Get Mystery Box with random crypto!

የፋኖስ ንፅረቶች (✍በአይሳነው)

የቴሌግራም ቻናል አርማ fanwithay — የፋኖስ ንፅረቶች (✍በአይሳነው)
የቴሌግራም ቻናል አርማ fanwithay — የፋኖስ ንፅረቶች (✍በአይሳነው)
የሰርጥ አድራሻ: @fanwithay
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 206
የሰርጥ መግለጫ

------------
ሃሳብህ ሲራቀቅ፣ ዕውቀትህ ሲጠልቅ፤ ተግባርህ ሲፀድቅ ምንም ዓይነት የሕይወት ፈተና አይጥልህም!
#ግጥም
#አጫጭር_ልብ_ወለዶች
#አጫጭር_ወጎች
#ከእውነታ_ጥግ
#ከአመለካከት_ጥግ
#ከሀሳብ_ጥግ
#ጥበብ_በፈገግታ
#ለማንኛውም_አስተያየት
@Fanos_am24

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-02 19:07:14 አንድ ጥበበኛ ሰው በአዳራሹ ውስጥ ተሰብስበው ለሚያዳምጡት ሰዎች አንድ ቀልድ ጣል ሲያደርግ ሁሉም ከልባቸው ሲስቁ አዳራሹ በሳቅ ጩኸት ተሞላ።
ከትንሽ ቆይታ በኋላ ጥበበኛው ቅድም ያወራውን ቀልድ ደገመላቸው። በዚህን ጊዜ የሳቁት ሰዎች ግን ጥቂት ብቻ ነበሩ።
ጥበበኛው ያንን ቀልድ ምንም ሰው እስከማይስቅ ድረስ እየደጋገመ ነገራቸው።
በመጨረሻም ጥበበኛው ፈገግ አለና እንዲህ አለ፦
"በተመሳሳይ ቀልድ ብዙ ጊዜ ደጋግማችሁ አትስቁም፣ ነገር ግን ለምንድነው በተመሳሳይ ነገር እየደጋገማችሁ የምታለቅሱት።"

@fanwithay
56 views" Aysanew " Mente", 16:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 13:30:58 ስቴቨን ኮቬይ እንደሚለው “አንድ

ሲደመር አንድ ከሁለት በላይ ነው”፡፡

7. መጋዛችሁን ሳሉ

ስቴቨን ኮቬይ መጽሐፉ ውስጥ ግሩም አፈ ታሪክ አለ፡፡ አንድ ተጓዥ መንገደኛ በአንድ ጫካ ውስጥ አቋርጦ ሲያልፍ አንድ ምስኪን እንጨት ቆራጭ ላቡ ጠፍ እስከሚል ድረስ ያለምንም እረፍት እንጨት ሲቆርጥ ይመለከታል፡፡ ተጓዡ መንገደኛ ቆም ይልና የመጋዙን መደነዝ አስተውሎ ኑሮ “ወዳጄ! ለምን መጋዝህን ዕረፍት ወስድህ አትስለውም?” ይለዋል፡፡ ልፋ ያለው እንጨት ቆራጭ “አይ ለሱ እንኳን ጊዜ የለኝም” የሚል የዋህ ምላሽ ይሰጠዋል፡፡ ይኼ ምስኪን እንጨት ቆራጭ ዕረፍት ወስዶ መጋዙን ቢስል በተሻለ ቅልጥፍና ብዙ እንጨት መቁረጥ እንደሚችል አልተረዳም፡፡

የተራ ቁጥር ሰባት ልምድ መልዕክት ቀላል እና ግልጽ ነው፡፡ በቂ ዕረፍት ምንጊዜም አድርጉ ነው፡፡ ከስራ በኋላ ራሳችሁን ዘና የማድረግ ልምምዱ ይኑራችሁ፡፡ መዝናናት ለጊዜው ከሚሰጠው ደስታ ባሻገር ለቀጣይ ስራ ያዘጋጃል፡፡ ሁልጊዜም እንደምለው ትልልቅ ኩባንያዎች ወጪ ችለው፣ ወርሃዊ ደሞዝ መክፈላቸውን ሳያቋርጡ ሰራተኞቻቸውን የሚያዝናኑት በጣም ቸር ስለሆኑ አይደለም፡፡ ይልቁንም የተዝናና ሰራተኛ ይበልጥ ውጤታማ እንደሚሆን እና እነሱንም ይበልጥ ውጤታማ እንደሚያደርጋቸው ጠንቅቀው ስለሚያውቁ ነው፡፡

