Get Mystery Box with random crypto!

ከዚህ አንጻር የኢትዮጵያ የንብረት ታክስ ህጎች ሁለት መሰረታዊ ውስንነቶች አሉባቸው፡፡ከእነዚህም ው | Farankaa - ፈራንካ

ከዚህ አንጻር የኢትዮጵያ የንብረት ታክስ ህጎች ሁለት መሰረታዊ ውስንነቶች አሉባቸው፡፡ከእነዚህም ውስጥ በአሁኑ ጊዜ ባለው የሀገሪቱ የንብረት ታክስ አጣጣል መሰረት በከተማ መሬቶች ላይ የሚጠል ታክስ አለመኖሩ አንደኛው ነው፡፡ በአዋጅ ቁጥር 80/1968 መሰረት የከተማ መሬቶች ባለዞታዎች ከሚከፍሉት የመሬት መተቀሚያ ኪራይ ውጪ የመሬቶቹ ባለይዞታ በመሆናቸው የሚከፍሉት የንብረት ታክስ የለም፡፡
በሌላ በኩል በአዋጅ ቁጥር 80/1968 መሰረት ታክስ የሚጣልባቸው ንብረቶች የከተማ ቤቶች ሲሆኑ ይህም ሁኔታ በሌሎች ሀገራት ካለው እና ቤቶችን ጨምሮ በሁሉንም አይነት ግንባታዎች ወይም ህንጻዎች ላይ ከሚጣለው የንብረት ታክስ አንጻር ሲታይ ውስንነት አለው፡፡

በሀገሪቱ ካሉት የንብረት ታክስ ህጎች ውስንነት በተጨማሪ ያሉትን ህጎች ለማስፈጸም የሚረዱ የመሰረታዊ ሁኔታዎች አለመሟላት ችግርም ይስተዋላል፡፡በዚህ ረገድ የንብረቶች የንበረቶች ዋጋ ተመን አንዱ እና ዋነኛው ነው፡፡ከላይ እንደመለከትነው የንብት ታክስ ዋጋን መሰረት ያደረገ (ad valorem) የታክስ አየነት ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ታክስ የሚጣልባቸው ንብረቶች ዋጋ መታወቁ አስፈላጊነት አለው፡፡ የእነዚህ ንብረቶች ዋጋ በየግዜው መተመን እና ወቅታዊ ዋጋቸውን ማወቅም ለንብረት ታክስ ፍትሀዊነት እና ውጤታማነት ጉልህ ሚና አለው፡፡

በአሁኑ ግዜ በሀገራችን ያለውን የንብረቶችን ዋጋ አተማመን ስንመለከት የወቅታዊነት ችግር ይስተዋልባቸዋል፡፡ ለአብነትም ያህል በመዲናችን በአዲስ አበባ ያለውን የንብረቶች ዋጋ አተማመን ስንመለከት ይህ ስራ የተሰራው ከሶስስት አስርት አመታት በፊት እንደሆነ እንገነዘባለን፡፡ ይህም የንብረቶቹን ወቅታዊ ዋጋ ከማሳወቅ እንዲሁም የንብረት ታክስን በፍተሀዊነትእና በውጤታማነት በመተግበር ረገድ ችግር መፍጠራቸው አያጠራጥርም፡፡ ይህንንም በአሁኑ ግዜ የንብረት ታክስ ለከተማ መስተዳድረሩ ከሚያስገኘው ገቢ መረዳት ይቻላል፡፡ በአሁኑ ግዜ በከተማ መስተዳድሩ ያለው የዚህ ታክስ ሽፋን ከአጠቃላይ የከተማ መስተዳድሩ ገቢ ከሁለት በመቶ ያነሰ ነው፡፡

ይህም በሌሎች ሀገራ ካለው እና እስከ መቶ ፐርሰንት ሽፋን የከተሞች ገቢ ከሚያስገኘው የንብረት ታክስ አንጻር በእጅጉ አነስተኛ ነው፡፡


