Get Mystery Box with random crypto!

ፋና ብዕር

የቴሌግራም ቻናል አርማ fanabeire — ፋና ብዕር
የቴሌግራም ቻናል አርማ fanabeire — ፋና ብዕር
የሰርጥ አድራሻ: @fanabeire
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 845
የሰርጥ መግለጫ

ፋና ብዕሮች ነን
ለ እናንተ ካለን የጥበብ ማዕድ አብራቹን እንድትቆርሱ መሦባችንን አቀረብን
የጣፈጣችሁን አጣጥማቹ ያሳነስነው
ካለ ደሞ @fanabire በዚ ይንገሩን
የተሰማችሁን ሀሳቦች አጋሩን ለመታረም የሚተጉ ልቦች አሉን
ሀሳቦቻችሁ የብርታት ስንቆቻችን ናቸው እና በርቱ በሉን እንጠነክራለን ስህተቶቻችንን ጠቁሙን እንታረማለን
@fanabeire
፠ፋና ብዕር፠

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-29 19:43:54 መድሃኒት
""""""""""""
ለምን ዲኝ እናጢስ?
ምን ይረባል ከርቤ?
የምን ባላውልያ?
የምን ባለድቤ?

ቀልቡ ተሰውሮ ፥ ለጠፋው ብልሃት
አዋቂዋ አንቺ ነሽ ፥ የቡዳ መድሃኒት!

አረጋኸኝ መንገሻ(ፋና ብዕር)
417 views16:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 19:59:14 ሃሰሳ!
""""""""""
ስሜት ፣ እምነት ፣ እውነት
እኔ ፣ አንቺ ፤ ፍርሃት...

አንድ ጎዳና ላይ ፥ ተጉዝን ባንድ እግር
ስንዳክር አነጋን ፥ ለማይቋጭ ፍቅር!

አረጋኸኝ መንገሻ(ፋና ብዕር)
560 views16:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 19:27:39 ጥያቄ
"""""""""""""""
ለሰላም መዘመር
እምነቴ ነው ላለኝ
ለዛ ባለ ጦማር
ጥያቄ ነበረኝ።
የተናገርከው ቃል
ፅንፍ እውነት ካለበት
ብዕር ይጣላል ወይ
ጠመንጃ ለማንገት

ብላችሁ በሉልኝ።

ቤተልሔም አባይ(ሰንፔር)ፋና ብዕር
314 views16:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 19:42:28 ሃቅ
""""
በድን ገላን ማቀፍ፥
በሙት ልብ ማረፍ፥

ራስ ያሳንሳል ፥ ይንዳል ምሰሶ
ከሃዘን ያዋዳል ፥ ሳቅ በእንባ ለውሶ!

አረጋኸኝ መንገሻ(ፋና ብዕር)
887 views16:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 18:30:52 * ሴት አላምንም! *
-------------------
ዘጠኝ ወር አርግዤ
አምጬ ወልጄው
ፈግጌም ተክዤ
በልቤ አቅፌው ፤
( ፍቅርን ላሞህረው )
በመውጣት ፥ በመውረድ
ስዬ አሳድጌው
ክፋት ሳላናግድ
በጎነት ሸልሜው ፤
( ከ'ምነት ላዋህደው )
በህይወት ሳያድግ
በ'ድሜ አደገና
በስሜት ሲፋተግ
በልቡ ሳይጠና --
( ለሚኖርለት ሃቅ
መሞትን ሳይሰንቅ ፥
ለሞተለት እውነት
ሳይቆም ሊኖርለት )
""እማዬ አሁንስ በጣም ነው ያስጠላኝ
ከ'ንግዲህ በኋላ ሴት አላምንም"" አለኝ!
( እጅግ የደነቀኝ
መጥሬቱ የገባኝ )
የፍቅር ፥ የእምነት ምሳሌው የሆንሁት እናቱን አስቀምጦኝ
ሴት እንደማያምን ለሴቷ ነገረኝ!

A.P.N.K. -- የሜሮን
367 views15:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 19:41:36 ነሽ!
"""""

መስከረም ነሽ መሰል፥ በክረምት አባቢ
በአደይ ተሞሽረሽ ፥አምረሽ የምትጠቢ።

ፀደይ ነሽ ለጊዜው ፥ ለሃዘንና ዕንባ
ሳቅ ለራቀው ክረምት ሆድን ለሚያባባ።

እውነትም ንጋት ነሽ ፥ ፀሃይ የሳቅ ዕንቁ

ግን ይሄን ማን ያውቃል...

እንደኔ በወቅቱ፣
በክረምቱ ጭቃ ዝለው ካላወደቁ!

