Get Mystery Box with random crypto!

ሁሉም ለምን ያልፋል? ( በእውቀቱ ስዩም) የጣፈንታ መዳፍ ደስታና መከራን: እያፈሰ ሲናኝ 'ሁሉም | ፅሁፍ በፋኢዛ 🤗

ሁሉም ለምን ያልፋል?
( በእውቀቱ ስዩም)

የጣፈንታ መዳፍ
ደስታና መከራን: እያፈሰ ሲናኝ
"ሁሉም ያልፋል " ብሎ : ማነው የሚያፅናናኝ?
ግራ በተጋባ :በዞረበት አገር
ካንቺ የምጋራው :ሰናይ ሰናይ ነገር
ፊቴን የሚያበራው :ያይንሽ ላይ ወጋገን
ዛሬ ተለኩሶ : የሚያሳየኝ ነገን
ለምን ሲባል ይለፍ : ያንን መሳይ ፍቅር
ደሰታሽ ይገተር: ሳቅሽ ቆሞ ይቅር!!
በብሩህ ቀላማት የተሸላለመ
-የተዋበ ህልሜ
በሁለት ጦርነት: መካከል የቆመ
-አጭሩ ሰላሜ
ያፍላነት ወኔየ : የጉርምስና አቅሜ
ነበር ተብሎ እንዳይቀር :እንዳገኘው ወትሮ
ባለበት ላይ ይቁም :ባስማት ተገትሮ::
እና
ከጣፈንታ መዳፍ: ሞልቶ ከሚፈሰው
በሰው የሚደርሰው
ለሰው የሚደርሰው
በጊዜ ኬላ ላይ : ተዛዝሎ ሲሰለፍ
በጎ በጎው ይቆይ : ክፉ ክፉ ይለፍ!!

...

ሕያው

ወደ ምንም..


ህመም ፀናሽ ስሱ ልቤ ሀያል ሆነ ጣር አወቀ.
ያ'ይኔ ጀርባ የ'ምባ ኮዳ ከረጢቱን አደረቀ.
ደነደነ አካላቴ የደም ጭቃ ተላመደ.
የገላዬ እርጥብ ጠረን የግፍ እጣን ጪስ አወደ.
ወደፊቴ ተካካደ ከህልሜ ዓለም ከነገዬ.
ተስፋን ተፋሁ ከናካቴው እኔም ሞትኩኝ ከዘገዬ.

እኔነቴ..
በቃ እንግዲህ እንጃለቱ ሰውነትን ከሰበረው.
እንደ ምንም ተፈጥሬ ምንምን ነው የምኖረው..


...


" ጥበብ እውነትን ለማጉያ የምንጠቀምበት የውሸት ዓይነት ነው። "

#ፀሐይ ለምን ቢጫ ሆነች?


" ቢያንስ ራሳቸውን ሲያዳምጡ አይረባበሹም። "

#ባልንጀሮቹ

" እንደ አህያ ሥጋ አልጋውን ትቶ አመድ ላይ የተንከባለለው ሰውዬ፣ በአመዳሞቹ ግዛት ደግሞ ሌላ ትርጓሜ እንዳለው ማን በነገራቸው። ማን በነገራቸው አመድ የወርቅ እኩያ እንደሆነ በዛኛው ግዛት።"

#ፍፁም

" ምንም ነገር እኮ በመሠረቱ አይጠፋም። ጨክኖ ያለ-መፈለግ ወይም ያለመፈለግ ይሆናል እንጂ ...ምንም ነገር ፈላጊ ካለ እኮ ጨርሶ አይጠፋም።"

#የሩሲያ ፎቶግራፎች

" ምንም ነገር የማያረባ ሰው አይረባም ይላሉ። ወይ ልጅ፣ ወይ ብር፣ ወይ ስም፣ ወይ እውቀት፣ ወይ ጽድቅ ... ሰው እስከሆነ የሆነ ነገር ማርባት አለበት ባይ ናቸው፤ ባዮቹ። ካልሆነ "አይረባም!" "

#ግስ አርቢዎቹ

"ይመስላል ዘላለም" ከተሰኘው የደራሲ ሌሊሳ ግርማ መፅሀፍ በሀይላይተራችን ከተቀለሙት የተቀዳ።