Get Mystery Box with random crypto!

ተጨማሪ መረጃ ከወልድያ በዛሬው የወልዲያ ስብሰባ የተሳተፉት ወካይ ማህበረሰብ የሀይማኖት አባት ፣ | 𝗙𝗔𝗡𝗔 𝗧𝗩 (ፋና)️ ️️

ተጨማሪ መረጃ ከወልድያ
በዛሬው የወልዲያ ስብሰባ የተሳተፉት ወካይ ማህበረሰብ የሀይማኖት አባት ፣ የሀገር ሽማግሌ ፣ ወጣቶችና ሙህራኖች ሲሆኑ የወልዲያ ከተማ ከንቲባ ዱባለ አብራሬ ፣ ከመኳከያ ጄኔራሎችና ኮሎኔሎች እንዲሁም አቡነ ኤርሚያስ አወያይ ነበሩ
የተነሱ ጥያቄወች

1 - የማንነትና የወሰን ጥያቄ ሳይፈታ ሸኔና ህወሀት ትጥቅ ሳይፈቱ አማራ የጥቃት ሰለባ የትኩረት ኤሪያ እየሆነ ባለበት ሁኔታ ለምን ልዩ ሀይል ይበተናል

2 - የሌሎች ክልል ልዩ ሀይሎች ትጥቅ አፈታት ሁኔታ

3 - የተሾመ ቶጋ ንግግር አንድምታ ምንድነው

4 - ጄነራል ተፈራ ማሞ ህክምና የተከለከለው ለምንድነው ?

5 - ለዳግም ወረራ እያመቻቻችሁን ነው ታሪካዊውን ህዝብ ለማዋረድ እየሰራችሁ ነው መንግስትም ፕላን አድርጎ እየሰራበት ነው የኛ አመራሮችም ትግል እያደረጋችሁ አይደለም

6 - ውሳኔውን አንቃወምም በውሳኔው ዙሪያ ግን በየደረጃው ውይይት መደረግ ህዝብ መምከር መወያየት ነበረበት ይሄ የፖለቲካ አመራሩ ጥፋት ነው ለምን ሁሌ ትእዛዝ አስፈፃሚ ትሆናላችሁ በሚል ለከንቲባው ቀርቧል

7 - የአማራ ልዩ ሀይል በሰራው ስራ በከፈለው መስዋትነት ልክ ሪስፔክት አልተደረገም ይባስ ብሎ የስም ማጥፋት ዘመቻ እየተደረገበት ነው

8 - ልዩ ሀይሉ እንዳይረጋጋ እንዲዋከብና ሆን ተብሎ እንዲበተን አሁን ላይ ወደ ተፈቀዱ የፌደራልና የክልል የፀጥታ ተቋማትም እንዳይቀላቀሉ ሆን ተብሎ ነው እየተሰራ ያለው የሚሉና ሌሎችም በርከት ያሉ ጥያቄወች ከ15 በላይ በሆኑ ጠያቂወች ተነስተው
ምላሽ
በሁሉም አወያዬች ምላሽ ተሰጥቶበት ጥያቄውም ወደ ላይ እንደሚላክና አንድ ቤተሰብ የሆነው የሰሜን ወሎ ህዝብና መከላከያ መካከል ቅራኔ እንዳይፈጠር ጥንቃቄ እንዲደረግ መከላከያ ከልዩ ሀይሉ ጋር በቅርበት የሚተዋወቅ ለአንድ አላማ የተዋደቀ መስዋትነት የከፈለ ሬሽን የተካፈለ ሀዘንና ደስታን ያሳለፉ ስለመሆኑ
መከላከያ የተሰጠውን ተልእኮ ፈፃሚ እንደሆነ ግን ደግሞ ሁሉንም ነገር ማህበረሰቡን ባከበረና በትእግስት እንደሚያደርግና አጠቃላይ በተነሱት ጥያቄወች ዙሪያ በየደረጃው ምክክር እንደሚደረግበት ወጣቱም ከመንገድ መዝጋትና ሌሎች ህገወጥ ድርጊቶች እንዲቆጠብ በመግባባት ተጠናቋል ሲሉ የውይይቱ ተሳታፊዎች ለአዩ ዘሀበሻ ገልፀዋል።