Get Mystery Box with random crypto!

ጉድለት! '''''''''' ሰው እርቃኑን ቀረ ፥ ካጀብ እየሸሸ ከማያከርመው ቤት ፥ ላያድር እያመ | ፋና ብዕር

ጉድለት!
""""""""""
ሰው እርቃኑን ቀረ ፥ ካጀብ እየሸሸ
ከማያከርመው ቤት ፥ ላያድር እያመሸ!

ሰው ከኑሮ ጓዳው ፥ ተሰፋ ከነጠፈ
የነገ ቡቃያው ፥ ፍሬ ከረገፈ

ከስጋ መከራ ፥ ነብስ ሞት ይጠ'ላል
ከሰውም ሰውነት ሰውነት ይጎድላል!

አረጋኸኝ መንገሻ(ፋና ብዕር)