Get Mystery Box with random crypto!

1.1 ቢሊዮን ብር የወጣበት 9ኛው የኃይሌ ሆቴል በወላይታ ሶዶ ከተማ ተከፈተ! #FastMereja | FastMereja.com

1.1 ቢሊዮን ብር የወጣበት 9ኛው የኃይሌ ሆቴል በወላይታ ሶዶ ከተማ ተከፈተ!
#FastMereja
ከ14 ዓመታት በፊት እ.ኤ.አ 2010 በኃይሌ ሪዞርት - ሀዋሳ የተጀመረዉ ጉዞ በአሁኑ ወቅት 8 ሆቴሎች እና ሪዞርቶችን በተለያዩ የሃገሪቷ ከፍሎች በሀዋሳ ፤ በአርባምንጭ ፤ በአዳማ ፤ በባቱ ፤ በጎንደር ፤ በሱሉልታ እና በአዲስ አበባ ገንብቶ በስራ ላይ ይገኛል።

ዘጠነኛ መዳረሻ የሆነው በደማቋ ወላይታ - ሶዶ ከተማ ባለ አራት ኮኮብ ሆቴል ተገንብቶ ተጠናቋል። ይህ በወላይታ ሶዶ የተገነባው ሆቴል 300 ለሚሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎች የስራ እድል ከመፍጠርም ባሻገር ከፍተኛ ጥራት ባለው የአገልግሎት ባህል ህብረተሰቡን ለማገልገል የቆመ መሆኑ ተገልጿል።

ሆቴላችን ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል የተለያየ አይነትና ስፋት ያላቸዉ 107 የእንግዳ ማረፊያ ክፍሎች፣ ደረጃቸውን የጠበቁ የመመገቢያ አዳራሾች እንዲሁም ባሮች፣ ከ15 እስከ 500 ሰዎችን በምቾት ሊያስተናግዱ የሚችሉ ሰባት ሁለገብ አዳራሾች፣ ከፍተኛ ፍጥነት ያለው የበይነ መረብ (ኢንተርኔት) አገልግሎት፣ የእስቲም፣ የሳውና እና የማሳጅ አገልግሎት፣ የስፖርት ማዘወተሪያ ስፍራዎች (የመዋኛ ገንዳ እና ጂምናዚየም)፣ በቂ የሆነ የመኪና ማቆሚያ ስፍራ ለደህንነት ከተገጠሙ የ24 ሰዓት የጥበቃ ካሜራዎች።

የእንግዳ ማረፊያ ክፍሎቹ በሚገባ የተሰናዱ እና የተዋቡ እንደሆኑ ተነግሯል፤ በውስጣቸውም ስማርት (Smart TV) ከተለያዩ የቻናል አማራጮች ጋር፣ የ24 ሰዓት የክፍል ውስጥ መስተንግዶ አገልግሎት፣ የአየር ማቀዝቀዣ (AC)፣ ከእፅዋት የተቀመሙ ተፈጥሮዊ የመታጠቢያ ሳሙናዎች፣ የእሳት አደጋ መቆጣጠሪያ እና የአደጋ ጊዜ መውጫ ያላቸው፣ ከፍተኛ ፍጥነት ያለው የበይነ መረብ(ኢንተርኔት) አገልግሎት የተሟላላቸው ናቸው::

ለግንባታው 1.1 ቢሊዮን ብር ወጪ እንደሆነ ሻለቃ ኃይሌ ገ/ስላሴ ተናግሯል። በመክፈቻ ስነስርዓቱ ላይ የክልል፣ የዞን እና የሶዶ ከተማ ከፍተኛ የስራ አመራሮች ተገኝቷል።