አንድ አንድ ሰዎች “እኔ መዝናናት አይሆንልኝም” ይላሉ፡፡ “መዝናናት ራሱን የቻለ ችሎታ ነው” ይላል አንድ ሌላ ወዳጄም፡፡ በመሆኑም “እንዴት እንዝናና?” የሚል ጥያቄ ያላችሁ ሰዎች እነዚህን የመዝናኛ አማራጮች እንድትፈትlቸው እጋብዛለሁ፡- ዋና ዋኙ፤ ከወዳጅ ዘመዶቻችሁ ጋር አስደሳች ጊዜ አሳልፉ፤ ዮጋ ስሩ፤ ዳንስ ደንሱ፤ ከከተማ ከተቻለም ከሀገርም ወጣ ብላችሁ ጎብኙ፤ ደስታ ይሰጠኛል ብላችሁ የምታስቡትን የትርፍ ጊዜ የመዝናኛ አማራጭን (Hobby) ሞክሩ፡፡

ቸር እንሰንብት!

@fanwithay
85 views" Aysanew " Mente", 10:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-27 20:15:19 #እጅግ_በጣም_ስኬታማ_የሆኑ_ሰዎች_7_ልምዶች
በጣም አስተማሪ መልዕክት ነው #SHARE
@fanwithay

ከአስራ አምስት ሚሊዮን ቅጂ በላይ ተሽጧል፤ በሰላሳ ቋንቋዎች ተተርጉሞም ለንባብ በቅቷል፤ በእኛው አማሪኛ ቋንቋም ተተርጉሞ መታተሙንም አውቃለሁ፡፡ ይህ መጽሐፍ “The 7 Habits of Highly Effective people” ይባላል:: “እጅግ በጣም ስኬታማ የሆኑ ሰዎች 7 ልምዶች” ብለን ቃል በቃል እንተርጉመው፡፡ የመጽሐፉ ደራሲ ስቴቨን ኮቬይ ይባላል፡፡ ይህ መጽሐፍ በግለሰብ ደረጃ ብልፅግናን (Personal development) ለመፍጠር እንዲረዱ ታስበው እስከ ዛሬ ድረስ ከተጻፉ መጽሐፍት መካከል ወደር የማይገኝለት ነው፡፡ ካላነበባችሁት እንድታነቡት እመክራለሁ፡፡ ያነበብነውም ደግመን ልናነበው ይገባል የሚል እምነት አለኝ፡፡

የዚህ ድንቅ መጽሐፍ ደራሲ ስቴቨን ኮቬይ “ውስጣዊ ድል ከውጫዊ ድል ይበልጣል” ይላል፡፡ እዚህ ምድር ላይ ማግኘት የምንፈልጋቸውን ነገሮች በሙሉ ለማግኘት አስቀድመን ራሳችንን ማሸነፍ፤ የህይወታችን ሾፌር መሆን፤ ውስጣዊ ማንነታችንን መቆጣጠር ወዘተ አለብን ማለት ነው፡፡ “ከተማን ከሚመራ ሰው ይልቅ ራሱን የሚመራ ሰው ይበልጣል” ይላል ጠቢቡ ሰለሞን፡፡ ራስን ማሸነፍ ሌሎች ውጫዊ ነገሮችን የማሸነፊያ ቁልፍ ነው፡፡ በመቀጠል በቅደም ተከተል የምንመለከታቸው 7 ልምዶች ማንኛውም ሰው የግል ህይወቱ መሪ እንዲሆን በእጅጉ የሚያግዙ ናቸው፡፡ አሁን ቦታውን ለእነዚህ ልምዶች ለቀቅ እናድርግ እስኪ፡፡