የንብረት ታክስ አጣጣል በኢትዮጵያ

አዋጅ ቁጥር 80/1968 የከተማ መሬት ኪራይን እና የከተማ ቤቶችን ታክስ ወይም ግብርን አስመልክቶ የተደነገገ ሲሆን በዚህ አዋጅ አንቀጽ 5 መሰረት በከተሞች የሚገኙ ቤቶች ባለቤት የሆኑ ግለሰቦች፣ ቤተሰቦች፣ ድርጅቶች፣ ወይም ህብረት ስራ ማህበራት ባለቤት በሆኑበት ቤት ላይ ግብር ወይም ታክስ መክፈል እንዳለባቸው ይደነግጋል፡፡ ከዚህ አዋጅ በመቀጠል የወጣው አዋጅ ቁጥር 161/1972 በፊተኛው አዋጅ ላይ መሰረታዊ መሻሻል ላደረገ በመሆኑ ይኸው አዋጅ ቁጠር 80/1968 የንብረት ታክስን በዋናነት ይገዛል፡፡
በዚህ አዋጅ መሰረት በከተማ የሚገኙ ቤቶች ባለቤቶች ግብር ወይም ታክስ መክፈል የለባቸው ሲሆን ይህንን ታክስ ለማስላትም የቤቶቹ አመታዊ ኪራይ ለንብረቶቹ ዋጋ አተማመን እንደሚያገለግል ተመልክቷል፡፡

የንብረቶችን የኪራይ ተመን መሰረት በማድረግ የተለያየ ዋጋ ያላቸው ንብረቶች በተለያየ የታክስ የማስከፈያ ልክ (tax rate) ግብር እነዲጠልባቸው የሚደረግ ሲሆን ይህንን ዋጋ ከግምት ውስጥ በማስገባትም አነስተኛ የኪራይ ዋጋ ግምት ያላቸው መኖሪያ ቤቶች ከንብረት ታክስ ክፍያ ነጻ ይሆናሉ፡፡

ከንብረት ታክስ ነጻ የሚሆኑ ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 80/1968 ውስጥ የተዘረዘሩ ሲሆን እነሱም የሚከተሉት ናቸው፡፡
• መንገዶች አደባባዮች ፣ መዝናኛ አና የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች እና መካነመቃብሮች
• የአምልኮ ስፍራዎች እና ግቢዎቻቸው ለትርፍ ያልተቋቋሙ ትምህርት ቤቶች እና ትምህርት ቤቶች
• የመንግስት በጀት የሚንቀሳቀሱ መንገስታዊ መስርያ ቤቶች
• አመታዊ የኪራይ ተመናቸው ከ300 ብር በታች የሆኑ መኖሪያ ቤቶች
እነዚህ ከንብረት ታክስ ክፍያ ነጻ የሆኑ ንብረቶችን አስመልክቶ ግልጽ መሆን የለበት ነገር ንብረቶችን ከታክስ ክፍያ ነጻ የማድረግ አሰራር ለታሰበለት አላማ ብቻ መዋል ያለበት አሰራር መሆኑን ነው፡፡ ከዚህም ጋር በተያያዘ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ገዢ የሆነ ውሳኔ ወስነኗል፡፡በየሰ/መ/ቁ. 66474 ላይ እንደተወሰነው በአዋጅ ቁጠር 80/1968 መሰረት ከ ንብረት ታክስ ነጻ የሚሆኑት በዚሁ ህግ በግልጽ የተመለከቱት የንብረት አይነቶች እንጂ እነዚህን ንብረቶች ሽፋን
በማድረግ ሌሎች ንብረቶችን ከዚህ ታክስ ነጻ ማድረግ አይቻልም፡፡በሀገራችን ስላለው የንብረት ታክስ እናንተስ ምን ትላላችሁ?