Get Mystery Box with random crypto!

በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ ኢትዮጵያ ገብተው በሕገ-ወጥ የወርቅና የተለያዩ ማዕድናት ፍለጋ ላይ የተሰማ | 𝗙𝗔𝗡𝗔 𝗧𝗩 (ፋና)️ ️️

በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ ኢትዮጵያ ገብተው በሕገ-ወጥ የወርቅና የተለያዩ ማዕድናት ፍለጋ ላይ የተሰማሩ የውጭ ሀገር ዜጎችና ተባባሪዎቻቸው በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል አስታወቀ።

የፀና የጉዞ ሰነድ፣ የመግቢያ ቪዛ እንዲሁም የመኖሪያ ፍቃድ ሳይኖራቸው በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ ኢትዮጵያ ገብተው በጋምቤላ ክልል በሕገ-ወጥ የወርቅና የተለያዩ ማዕድናት ፍለጋ ላይ የተሰማሩ 45 የውጭ ሀገር ዜጎች እና ሦስት ኢትዮጵያውያንን ከነ-ኤግዚቢቱ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል ይፋ አድርጓል።