1. ኃላፊነት ውሰዱ

ጅብ ከሄደ በኋላ የውሻ መጮህ ምንም ውጤት አያመጣም፤ ትርፉ ድካም ነው፡፡ ውጤት የሚያመጣው ጅቡ ከመምጣቱ በፊት አስቀድሞ በማነፍነፍ ድምጽ ማሰማት ነው፡፡ ሁኔታዎችን፣ ሌሎች ሰዎችን፣ ዓለምን ወዘተ የሚወቅሱ ሰዎች በህይወታቸው የረባ ቁም ነገር አያከናውኑም፤ ሁልጊዜም ኃላፊነትን የሚያሸክሙት ከእነሱ ውጪ ላለ ሌላ አካል ነው፡፡ ኃላፊነትን መሸከም ስንችል ነው የህይወታችንን ጉዞ አቅጣጫ መወሰን የምንችለው፡፡ የተሸከርካሪውን መሪ ለሌላ አካል አሳልፈን ሰጥተን የምፈልገው ቦታ አይደለም የደረስኩት፤ በፈለኩት ፍጥነት አይደለም እየተጓዝኩ ያለሁት ወዘተ ልንል አንችልም፤ ብንልም ዋጋ የለውም፡፡ የጉዞውን አቅጣጫ፣ ፍጥነት እና አድራሻ የሚወስነው አሽከርካሪው ነው፡፡ ልምዳችን መውቀስ፣ ጣት መጠቆም፣ ራስን መከላከል ወዘተ ከሆነ እውነቱን ለመናገር የሚወቀስ ነገር ማግኘት አይከብድም፡፡ ዘወትር የእናቴ መቀነት አደናቅፎኝ ነው ማለት ህይወታችን ባለህበት እርገጥ እንዲሆን በር ወለል አድርጎ ይከፍታል፡፡ ስለዚህ ለውጥ ለማምጣት፣ የራሳችን ሰዎች ለመሆን፣ ውስጣችንን ድል ለማድረግ ወዘተ ሁልጊዜም ለገዛ ራሳችን ህይወት ሙሉ ኃላፊነት እንውሰድ፡፡ ቃላችንን የምናከብር፤ በአልንበት ቦታ የምንገኝ፤ በገዛ ራሳችን ጥረት የምንፈልገውን ማንኛውንም ዓይነት ነገር እጃችን ለማስገባት መጓዝ ያለብንን ያህል ርቀት መጓዝ የምንችል ሰዎች እንሁን፡፡ “ስራ እኮ ጠፋ! እኔ ምን ላድርግ?!” ከማለታችን በፊት ስራ ለማግኘት የምንችለውን ድንጋይ በሙሉ መፈንቀላችንን እርግጠኛ እንሁን፤ ቀጣሪዎች የሚፈልጉትን ዕውቀት እና ክህሎት ይዘን ለመገኘት ጥረት እናድርግ፤ የተለመደውንም ያልተለመደውንም አማራጭ እንፈትሽ፡፡ ሳይኮሎጂስቶች “Life is 10 % what happens to us and 90 % how we react to it” ይላሉ፡፡ የህይወታችንን አብዛኛውን (90 %) ክፍል በምንፈልገው መልኩ መስራት እንችላለን ማለት ነው፡፡ የምናጭደው የዘራነውን ነው፡፡

2. የምትፈልጉትን ነገር አስቀድማችሁ እወቁ

ስቴቨን ኮቬይ “ነገሮች ሁለት ጊዜ ይፈጠራሉ” ይላል፡፡ የመጀመሪያው ፈጠራ የሚጠናቀቀው አእምሮአችን ውስጥ ነው፡፡ ከቤት ከመውጣታችን በፊት የምንሄድበትን ማወቅ ይኖርብናል፡፡ ከአንድ እና ሁለት፣ አምስት እና አስር ዓመት ወዘተ በኋላ ምንድን ነው ማግኘት፣ ማድረግ፣ መሆን ወዘተ የምንፈልገው? ለእነዚህ ጥያቄዎች አጥጋቢ መልስ መስጠት ነገሮቹ በተጨባጭም ወደ ህይወታችን የሚመጡበትን ዕድል ከፍ ያደርጋል፡፡ “We rise to the level of our expectations” ይባላል፡፡ የምናገኘው የምናስበውን ነው፤ የምንደርሰው እንደርሳለን ብለን የምናስበው ከፍታ ድረስ ነው፡፡ ግባችንን ማወቃችን ትኩረታችንን ለመሰብሰብ ይረዳናል፤ ከነፈሰው ጋር አንነፍስም፤ በፈተና መካከል ጸንተን እንቆማለን፡፡ ሳይኮሎጂስቶች የህይወታችንን ግብ በቅጡ ለመለየት የሚረዳን አንዱ ሁነኛ መንገድ “የቀብራችን ዕለት እንዲነበብ የምንፈልገውን የህይወት ታሪካችንን መወሰን ነው” ይላሉ፡፡ ቁጭ ብለን ልናስብበት ይገባል፡፡

3. ቅድሚያ ለሚገባቸው ነገሮች ቅድሚያ ስጡ

“ሁሉ አማረሽን ገበያ አታውጧት” ይባላል፡፡ ቅድሚያ መስጠት ላለብን ነገሮች ቅድሚያ መስጠት አለብን፡፡ ሁለት እግር አለኝ ተብሎ ሁለት ዛፍ ላይ አይወጣም፡፡ ኮቬይ እንዲህ ይላል፡- “ራሳችሁን ከእነዚህ ሶስት አጉል ልምዶች በአንዱ መውቀስ ቢኖርባችሁ በየትኛው ነው የምትወቅሱት? (1) መስራት ያለብኝን ነገር በቅደም ተከተል መለየት አልችልም፤ (2) በአስቀመጥኩት ቅደም ተከተል መሰረት መስራት አልችልም፤ (3) በወሰንኩት ቅደም ተከተል መሰረት ለመስራት አስፈላጊው ቁርጠኝነት የለኝም፡፡ ብዙ ሰዎች ቁርጠኝነቱ የለኝም ነው የሚሉት፡፡ ጠለቅ ብለን ከመረመርነው ግን እውነቱ ሌላ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ እውነቱ ቅደም ተከተሉ ውስጣችን በጥልቀት አለመስረጹ ነው፡፡ ልምድ 2ን ማለትም የህይወት ግባችንን አስቀድመን በሚገባ ለይተን በሚገባ ውስጣችንን መቅረጽ አለመቻላችን ነው”::

