Get Mystery Box with random crypto!

አምራች ኢንተርፕራይዞች የሚሳተፉበት 'የኛ ምርት' የተሰኘ አውደርይና ባዛር ተከፈተ አዲስ አበባ፣ | FBC (Fana Broadcasting Corporate)

አምራች ኢንተርፕራይዞች የሚሳተፉበት 'የኛ ምርት' የተሰኘ አውደርይና ባዛር ተከፈተ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አምራች ኢንተርፕራይዞች የሚሳተፉበት ሀገር አቀፍ አውደርዕይና ባዛር ''ኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት'' በሚል መሪ ሃሳብ ዛሬ በስካይ ላይት ሆቴል ተከፍቷል፡፡

አውደርዕይና ባዛሩ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል እና የፌዴራልና የክልል ተቋማት አመራሮች በተገኙበት ነው የተከፈተው፡፡

ከ100 በላይ በጨርቃ ጨርቅና አልባሳት፣ በቆዳና ቆዳ ውጤቶች፣ ግብርና ማቀነባበር፣ በኢንጂነሪንግ ምርቶችና በፈጠራ ስራዎች የተሰማሩ አምራች ኢንተርፕራይዞች ተሳትፈዋል፡፡

ሀገር አቀፍ አውደርዕይና ባዛሩ ከታሕሳስ 3 እስከ 7 ቀን 2016 ዓ.ም ለሸማችና ጎብኚዎች ክፍት ሆኖ እንደሚቆይ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት መረጃ ያመላክታል፡፡https://www.fanabc.com/archives/226392