አረጋኸኝ መንገሻ(ፋና ብዕር)
866 views16:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 18:46:04 * ግራ ጋቢ ፈታይ! *
---------------------
ይወአ ዜጊ ጉደ ንትንናት ልማግደይ
ይባአ ዳሁይደንእ ርገአ ሞስ ልጣሸይ!

ልመዐ ውለአ ንመዘ ሮዞ ልሳለመይ
ልየቃበ ርቅፍ ስርው ንሙድንወ ልላድገይ!

ትለየለከ ትላጠ ትሳ'ያጉየ ንሰባ
ትለሁለ ችቶጌ ውተዝገተ ንጡሸባ!

ስንኳንእ ሞርከለ ምሮድንዘ ነከመ
ስትለ'ለ ዱቀማ ትጦንቅ ነለሰመ!

ንትሞ ንለብቀተ ፥ ትሟሟአ ንጋሰያ
ንምለ ጋነ ችዮባ ንንሆ ፋስተ ንጣያ!

ይዳገ ፊናሸተ ፥ ቹሟ ፊናሸአ ናንልለባተ
ይናል ንፍነሸማ ውተሞ ዩሳያላ ርክም ናፋጣተ!

ማኛእ ድንግ ንነ -- ተንናእ ፍጫንርቅ
ማድአበ ንጠርቆተ -- ንለምልመተ ፍጥርቅ!

ንችሳራከ ፍዛ ይላ ያቢረጥመ ንተርሠተ
ንችሳራበ ችቦጅ ፥ ንችሳራ ንላበተ!

ንምለ? ንምለ? ንምለ? ንምለ ህዚ'ለ ንቃበ?
ንምበ ፥ ስንምለስ ርቅፍ ንራዘየእ ሉጥ ንብለቀበ?

ውበስባ ፥ ውመልባ ምጹፍበ ኝባገልአ
ውነማ ዳረተየ ሁችካባ ኝዱረስአ?

A.P.N.K. -- የሜሮን
352 views15:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 20:30:14 ጉድለት!
""""""""""
ሰው እርቃኑን ቀረ ፥ ካጀብ እየሸሸ
ከማያከርመው ቤት ፥ ላያድር እያመሸ!

ሰው ከኑሮ ጓዳው ፥ ተሰፋ ከነጠፈ
የነገ ቡቃያው ፥ ፍሬ ከረገፈ

ከስጋ መከራ ፥ ነብስ ሞት ይጠ'ላል
ከሰውም ሰውነት ሰውነት ይጎድላል!

አረጋኸኝ መንገሻ(ፋና ብዕር)
930 views17:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 19:22:23
ሰላም እና ጤና ለናተ የተከበራችሁ የፋና ብዕር ወዳጆች እነሆ ካነበብነው የተማርንበትን እናጋራችሁ
የመፀሐፉ ርዕስ = ሜሎሪና(ስውር ጥበብ)
የመፀሐፉ ደራሲ = ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ

የመፀሐፉ የገፅ ብዛት =209
መፀሐፉ በ19 ምዕራፋት የተከፈለ ሲሆን በሰኔ 2012ዓ.ም በ165ብር ለንባብ በቅቶ ተወዳጅነትን አትርፏል።

ይዘቱ የስነ-ልቦና መፀሐፍን መስሎ ባስደናቂ ልቦለዳዊ አተራረክ መካሪ እና የሰው ልጅ አእምሮውን በሚገባ ከተጠቀመበት የተሻለ የሂወት መስመር እንደሚኖረው ያስገነዝባል።
"ያንተነትህ ውቅር ፣ ትዝታና ተስፋ ቢኾኑም፣ ዛሬን ግን እንዴት መኖር እንዳለብህ እወቅ። ምክንያቱም፦
፩ ትላንትን የምታርመውም ኾነ የምታድሰው ዛሬ ላይ ኾነህ ነው።
፪ ነገ ውብ የምትኾነውዛሬን ስትንከባከባት ነው።
፫ ነገ ከተስፋነቷ በስተቀር ያንተ አይደለችም ተስፋህ እውን ኾና የምታገኛት ግን ዛሬን በተጠቀምክባት ልክ ነው። " ከመፀሐፉ ገፅ 188 የተቀነጨበ
መፀሐፍትን በግዢም ሆነ በኪራይ ለማግኘት "ዝዋይ ራያ መፀሐፍት መደብር"ን ይጎብኙ።

መልካም ንባብ ለተሻለ አስተሳሰብ!

ፋና ብዕር
845 views16:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-16 19:00:43 ባለ እዳዋ እኔ
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
አዳራሹ ቤቴ ጠንበለል ማገሩ
አንተ ፍረስና ይሸበር ሰፈሩ
ምን ያሸብረዋል የሰፈሩ ሰው
የመጣውን እዳ እኔ ልችለው

ቤተልሔም አባይ(ሰንፔር)ፋና ብዕር
370 views16:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