4. በጋራ እኩል ተጠቃሚነት መርህ ተመሩ

ከተቃራኒ ፆታ ጀምሮ እስከ የንግድ ስራ ግንኙነት ድረስ በጋራ እኩል ተጠቃሚነት መርህ መመራት ትልቅ ጥቅም አለው፡፡ “አዎ! በሚገባ አምንበታለሁ፡፡ በእኩል ተጠቃሚነት መርህ ነው ህይወቴን የምመራው፡፡” ትሉ ይሆናል፡፡ እንደምትሉት እንደምትኖሩ ግን እርግጠኛ ሁኑ፡፡ ለማሸነፍ ከመጣር ይልቅ እንዴት በጋራ እኩል ተጠቃሚ ለመሆን ጥረት አድርጉ፡፡ የበለጠ ተጠቃሚ ለመሆን፣ ከሌላው ከፍ ብሎ ለመታየት፣ ልክ ሆኖ ለመገኘት ወዘተ ከመጨነቅ ይልቅ በጋራ እኩል እንዴት ተጠቃሚ መሆን እንደሚቻል ማሰብ እና ይህንን መርህ በየትኛውም የግንኙነታችን መረብ ውስጥ ተግባራዊ ማድረግ ይበልጥ ውጤታማ ያደርገናል፡፡

5. መጀመሪያ ለመረዳት ጥረት አድርጉ

መጀመሪያ ስንረዳ የሚረዱንን እናገኛለን፡፡ ብዙ ጊዜ ግን በአንጻሩ ጊዜያችንን የምናጠፋው ሰዎች እንዲረዱን በመፍጨርጨር ነው፡፡ ቆም ብለን  “ምንድነው እስኪ እያሉ ያሉት? ልክ ይሆኑ ይሆን? በየትኛው ማዕዘን ነው እነሱ ጉዳዩን ያዩት?” ወዘተ ብሎ በቀናነት ማሰብ እና ሰዎችን ለመረዳት ጥረት ማድረግ ጥሩ ነው፡፡ ሰዎችን የመረዳት ችሎታችን ጥሩ ሲሆን የሚረዱንን ሰዎች ቁጥርም ይጨምራል፡፡

6. 1 + 1 = 3

“ድር ቢያብር አንበሳ ያስር” ትልቅ መልዕክት ያለው አባባል ነው፡፡ በጋራ የሚሰሩ ስራዎች በግል ከሚሰሩ ስራዎች ይልቅ የላቀ ውጤት ያመጣሉ፡፡ አንድ እጅ ብቻውን አያጨበጭብም፡፡ ሩጫን በመሰለ የግል ጥረትን በከፍተኛ ሁኔታ በሚጠይቅ የውድድር ዘርፍ እንኳን አትሌቶቻችን ሲተባበሩ የሚያስመዘግቡትን አንጸባራቂ ድል እናውቀዋለን፡፡ በየትኛውም አጋጣሚ በጋራ የመስራትን መንፈስ ማዳበር ጠንካራ ያደርጋል፤ የበዛ ፍሬም ያፈራል፡፡ አብረን መብላት ብቻ ሳይሆን አብረን መስራትንም ባህላችን እናድርግ፡፡
209 views" Aysanew " Mente", 17:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-14 22:55:12 # የአለም__እውነታወች
1. የሚከተልህ ሁሉ አድናቂህ አይደለም

