Get Mystery Box with random crypto!

......................ቃል ኪዳን........................ በብዕሬ ለቀወ | የፋኖስ ንፅረቶች (✍በአይሳነው)

......................ቃል ኪዳን........................

በብዕሬ ለቀወሶ ብዙ ቃላቶቸን ነበረ ስሰድር
የሚጣጣመውን እየመራረጥኩኝ
ለማዋደድ ስጥር
የቃላት ወንዞችን በነጣው
ሜዳላይ ለማፍሰስ ስታትር
ብዙም አልከበደኝ አንዱን ከአንዱ ሳስር፡፡

የልቤን ሀሳብ ልብ
እጅግ በርቶ እንዲታይ
ከፅሁፌ በላይ አስቀምጬ ከላይ
ሀሳቤን ስዛራው መስመሩን ሳልለያይ
አንዳች አልታከተኝ
ሁሉን በአንኩሮት ሳይ
ለካስ ልቤ ኖሩዋል ውጪን ሲያሳየኝ
ዳር ዳሩን ሲያፅፈኝ
መች ውስጡን አስነካኝ
የልቤ ውስጥ መድማት
ዛሬ አይኔ አሳየኝ : :

ከአይኖቼ ሚወጡት ነጭ የነበሩት
በጠቆረው ፊቴ ወርድው የሚፈሱት
ዛሬ ተቀይረው ቀይ ደም በሆኑት
የልቤን ውስጥ ህመም
ካአይኔ ተረዳሁት፡፡
እንደለመደብኝ ብዕሬን
አነሳው ልቤኑ ልፅፈው
ቃል ኪዳን በሚለው
ሁለት በሆኑ ቃላት በታሰረው
ለመፅሀፍ ቀሎ ለድርጊት ከራቀው
በፅሁፍ ስናየው እጅግ በሚቀለው
ሀሳቤን ጀመርኩት ልቤንም ላፅናናው
ነገር ግን አልቻልኩም እጅጉን ከበደኝ
ያን ሁሉ ቃላቶች የፃፉት እጆቼ
ጆሮ ዳባ አሉኝ
አይምሮዬ ከድቶኝ ማሰቡም ተሳነኝ
ሁለት የሚመስሉ ስናያቸው አንሰው
አንዱ ለአንዱ ሲሰጥ
በጣም የሚቀለው
እኔ ጋር ሲደርስ ግን ተራራ የሆነው
ብዕሬ እንኳን ታየኝ ለመፃፍ ስሞክር
ቃል ለሚለው ቃል
ማልቀሱን ትቶ እንባውን ሲቋጥር፡፡

አይሳነው ( ምንቴ )
@fanos_am24