት በ | FastMereja.com

መንግሥት የሰጠውን የ72 ሰዓት ጊዜ በመጠቀም እጅግ በርካታ የትግራይ ሚሊሻና ልዩ ኃይል አባላት በየግንባሩ እጅ እየሰጡ ነው ።

መንግሥት የሰጠውን የ72 ሰዓት ጊዜ በመጠቀም እጅግ በርካታ የትግራይ ሚሊሻና ልዩ ኃይል አባላት በየግንባሩ እጅ እየሰጡ መሆኑን የአስቸኳይ ጊዜ መረጃ ማጣሪያ አስታወቀ።

በአፋር ክልል በኩል ብዙዎች ገብተው እጅ የሰጡ ሲሆን በማይጸብሪ ተቆርጦ የቀረው ኃይል እጁን በሰላም በመስጠት ላይ መሆኑም ተገልጿል።

ጥሪውን ሰምተው እጅ በመስጠት ላይ ለሚገኙ የትግራይ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ አባላት ለሕዝባቸው በማሰባቸው መንግሥት ምስጋናውን ያቀርባል።

በጁንታው ኃይል ተጽዕኖ ውስጥ ሆናችሁ እጅ ለመስጠት ያልቻላችሁ ሁሉ በያላችሁበት ትጥቃችሁን ፈትታችሁና የጁንታው መጠቀሚያ ከመሆን ተቆጥባችሁ መከላከያ እስከሚደርስላችሁ እንድትጠብቁ በአጽንዖት እናሳስባለን።
-------------
@fastmereja