2. ውሻ ጭራውን የሚቆላው ላንተ ሳይሆን
በእጅህ ላለው ዳቦ ነው፣ አስመሳይና
ተለማማጭ ሰውም እንዲሁ ነው።

3. ሕይወት ድልድይ ናት፣ አቋርጣት እንጂ
በላይዋ ላይ ቤት አትስራ።

4. ውሀ ቅርፁን ከመያዣው ጋር እንደሚስማማ
ሁሉ ብልህም ራሱን ከሁኔታው ጋር ይስማማል።

5. ምንም ያህል ርቀት በተሳሳተ መንገድ
ብትጓዝም ወደኋላ ተመለስ።

6. ዝቅ ብለህ ብትመለከት ምን ያክል ከፍ
እንዳልክ ታውቀዋለህ።

6. አንድ ሰው ስትተዋወቀው በልብሱ
ልትመዝነው ትችላለህ፣ ስትለየው ግን
በአስተሳሰቡ ትመዝነዋለህ።

7. ሠርግ እና ቀብር አንድ ናቸው። ልዩነቱ
የሠርግ አበባን ባለቤቱ ማሽተት መቻሉ ብቻ
ነው።

8. አምላክህን ደስታህን በቅንነት ብትጠይቀው
ይሰጠሀል። ብቻ በቤትህ በሀቀኝነት ኑር።

9. ማንክያ የሾርባን ጣዕም እንደማያውቅ ሁሉ
ለስሙ የተማረም የጥበብን ጣዕም አያውቅም።

10. ሀገር እንዳትጠፋ ትልቅ ነገርን አታጥፋ።
"ሰው ሆይ በትዕቢትና በንቀት መወጠርህን
አቁም። የውሸት መኖርህን፣ ሰዎችን መበደልህን፣
ፈጣሪህን ማሳዘንህን አቁምና መልካም ነገርን
አድርግ። ልብ በል ሺህ ጊዜ የውሸት ብትኖር
አንድ ጊዜ የእውነት መሞትህ አይቀርም።

ስንት ቁጥር ተመቻችሁ.?
psychoet
123 views" Aysanew " Mente", 19:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-10 13:15:13 ሶቅራጦስ በአቴና አደባባይ ሲዘዋወር ሳለ አንድ ጠቢብ ሰው ስለፅናት ሲያስተምር ያያል፡፡ ሶቅራጦስ የጠቢቡን ሰው ንግግር በማቋረጥ ጽናት ምን እንደሆነ ይጠይቀዋል፡፡ ሰውየውም ሲመልስ፡-
‹‹ፅናትማ ጠላት እየቀረበህ ቢመጣም ከቦታህ ሳትነቃነቅ መጠበቅ ነው›› አለው፡፡ ሶቅራጦስም፡-‹‹እቅድህ ከሽፎ መሸሽ ቢኖርብህስ?›› ሲል ይጠይቀዋል፡፡ ጠቢቡም፡-‹‹በርግጥ በዚያን ጊዜ ፅናት ሌላ ይሆናል፡፡›› ሲለው ሶቅራጠስም ‹‹ስለዚህ ፅናት ከቦታህ አለመነቃነቅ ወይም ከቦታህ አለመሸሽ ካልሆነ ታዲያ ፅናት ምንድነው?›› ብሎ ይጠይቀዋል፡፡ ጠቢቡም ሰው ለጥያቄው የሚሰጠው መልስ ተቸግሮ ‹‹አሁን ሳስበው በትክክል ጽናትን የማውቀው አልመሰለኝም፡፡›› አለው፡፡

ሶቅራጦስም፡- ‹‹እኔም አላውቀውም›› ‹‹ነገር ግን ፅናት አዕምሮህን መጠቀም ነው፡፡ በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ብትሆን እንኳን ትክክለኛውን ነገር ብቻ ማድረግ ከቻልክ ያ ፅናት ነው፡፡›› በማለት ተናገረ፡፡
*ብቻ ዝም መለት ባለብክ ግዜ ዝም መለት *መናገር ባለብክ ጊዜ መናገር
*መሮጥ ባለብክ ጊዜ መሮጥ
*መቃወም ባለብክ ጊዜ መቃወም
*መደገፍ ባለብክ ጊዜ መደገፍ
አዎ! ትክክለኛውን ነገር በትክክለኛው ጊዜና በትክክለኛው ቦታ ማድረግ መቻል ፅናትም፣ ብልሃትም ነው ሃሳብህ ሲራቀቅ፣ ዕውቀትህ ሲጠልቅ፤ ተግባርህ ሲፀድቅ ምንም ዓይነት የሕይወት ፈተና አይጥልህም ለዚህም ምስጥሩ ማንበብክ ነው ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል ።
"ሰላም ለ ሓገራችን ሰላም ለ አለማችን ።

@fanwithay
134 views" Aysanew " Mente", edited  10:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-04 22:32:49 Try Again
።።።።።።።።።
ብትዘል ብትፈርጥ ከሌለህ አላማ
ወድቀህ ብትነሳ ብትቆስል ብትደማ
ክርስቶስ ካልሆነ ለህይወትህ መሪ
Try again ትባላለህ እንደ ፈጣን ሎተሪ


