☞ ዝክረ ኸሚስ 6 . የሩቅ እንጉርጉሮ ።።።።።።።።።።።።። ሰው በመሆን ንጋት ፣ ሰው በመሆን መንገድ በሓድራ አደባባይ ላ‘ብሮነቱ ሰንደቅ ፣ ሰው የማለት ዜማ በመሀባ ቅኝት ቃሉ ሲንደቀደቅ ፣ ( ፍቅር ምን ይመስላል ... ! ) የኔነትን ዋርካ ... ላብሮነት መገንደስ ?! ክፋት ግብግቡን ...ጥል መሻቱን መዳስ ?! . በኒያ ኮርቻ ፣ በጡሀራ ልጓም ፣ የከራማውን ኩል በሂማ ወለባ ጀማው ጋራ ኩለው ፣ ቼ በለው ለሀገር - የመኣና ፈረስ በጀዝም ኮልኩለው፣ ( እንደምን ነው መድረስ ... ! ) የኽልቄውን ሃጃ ... በአማና ማድረስ ?! ያገሬውን ሰማይ ... ለ‘ርዚቅ መኸር ማረስ ?! . እኮ ... ( ፍቅር ምን ይመስላል ... !? ) ( እንደምን ነው መድረስ ... !? ) . ሃያማ ንገሩኝ ... የቀን መቅናት መልኩ ... መጠኑ ቀለሙ ?! ከአዚማም ግርዶሽ እራሱን ፈልቅቆ ንቃት መሸለሙ ?! . ሃያማ ንገሩኝ ፣ ላለማዝመም ማግሩኝ ። . ድንግር ባለው ልብ ፣ ብትል ባለው ቀልብ ፣ በኢማን ድግ ሊያስሩት ፣ እንደት ነው መሰተር ... ጥመት ሲንጨፈረር ፣ ነፍሴ እንደት ይመይዝ ... ለጋ አቅሌ እንዴት ይክረር ? . « ሓድራ አደባባይ ሁሉም ይታጫል ፣ ያገር ልጅ ሲቀር እንደት ይቆጫል ። » . ብላችሁስ የለ ! . ብቻ ባለሁበት ... . « ያ‘ብሮነት ድልድዩ መሀባ እያረጀ ሽበቱ ወረረው ፣ አንድ ሰው ብቻውን ይሻገር ጀመረው ። » . አዎ ... ! ይሄው ነው አውነቱ ። . ዛሬ‘ኔ እንደዋዛ ... ዘመንን ስናፍቅ ፣ ስስት ምቹ መቶኝ ፣ አቅሌ ሲጉረበረብ ፣ እሞዠርግበት ቀልቤ ጥፍር የለው በላኝ እንዳብላሊት፣ ያጎረፋችሁት አባይ ገላው ኸይሚስ ሽርጥ ሲል ለሊት። . . እንጂማ ... ምን የሞቀ ጠሀይ ... ምን የሰባ ጀንበር ፣ ምን ኣጀብ ጨረቃ ... ምን የኮከብ ገበር ፣ ምን የበለገ እጣ ... ምን የሞላው መክበር ፣ ( ምን ያማረን ዘመን ... ! ) የቀልብ መሰላል ማማውን ማግሬ ፣ በሩቁ መነጠር - በዘማች መስታዎት ባየው አሻግሬ፣ ጉድ በል ነው ... ነፍስያን እንደ ጨርቅ ፣ ከመናቀፍ እድፍ እያንጨፈጨፈ ... ምን ያጥበውን አቅል ... ምን ያለዝብን መንፈስ ፣ የመሀባው ጂረት ሰውነት ወጅሮ ይታየኛል ሲፈስ ። . እንጂማ ይታያል ይዳሰሳል ፍቅር ! እንጂማ ይሠማል ይደመጣል ፍቅር ! ሁሉም እንደ ልኩ ... እውነት ሲከፋፈል ... ውብ ቃሉ ሲፈሰር ! . እንጂማ ይነካል ... ገምሻራው አካሉ ፍቅር ይዳሰሳል ! እንጂማ ያለዝባል ወንዝ ነው ይፈሳል ! ( ሌት አለው ውብ ዜማ ... በሩቅ አብሰልስሎ የራስ እንጉርጉሮ ከራስ የሚቀማ።) _ Semir aklu 837 viewsسمير ايمي, 19:45