Get Mystery Box with random crypto!

በተመሳሳይ ከፍታ ርቀት ላይ በመጓዝ ላይ የነበሩት የኳታር እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአየር ት | FastMereja.com

በተመሳሳይ ከፍታ ርቀት ላይ በመጓዝ ላይ የነበሩት የኳታር እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ስህተት ምክንያት ከመጋጨት ለጥቂት መትረፋቸዉ ተነግሯል።

ንብረትነቱ የኳታር አየር መንገድ የሆነዉ አዉሮፕላን ( ኳታር 6 ዩ) ከዶሃ ተነስቶ ወደ ኡጋንዳ ኢንቴቤ በ 38,000 ጫማ ከፍታ ላይ ሲበር የነበረ ቢሆንም በሞቃዲሾ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች አዉሮፕላኑ ወደ 40,000 ጫማ ወደላይ እንዲወጣ ተነግሮታል።

በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ 6 : 32 ገደማ በተመሳሳይ በ39,000 ጫማ ከፍታ ርቀት ላይ ከአዲስ አበባ ተነስቶ ወደ ዱባይ ሲጓዝ ከነበረዉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዉሮፕላን ( ኢቲ 602)
ጋር የተፋጠጠዉ የኳታር አዉሮፕላን ከመጋጨት ለጥቂት መትረፉ ተዘግቧል።

ሁለቱ ካፒቴኖች ስለ ክስተቱ ሲነጋገሩ የተቀረጹት ቅጂዎች ሁለቱም በሞቃዲሾ ከሚገኙ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች የተሳሳተ መመሪያ እንደተቀበሉ ያሳያል ተብሏል።

በሁለቱም አውሮፕላኖች ላይ የተገጠመው የግጭት ማስወገጃ ሲስተም (TCAS) ወዲያውኑ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል፣ ይህም በታዘዘው ከፍታ ላይ ሌላ አውሮፕላን መኖሩን በማመልከቱ ምክንያት በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ህይወት እንዲተርፍ ለማድረግ መቻሉ ዝግባዎች አመላክተዋል።

ይህን ተከትሎ በሞቃዲሾ የሚገኙት የፀጥታ ኃይሎች በሶማሊያ የሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን የሆኑትን ሙባረክ ኑር አሊን በቁጥጥር ስር እንዲዉል አደርገዋል ሲል ካፒታል ነው የዘገበው።

@fastmereja