Get Mystery Box with random crypto!

መ ረ ቅ: ሄዶን ሙዚቃ እየሰማን ያሳለፍነው ደስታ ላንቺ ብቻ ሆነ መንፈሴ ትዝታ እሩቅ ያለሺ | ፅሁፍ በፋኢዛ 🤗

መ ረ ቅ:
ሄዶን

ሙዚቃ እየሰማን ያሳለፍነው ደስታ
ላንቺ ብቻ ሆነ መንፈሴ ትዝታ
እሩቅ ያለሺው ግማሽ ሰውነቴ
በቃ ተለያየን ተቆረጠ አንጀቴ
(ዘፈን)

- ግለ ወሲብ ታውቃለህ?

- አውቃለሁ!

- ምንድን ነው?

- ፈገግ ብሎ ... ግብረ መዳፍ ማለት መሰለኝ! አለ።

- ከገዛ ገላህ ጋር ተዳርተህ ታውቃለህ?

- በስመአብ!! ድንጉጥ ማማተብ ታየበት! ምን ማለት ነው እሱ ከገዛ ገላ መዳራት?

- እስቲ ግም አትሁን! ጥያቄ አይደል እንዴ የጠየቅኩህ? ዘፈን በሌለበት እስክስታ ይቀናሀል!!

- ከዚህ በላይ ዘፈን? ሀሳብህ አልገባኝም።

- ይሄ ሀሳብ አይደለም! ታሪክ ነው።

- ታሪክ?

- እንደ ነገሩማ
እድሚያችንን ቀድመን ነበር ም'ናረጂ
ያማልክቱ ፀሎት ቢጠብቀን እንጂ።

እንደ ነበሩማ
ሞተን ነበር ሞትን መሞትን ቀድመን
እድሜ አማልክት ሆኖ እድል ባይጀባን።

- እድል? ለምን ታወዛግበኛለህ?

- አትለጠፍ!!

- ቀጥል ልስማህ...

- እንትሰማኝ ባይሆንም አወራለሁ። ታሪክ ልንገርህ?

- የምሰማው ነው የምታወራው?

- ነገር ቶሎ ይገባሀልና?

- በላ እያወራህ!

- ባለ አራት ገፅ ሺ ታሪክ
ገፅ አልባ አንድ እውነት

- ከእውነታዎች ገዝፎ ቢታወስ ጊዜ...

- ደሞስ በሳል ነህና?

- በልማ አውጋኝ!!

.
.
.

ይለጥቃል . . .
.
.
.

ካኖርንበት ስናነሳ...
.
.
.
ሄዶን

#ገፅ አንድ
ርዕስ የለውም!(ርዕሱ አይደለም።)

አጀብ ቢያውረው ቅንዝር ምንዝሬን
ተፈተለኩ ወደ ምድጃሽ
ባይበርደው ገላ መሞቅ ወጉ ነው
ፈቀድኩሽ ስልሽ እሺ በይ ከቻልሽ።

= አማልክቱ ጣልቃ ገብተው "ላስብበት" ብትል ጊዜ እሳቱ ጠፋ።

#ገፅ ሁለት
ፈቃድ አልባ ፈቃድ

ረመጥ ሳሳድድ ዘልቄ ከርስ
ፍም መስላ ቆመች እፊት ለፊቴ
እፍ እፍ ልበል ይብሰል መፍቀዷ
አንድም ለነፍሷ አንድም ላንጀቴ።

= አማልክቱ ጣልቃ ገብተው ንቃቴን ቢሰልቡት እፍ እፍታው በቀናት ተገምዶ መፍቀዷን አሳረርኩት መሰል።

#ገፅ ሶስት
ሰላቢ እውነት

ባጉል እፍታ ሲያር የከረመ
ሙት ያየ ገላ እንባ ሳይንደው
ነገን ያመነ ኩታ ደርቦ
ና ሲሉት ሄደ ወደ ወደደው።

= አፈሩ መልኩን ሳይቀይር አማልክቱ ጣልቃ ገብተው ተስፈኛ ኩታ የሸፈነውን በቋፍ የቆመ የከሰል ሀውልት ይነቀንቁት ጀመር።


.
.
.

ይለጥቃል . . .
.
.
.

ካኖርንበት ስናነሳ ...
.
.
.
ሄዶን

#ገፅ አራት
ተራማጅ ግዑዛን

አጀብ ያነገተ
ክንድ አልባ ጨርቅ አርጓል
የጉልበት ቁልቁለት
ወ'ዳይኖች ያርጋል
ወዲያ ካ'ስፋልቱ ዳር
ትዕንግርት ይፈልቃል
የፈረሰ ገላን በጉያው ሸክፎ
በነግ የተተካ ነጠላ ይስቃል። ...

= አማልክቱ ፈንጠር ፈንጠር ብለው ያስካካሉ።

ምንስ ይሆን ሸረቡ?
የትስ ይሆን መረቡ?
ማንስ ያያል ቢያውቀው?
ማንስ ያውቃል ቢያየው?
ምነው? ምነው?

#ከፍርሀት ባሻገር

ፀንሻለሁ ብል ተኝቶኝ ስጋት
ነግ በኔ ብለው ደጄን ላይረግጡ
ኳ! ባለ ቁጥር ሽብር ሸመታ
ምን በጀ ማርገዝ ምን በጀ ምጡ?