አይሳነው ( ምንቴ )
174 views" Aysanew " Mente", 19:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 15:15:25 ፍቅር ከሌለኝ ከንቱ ነኝ"
*
ዶላር እየዘገንኩ ለደኾች ባካፍል፤
ራእይ አለኝ ብዬ አገሩን ባካልል፤
ህልም ሁሉ ብፈታ ታምራት ብሰራ፤
ሽባ ብተረትር እውሩን ባበራ፤
ትንሹን ጉብታ ባደርገው ተራራ፤
ሸለቆ ብሞላ ገደል ሜዳ ባደርግ ፤
ጥበበኛ ብባል ብደርስ ከዕውቀት ጥግ፤
ዶለዙን ባሰላ ድ'ንኩን ሰው ባሳድግ፤
ዲዳ የሚያናግር ጸጋ እንኳ ቢኖረኝ፤
………….. ፍቅር ግን ከሌለኝ፤
………….. አበቃ ከንቱ ነኝ።

አይሳነው ( ምንቴ )

@Fanos_am24
186 views" Aysanew " Mente", 12:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-29 01:18:31 የቤት_እመቤት_በመሆን_ውስጥ_እመቤትነት አለ

ሕይወት_እምሻው

በአንድ ወቅት፣ ያገኘኋቸውን ወንዶች በሙሉ አንድ ጥያቄ ስጠይቅ ነበር፤ "የቤት እመቤት ማለት ምን ማለት ነው?" ከአንድ ወይም ሁለት መልሶች ውጪ የተሰጡኝ ፍቺዎች በሚከተሉት ሐረጎች ሊጠቃለል ይችላል።

"የማትሰራ ሴት"

"ሥራ የሌላት ሴት"

"ገቢ የሌላት ሴት"

"ሥራ አጥ ሴት"

"ሥራ ፈት ሴት"

እነዚህ መልሶች የሰጡኝን ወንዶች መልሼ ይሄንን ጥያቄ ጠየኳቸው።

ነጋ ጠባ አልጋ ማንጠፍ፣ ቆሻሻ ልብስ ማጠብ፣ የታጠበ ልብስ ማጠፍ፣ የታጠፈ ልብስ በየቦታው ማስቀመጥ፤ ከሻይ ማንኪያ እስከ በርሜል ሙልጭ አድርጎ ማጠብ ፣ የታጠበውን እቃ ማድረቅ ከሻይ ማንኪያ እስከ በርሜል ሙልጭ ተደርጎ የታጠበና የደረቀ እቃን በየቦታው ማስቀመጥ፣ ሥራ አይደለም?

በየቀኑ ከኩሽና እስከ ሳሎን ፤ ከሽንት ቤት እስከ ግቢ መጥረግና መወልወል፤

ከሳሎን ጠረጴዛ እስከ ቁም ሳጥን ጀርባ እና አልጋ ሥር ድረስ መጥረግና መወልወል፤

የቤቱን ሁሉ የተጠረገና የተወለወለ ቆሻሻን ሰብስቦ መጣልስ ፤ ሥራ አይደለም ?

ቀን ቆጥሮ አንሶላ ፤ ትራስ ልብስና አልጋ ልብስ መቀየር ፤ ጊዜን አስልቶ የኩሽና እቃ ግልብጥ አድርጎ አውጥቶ ማጽዳት፤ ጊዜን ወስኖ የመስኮትና የበር መስታወትን በጋዜጣ ሲያፀዱ እና ሲያስውቡ መዋል ፤ የአደፈ መጋረጃን መሐወጥ፤ ሥራ አይደለም?

"ምን አለቀ?" ብሎ ቀለብ መሸመት ፤ የተሸመተውን አመጣጥኖ ማዘጋጀት፤ የተዘጋጀውን ማቅረብና ቤተሰብ መመጠብ፤ ሥራ አይደለም? ደግሞ ከሁሉ በላይ፤

ልጅ ማርገዝ፤

ልጅ አምጦ መውለድ፤

ልጅ አጥብቶ ማሳደግ፤

ልጅ ማነጽ፤

ልጅን ለወግ ማብቃት ፤ ሥራ አይደለም?

እናም ወንድሞቼ...

አገልግሎትና ምርታማነት በጥሬ ገንዘብ በሚተመን የኢኮኖሚ ሥርአት ውስጥ በመኖራችን ብቻ ፤

በቀጥታ የገንዘብ ክፍያ የማያስገኝ ሥራ እንደ ሥራ በማይቆጠርበት ዓለም በመኖራችን ብቻ ፤ ይሄንና ሌላም ልዘረዝረው ብል መጽሀፍ የማይበቃውን ሥራ ሁሉ የምትሰራን ሴት "ሥራ የላትም" አትበለኝ።

ይልቅስ፣ በእኛ ሀገር የቤት እመቤት መሆን ፤ ከእመቤትነቱ ሸክሙ ይበልጣልና ፤ ሚዛናችሁን አስተካክላችሁ የቤት እመቤት ማለት ፤ "በዓለም ላይ ከባዱን ፤ ግን ክፍያ የሌለውን ሥራ የምትሰራ ሴት ማለት ናት" በሉኝ።

....................................................................
ብላለች እንደኔ እንደኔ አሳማኝ እና ልክ ነው ፡፡
እናንተስ ጋር ?



