Get Mystery Box with random crypto!

#ፋሲል_ከነማ ጋምቢያዊ ዜግነት ያለውን አጥቂ አስፈርሟል!! በኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ሁ | ፋሲል ከነማ (አፄዎቹ) እግር ኳስ ክለብ / Fasil Kenema Football Club ™🇦🇹

#ፋሲል_ከነማ ጋምቢያዊ ዜግነት ያለውን አጥቂ አስፈርሟል!!

በኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው ክለባችን ፋሲል ከነማ በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ኢትዮጵያን የሚወክል ሲሆን ለቀጣይ የ2015 አመት የፕሪሚየር ሊግ ውድድር ቡድኑን ለማጠናከር አዳዲስ ተጫዋቾችን በማስፈረም ላይ የሚገኝ ሲሆን ከዚህ ቀደም በቃል ደረጃ ከስምምነት ደርሶ የነበረውን ጋምቢያዊ ዜግነት ያለውን አጥቂ በዛሬው ዕለት የግሉ አድርጓል፡፡

ፋሲል ከነማ ያስፈረመው አጥቂ ጋራይ ጆፋን ዜግነቱ ጋምቢያዊ ሲሆን እድሜው 24 ቁመቱ 1-82 ሲሆን በሀገሩ ጋምቢያ የጀመረው የእግር ኳስ ህይወቱ በእስራኤል እና ጆርጂያ ክለቦች ቀጥሎ በጥሩ አቋም ላይ እንዳሳለፈ መረጃዎች የሚገልፁ ሲሆን #ጆፋን ወጣት ፣ ፈጣን እና ባለክህሎት ተጫዋች በመሆኑ በክለባችን ውስጥ ትልቅ ግልጋሎት እንደሚሰጥ ታምኖበት ለአንድ አመት በሚያቆይ ውል ፈርሟል።

#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው

@fasilkenema_sc_official