ብዬ
ራሴን በጀርባዬ አዝዬ
እጄን ከ'ጇ ጣል ባረገው
...

= እሳት የራበው የከሰለ ገላዋ ቀዝቅዟል። የቀዘቀዘን በስሱ ትጎነጫለች: አከላቷን ሸብሽባ ጥግን ተጠግታለች። ራሷን አሸማቀቀች ወይስ ራሷን ከለከለች? ጥያቄዎች እንደ አሸን መፍላት ጀምረዋል። ከነበር የተማረ ልብና ዛሬን ያመነ አዕምሮ ግን ከጥያቄዎች ባሻገር፤ ካ'ድካሚው ጉዞ ማበቻ ፤ ከምልጃና ካሳ ዕርገት ፤ ፍቅር ውስጡ የደበቀ ስርቻ ይታያቸው ነበር። ጥንድ አቅም ስርቻ።


ዝምዝምታ አየሩን ሞላው
መልስ አዝኗል ብቻውን ቀርቶ
ቢመኝስ ማን ይድረዋል?
ጥያቄን ጥያቄ አግብቶ።

= አመፀኛ ወኔ ከዝምታ ተጋፍቶ መፍቀዷን ጠየቀ። ሀፍረት የለበሰ ገጿን ወደ መሬት ደፍታ ...
አንዳንዴ... ለመፍቀድ ከፍቅር ይልቅ ስብዕና ይቀድምና የሴትነት መለኪያ መስሎ ያታልለናል። ከመውደድ ስም ይቀርብና ካመኑት ሳይሆን ካወሩት መዋል፤ ካወሩት መታየት ፍቅር ይሆናል።(ይመስላል።)

እንዲያ ነው የሆነው
እንዲያ ነው የሆንኩት
አርጓል ፍቅርህ ካልነበረበት
ኦና ነው ልቤ ውስጡ ቢከፈት።

.
.
.
ይለጥቃል . . .
.
.
.

ካኖርንበት ስናነሳ ...
.
.
.
ሄዶን

ባዕዱ እውነታ ከመሻቴ ባያስጥለኝ፤ መፍቀዷን ዳግመኛ ተማፀንኩት።


ጨው ቀመስ ቃልሽ ለጆሮዬ የመረረኝ
ባዕድ ምላሽሽ ከመሻቴ ባያስጥለኝ
ፈቃድሽን ልማፀነው ብንበረከክ
ረዳኝ እንጂ ልሞ አፈሩ
ስር ጉልበቴን መች ሻከረኝ?

ትጠየቅ!

ፀንሻለሁ ብል ተኝቶኝ ስጋት
ነግ በኔ ብለው ደጄን ላይረግጡ
ኳ! ባለ ቁጥር ሽብር ሸመታ
ምን በጀ ማርገዝ ምን በጀ ምጡ?
ብዬ ...
ራሴን በጀርባዬ አዝዬ
እጄን ከ'ጇ ጣል ባረገው
ደስታዋን አጠወለገው።
ክሰል ገላዋም ተናደ
ከተፋኝ ጥልቀት ተዋሀደ
ታሪካችንን አፈር አልብሳ
ዳግም በቀለች ሙት አፈር ልሳ።

.
.
.
ይለጥቃል . . .
.
.
.

ካኖርንበት ስናነሳ...
.
.
.
ሄዶን

#ገፅ አምስት
የጠፋው ገፅ

የስንብት ቃል

እንደ ቅርበትሽ ባልፀና
ነበር ጎትቶ ቢያርቀኝ
ቃላት ሸሽተው ከምላሴ
ዝምዝምታው ልቆ ቢቀለኝ
ለመራቄ የሚያዋጣ
ፍቅርሽ ውስጤ ነበረኝ።
#ስሞታ


#ገፅ አልባ አንድ እውነት

አድባሬ ናት ብዬ በምልልስ ብሞግታት፡ ቅንዝር ምንዝር ልኩን ላያልፍ ፡ ቀኑን ጠብቆ መንግስቴ ወደቀ። ዘውዴን ወዲያ አሽቀንጥሬ ልማድ ላ'ድን ወደ ማላውቀው ወደማያውቀኝ ኮበለልኩ ፤ ራቅኳት ብዬ ከራቅኩበት ሳለሁ ዓይኔ መሀል እስካገኛት፡ የሌለሁባት የሌለችብኝ ይመስለኝ ነበር።

#ዓይኔ ዓይኑ ሆና

ቅጥሩ ተንዶ
የመሸገበት ሲጋለጥ ዱሩ
ዘመን ያፀናው ላልቷል ጉንጉኑ
ዓያት ስታየው ዓይኔ ዓይኑ መሀል
የፅልመት በትር ሆና ብሌኑ።


= ከገዛ ገላዬ ከመዳራት ባ'ማልክቱ እርዳታ አመለጥኩ። አቤቱ አንድያ ዓይኔን ጠብቅልኝ። በእርሱ ህልውና ነውና ብሌኑም፤ ትርጉሜም ነፍሳቸው ህያው ሆኖ የሚቀጥል።

የአማልክቱ በረከት ይደርብን!!
አሜን!


የልደት ስጦታ!
Ⓒhedon2022