ጨረስኩ
:
234 views" Aysanew " Mente", edited  22:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-23 23:15:23 ......................ቃል ኪዳን........................

በብዕሬ ለቀወሶ ብዙ ቃላቶቸን ነበረ ስሰድር
የሚጣጣመውን እየመራረጥኩኝ
ለማዋደድ ስጥር
የቃላት ወንዞችን በነጣው
ሜዳላይ ለማፍሰስ ስታትር
ብዙም አልከበደኝ አንዱን ከአንዱ ሳስር፡፡

የልቤን ሀሳብ ልብ
እጅግ በርቶ እንዲታይ
ከፅሁፌ በላይ አስቀምጬ ከላይ
ሀሳቤን ስዛራው መስመሩን ሳልለያይ
አንዳች አልታከተኝ
ሁሉን በአንኩሮት ሳይ
ለካስ ልቤ ኖሩዋል ውጪን ሲያሳየኝ
ዳር ዳሩን ሲያፅፈኝ
መች ውስጡን አስነካኝ
የልቤ ውስጥ መድማት
ዛሬ አይኔ አሳየኝ : :

ከአይኖቼ ሚወጡት ነጭ የነበሩት
በጠቆረው ፊቴ ወርድው የሚፈሱት
ዛሬ ተቀይረው ቀይ ደም በሆኑት
የልቤን ውስጥ ህመም
ካአይኔ ተረዳሁት፡፡
እንደለመደብኝ ብዕሬን
አነሳው ልቤኑ ልፅፈው
ቃል ኪዳን በሚለው
ሁለት በሆኑ ቃላት በታሰረው
ለመፅሀፍ ቀሎ ለድርጊት ከራቀው
በፅሁፍ ስናየው እጅግ በሚቀለው
ሀሳቤን ጀመርኩት ልቤንም ላፅናናው
ነገር ግን አልቻልኩም እጅጉን ከበደኝ
ያን ሁሉ ቃላቶች የፃፉት እጆቼ
ጆሮ ዳባ አሉኝ
አይምሮዬ ከድቶኝ ማሰቡም ተሳነኝ
ሁለት የሚመስሉ ስናያቸው አንሰው
አንዱ ለአንዱ ሲሰጥ
በጣም የሚቀለው
እኔ ጋር ሲደርስ ግን ተራራ የሆነው
ብዕሬ እንኳን ታየኝ ለመፃፍ ስሞክር
ቃል ለሚለው ቃል
ማልቀሱን ትቶ እንባውን ሲቋጥር፡፡

አይሳነው ( ምንቴ )
@fanos_am24
187 views" Aysanew " Mente", edited  20:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-17 11:20:11 በልጅነቴ_ይሄን_ተማርኩ

ልጅ ሆኜ...
የአባቴ ዘመዶች እማዬ በሌለችበት ሲመጡ ፤ እሷ ዘመዶቿ ሲመጡ እንደምታደርገው ቤት ውስጥ ያለውን፣ እንቁላል ሁሉ ጠብሼ ፣ በብዙ ዳቦ አቀረብኩላቸው ። እማይዬ መጥታ የሆነውን፣ ስታውቅ ክፉኛ ገረፈችኝ።

ደግነት፥ ወገንተኝነት መሆኑን ያወኩት ያኔ ነው : :

ሁሌም ከኪሱ ብሮች የማይጠፋው ጓደኛኔ ጋር እየሄድን ነበር ፡ : አንድ ጉስቁልቁል ያለ ልጅ ፣
"ዳቦ ግዙልኝ” በርሃብ እያዛጋ ጠየቀኝ ።
ሁኔታውን ዐይቼ አላስችል ቢለኝ፤ ያለችኝን አንድ ብር ልሰጠው ከኪሴ ሳወጣ ፣ ጓደኛዬ እጄን ያዘና፣ “ለእሱ ከሰጠኸው ለአንተ፣ አይኖርህም”
አለኝ ።

ለጋስነት የድህነት መንስኤ መሆኑን፣ የተማርኩት ያኔ ነው ።

ሌላ ቀን ታላቅ እህቴ ፣ “እወደዋለሁ” እያለች፤ ከጋደኞቿ ጋር ቀን በቅን የምታነሳው ጎርምሳ ፣ ከታናሽ ወንድሙ ጋር ሰኞ ማክሰኞ ስጫወት መጣና
“እህትህ ግን ለምንድነው የምትጠላኝ?” ሲለኝ፤ “አረ እንደውም እሷ በጣም ትወድሃለች ፤ ለጓደኞቿ ሁሌ እወደዋለሁ እንዳለች ነው” አልኩት። ብዙም ሳይቆይ ነገሩን የደረሰችበት እህቴ፣ በንዴት እሳት ጎርሳ በርበሬ አጠነችኝ።

ምስጢርን በመጠበቅ ሽፋን፣ ውሸት መናገርን የተማርኩት ያኔ ነው።

አምስተኛ ክፍል ሆኜ አስተማሪያችን ጥያቄ ጠይቆ፣ የሚመልስ ቢጠፋ እጄን አውጥቼ የመሰለኝን ተናገርኩ ፡ : መሳሳቴ፣ “አንተ ደነዝ!”
ብሎ ሲናገረኝ የክፍሉ ተማሪ ሁሉ በአንድነት አውካካ።

ጥያቄን፤ መመለስ መሳለቅያ እንደሚያደረግ የተማርኩት ያኔ ነው : :

በኅብረተሰብ ክፍለ ጊዜ መምህራችን፣ “ሁላችሁም የአፍሪካ ካርታ ከመፀሀፍ ላይ እያያቹ
ደብተራችሁ ላይ ሳሉ" ብሎ አዘዘን ሁሉም ተማሪዎች ደብተራቸውን የጽሁፍ ስዕል ላይ አስደግፈው ፤የዋናውን ስዕል ጥላ እየተከተሉ ልክ እንደ መጽሐፉ አድርገው ስለው ሲመጡ ፤ እኔ ግን ፣ “እያያቹ ሳሉ” በተባለው መሰረት የመፅሐፉን ስዕል እያየሁ ሳላስደግፍ ደብተሬ ላይ ፣ “የኔን አፍሪካ” ስዬ መጣሁ : :
አስተማሪዬ አስደግፈው ለሳሉት ልጆች በሙሉ “እ...በ....ጥ...”እያሉ ፅፎ እኔ ጋር ሲደርስ ፣ እንደ ሌሎቹ ልጆች አስደግፈህ ብትሰራ ኖሮ እንዲህ
አይጣመምብህም ነበር ። ይሄ ምኑም አፍሪካን አይመስል!” ብሎ ዜሮ ከአስር ሰጠኝ : :

ቀድሞ የተሰራን ነገር፤ መቅዳት ሲያስሞግስ ፤ አዲስ ፈጠራና ሙከራ እንደሚያስቀጣ የተማርኩት ያኔ ነው : :

ደግሞ በሌላ አመት የህብረተሰብ ትምህርት ክፍለ ጊዜ ስለ ዘጠኙ ፕላኔቶች ስንማር እጄን አወጣሁና ፣ “ቲቸር ፣ ለመሆኑ ከመሬታችን
ውጪ ሌሎች ፕላኔቶች ውስጥ ሰዎች ይኖራሉ?” ብዬ ጠየቅኩ : :

ቲቸር "ምን እዚህ...! ደብተራችሁን፣ እንኳን በቅጡ አታነቡም : :ስለ ሌላ ፕላኔት አስበን እንራቀቅ ትላላችሁ" በሚል ውረፋ ክፉኛ አሸማቀቀኝ።

አርቆ ማሰብና መመራመር እደሚያስኮንን የተማርኩት ያኔ ነው : :

አድጌ ፤ መስሪያ ቤቴ ያጸደቀው መሪ ዕቅድ ፣ ገንዘብ እደሚያባክን ሲገባኝ ፤ ቅዳሜና እሁዴን ሰውቼ አዲስ መሪ ዕቅድ አርቀቅኩና ሰኞ
ላይ ለአመራሩ አቀረብኩ : :

“የመስርያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች ከስድስት ወር በላይ ፈጅተውና ለፍተው ያዘጋጁትን ዕቅድ በመናቅና ባስመታዘዝ” ጥርስ ተነክሶብኝ
ተገመገምኩ ። እሱን ተከትሎም የደረጃና የደሞዝ እድገት ታለፍኩ ፡ ፡

ቀናነት ከባድ ዋጋ እኝደሚያስከፍል የተረዳሁት ያኔ ነው : :

አሁን ታድያ በእድሜዬ ቶና ላይ ሆኜ ፤ ከጊዜና ኑሮ በተማርኩት መሠረት....

አዳልቼ ስሰጥ “ደግ ሰው” እየተባልኩ ፤

ከድሀ ነፍጌ ባስጠጋ እየሆንኩ፤

በአውራ ዋሾነቴ ሚስጥር ጠባቂ እየተባልኩ ፤

ጥያቄ ሳልመልስ “ምሁሩ” እየተባልኩ ፤

የተሰራን ገልብኩ “ፈጠረ” እየተባልኩ ፤

ቀና ባለመሆን ሽልማት እያፈስስ ፣

ደልቶኝ እኖራhሁ : :

ጨረስኩ ...
201 views" Aysanew " Mente", 08:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