Get Mystery Box with random crypto!

በትግራይ ክልል ለወያኔ ስልጠና ሲሰጡ ሲያስታጥቁና ከጎኑ ተሰልፈው ሲዋጉ የነበሩ የውጭ ሃይሎች እን | 🇪🇹 E.Z መረጃ 🇪🇹

በትግራይ ክልል ለወያኔ ስልጠና ሲሰጡ ሲያስታጥቁና ከጎኑ ተሰልፈው ሲዋጉ የነበሩ የውጭ ሃይሎች እንዲሁም በሐገር ውስጥ ራሳቸውን የፌደራሊስት ሃይሎች ብለው እየጠሩ የትግራይ ክልልን ምሽግ አድርገው የቆዩ የታጠቁ ሃይሎች ከትግራይ ክልል ለቀው መውጣት ለአማራ ሕዝብ እንደትልቅ ድል እንዲቆጠር የሚያደርገው ጉዳይ ነው።
እነዚህ ፀረ-አማራ ሃይሎች ከትግራይ ክልል ለቀው የሚወጡ ከሆነም የአማራ ልዩሃይል በጥምር ጦሩ በትግራይ ክልል በሽሬ በአክሱም ወይም በአድዋ እንዲንቀሳቀስ የሚያስገድደው አንዳች የሕልውና ስጋት ስለማይኖርበት ለቀው ይወጣሉ።
የአማራ ልዩሃይል ወደትግራይ ክልል ማለትም ወደሽሬ ወይም ወደሌሎቹ አካባቢዎች ከዚህ በፊት ካለም የሕልውና አደጋ ስለነበረበት እንጅ በትግራይ ክልል ቆላ ደጋ ወይም ጋራ ሸንተረር የማቋረጥ ፍላጎት ስለነበረው አለመሆኑ እሙን ነው። ስለሆነም በትግራይ ክልል ያሉ የውጭ ሃይሎች እንደሚወጡ ሁሉ የአማራ ልዩሃይልም ካለ መውጣቱ የሚጠበቅ ነው።

በሕገ መንግስቱ መሰረት የተባለው እያሉ በወያኔ ትርጉም በአማራ ስም በተቆርቋሪነት ስም ተሰልፈው ወልቃይትንና ራያን ወደትግራይ ያካለሉ ወያኔዎችና አፍቃሬ ወያኔዎች ማወቅ ያለባቸው በሕገ መንግስቱ  ከዚህና ከዚያ ወዲያ ያለው የአማራ ወይም የትግሬ ክልል መሬት ወይም ወሰን ነው የሚል የተካለለ በሕገ መንግስቱ የተብራራ አንቀፅ አለመኖሩን ነው።ምኞቶች ግን ስለመኖራቸው ያለ ልክ የሚጮሁ አጀንዳዎቹ ብቻ በራሳቸው ይናገራሉ።

ለማንኛውም ለኢትዮጵያ ስጋት ለመሆን ትግራይ ክልልን በምሽግነት መርጦ የነበረ የውጭም ሆነ የውስጥ የጥፋት ሃይል  ከእንግዲህ እንደፈለገ ለጥፋት አላማ የመፈንጨት ዕድሉ ጠባብ እየሆነ መምጣቱን ነው።

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet