Get Mystery Box with random crypto!

#ፋሲል_ከነማ ስፖርት ክለብ አሰልጣኝ ሀይሉ ነጋሽን በዋና አሰልጣኝነት ሹሟል!! ኢትዮጵያ ቤትኪን | ፋሲል ከነማ (አፄዎቹ) እግር ኳስ ክለብ / Fasil Kenema Football Club ™🇦🇹

#ፋሲል_ከነማ ስፖርት ክለብ አሰልጣኝ ሀይሉ ነጋሽን በዋና አሰልጣኝነት ሹሟል!!

ኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው ክለባችን ፋሲል ከነማ ከቀድሞ አሰልጣኝ ስዩም ከበደ ጋር በስምምነት ከተለያየ በኋላ በምክትል አሰልጣኝ ኃይሉ ነጋሽ (ቲጋና) እየተመራ በጥሩ የዋንጫ ፉክክር ውስጥ ገብቶ ከመሪው ክለብ ጋር የነበረውን ሰፊ የነጥብ ልዩነት በማጥበብ የሁለተኛ ደረጃን በመያዝ በአስደናቂ ሁኔታ ማገባደዱ የሚታወስ ሲሆን የክለባችን የቦርድ አመራሮች በክለባችን ውስጥ በምክትል አሰልጣኝነት ለአራት አመት በማሳለፍ ያገለገለውን ባለብሩህ ተስፋ ሰጭ ወጣት አሰልጣኝ ለአንድ አመት በሚያቆይ ስምምነት በዛሬው እለት በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ውሉን አፅድቋል።

ፋሲል ከነማ በምክትል አሰልጣኝነት ሚና ሙሉቀን አቡሃይን ያስቀጠለ ሲሆን ክለባችን ወደ ፕሪምየር ሊጉ ሲያድግ የአሰልጣኝ ዘማርያም ምክትል የነበረው እና ከዛም በዋና አሰልጣኝነት አፄዎቹን የመራው አሰልጣኝ ምንተስኖት ጌጡ ደግሞ የአካል ብቃት አሰልጣኝ በመሆን የአሰልጣኝ ቡድኑን የቀላቅሏል።

ከዋና አሰልጣኝ ኃይሉ ነጋሽ (ቲጋና) ጋር ስለ 2015 አመት የውድድር አመት የጨዋታ አቀራረብ፣ ስለ አፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ጨዋታ አጠቃላይ ዝግጅት ምን እንደሚመስል ያቀረብነውን መጠይቅ ከዝግጅት ምስሎች ጋር በቅርቡ ይዘንላችሁ እንቀርባለን።

#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው


@fasilkenema_sc_official