Get Mystery Box with random crypto!

በሀረሪ ክልል የሚከበረው የሸዋል ኢድ በዓል በዓለም ቅርስነት ተመዘገበ የሸዋል ኢድ በዓል አከባበ | FastMereja.com

በሀረሪ ክልል የሚከበረው የሸዋል ኢድ በዓል በዓለም ቅርስነት ተመዘገበ

የሸዋል ኢድ በዓል አከባበር በተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ተቋም (ዩኔስኮ) በማይዳሰስ ቅርስነት በመመዝገቡ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

አቶ ኦርዲን ይሄንን ተከትሎም ሀረር በዩኔስኮ ሁለት ቅርሶችን ያስመዘገበች ብቸኛዋ የሃገራችን ያደርጋታል ብለዋል።

የክልሉ መንግስትም የዓለም ቅርስ የሆነውን የሸዋል ኢድ በዓል ለመጠበቅ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ የገለጹት ርእሰ መስተዳድሩ ቅርሱ በዩኔስኮ እንዲመዘገብ አስተዋጽኦ ለነበራቸው አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

የሸዋል ኢድ በዓል ሀገራችን በማይዳሰስ ቅርስነት በዩኔስኮ የተመዘገበ 5ኛ ቅርስ ሆኗል።
ኢትዮጵያ ካሏት ደማቅ ማህበራዊ እሴቶች ውስጥ አንዱ የሸዋል ኢድ በዓል አከባበር የአለም ቅርስ ሆኖ መመዝገቡም የቱሪስት ፍሰቱ እንዲጨምር ከማድረጉም ባለፈ የሀገር መልካም ገፅታ ለመገንባት የሚያግዝ መሆኑን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመለክታል።

@fastmereja